Get Mystery Box with random crypto!

በመጀመሪያው ቀን ትውውቅ እንዴት ልገመግመው? #ተንቢሀት_ካውንስሊንግ (001) ጥያቄዬ የሚከተ | በሰለፎች መንገድ

በመጀመሪያው ቀን ትውውቅ እንዴት ልገመግመው?

#ተንቢሀት_ካውንስሊንግ (001)

ጥያቄዬ የሚከተለው ነው ፤
በመጀመሪያ ትውውቅ የምርጫዬን ዓይነት
እንደሆነ እንዴት ልገመግመው እችላለሁ?

ስብዕናውን ለመረዳት እና አስተሳሰቡን
ለማወቅስ ምን መጠየቅ ወይም መናገር
አለብኝ?

የተሳሳተ ምርጫ ላይ ወድቄ የስሜት ጉዳት
እንዳይደርስብኝ መጠንቀቅ እፈልጋለውና
እባካችሁ ምክር ለግሱኝ።

::::::::::::::

➴#ምላሽ:– ከሁሉም በፊት ከአላህ ጋር ያለሽ
ትስስር በጣም ጠንካራ ይሁን፤ ከአላህጋር
ያለሽ ትስስር ጠንካራ ከሆነ እና ዘወትር ዱዓ
ካልተለየሽ የጉዳዬችሽ ፍጻሜ ሁሉ ያማረ
እንደሚሆን አያጠራጥርም። አላህ እርሱን
ታዛዦችን ወደ መልካም መንገዶች ይመራል፡፡

ﻭَﻣَﻦ ﻳَﺘَّﻖِ اﻟﻠَّﻪَ ﻳَﺠْﻌَﻞ ﻟَّﻪُ ﻣِﻦْ ﺃَﻣْﺮِﻩِ ﻳُﺴْﺮًا
«አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለርሱ
መግራትን ያደርግለታል» ጦላቅ 4

ውዷ እህታችን!
በጥያቄሽ ላይ እንደቀረበው አይነት የህይወት
መንገድን የሚያስቀይሩ መንታ መንገዶች
ሲገጥሙን ምርጫን ወደ አላህ ማስጠጋት
መልካም መሸሸጊያ ነው፡፡ ፍርሃትና ስጋትን
ሁሉ ያጠፋል፡፡ አላህ ትክክለኛውን ምርጫ
እንዲያሳይሽ ከብዙ እና ብርቱ ዱዓ ጋር
ደጋግመሽ [እስቲኻራ] አድርጊ፡፡

ትዳር ላሠቡ ሁለት ጥንዶች የመጀመሪያ
ትውውቅ እና መተያየት በመሀላቸው
መፈቃቀድ እና ተቀራራቢ የነፍስ ፍሰት መኖሩን
ለመፈተሽ ወይም ለማወቅ የሚጠቅም ነው፡፡
በዚህ ሂደት ዐይን በሚያየው አካላዊ ገፅታ
አሊያም በንግግርና በውይይት መጣጣምና
መፈቃቀድ ሊፈጠር ይችላል።

ስታይው የምችደሰችበትና የምትወጅው
አይነት መሆኑንም ማስተዋል ያስፈልጋል ፡፡

በዚህ የመጀመሪያ ትውውቅ ወቅት አላህ
ከአንቺ ጋር ሁሌም እንደሆነ አስቢ፤ ራስሽን ብቻ
ሁኚ፤ ምን መናገር ወይም መጠየቅ እንዳለብሽ
በማሰብ ስሜትሽን አትረብሺ፡፡ እነዚህ ነጥቦች
ወደ ለትክክለኛው ምርጫ ያግዙሻል፡፡

ነገር ግን ይህ ሰው ትክክለኛ ምርጫ መሆኑን
ለማረጋገጥ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ባልሆኑ
መንገዶች መሠረታዊ የሆኑ በርካታ ወሳኝ
ነጥቦችን መመርመር እና ማጣራት ያስፈልግሻል፡፡

1) ለእምነቱ ያለው ትኩረት ምን ያህል ነው? ሰላት በህይወቱ ውስጥ ምን ቦታ አለው?ከሰዓት ከመዘውተር እና ከሁኔታ አንፃር በትክክል ሰላቱን ይጠብቃል?

ትክክለኛውን የትዳር አጋር ለማግኘት እነዚህ ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ማግኘት አለባቸው፡፡ ሰላቱን የሚጠብቅ ሰው ከአላህ ጋር ዘወትር የተሳሰረ ነው ፤ ከአላህገር የተሣሠረ ሰው አብሮ ከሚኖረው ሰው ጋር መልካም ግንኙነት እንደሚኖረው ይታመናል፡፡

2) ለወላጆቹ ምን ያህል መልካም ነው? ለወላጆቹስ በጎ ነውን? ይህን ጥያቄ ቀጥሎ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
ለወላጆቹ መልካም ከሆነ አላህን የሚፈራ እና የአላህን ውዴታ የሚፈልግ ሰው ለመሆኑ አንድ ማስረጃ ነው፡፡

፨ ከነዚህ ምላሾች በመነሣት ከዚህ ሰው ጋር የህይወት ጥምረት መፍጠር እምነት የሚጣልበት መሆኑን እና አለመሆኑን መገምገም ይቻላል፡፡

3) ከወንድሞቹ ፣ ከእህቶቹ ፣ ከጓደኞቹ፣ ከስራ ባልደረቦቹ አንዲሁም በዙሪያው ከሚገኙ ሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት ምን ይመስላል? ተወዳጅ ሰው ነው? ከሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት ጤናማ እና ያልተረበሸ ነው? ለሰዎች ያለው አቀራረብ ለዛ አለው?

፨ የእነዚህ ጥያቄዎች ምላሾች ደግሞ የማህበራዊ ግንኙነቱን ስኬታማነት ያሳያሉ፡፡

4) የህይወት ታሪኩ ምን ይመስላል? ቢያንስ ስለዚህ አጭር ነገር ማወቅ የኀላ ማንነቱን ለማወቅ ጠቃሚ ነው። ዕውቀት በመፈለግ ባሳለፈባቸው ትምህርት ቤቶች ፣ ሪዝቅ በመፈለግ ባሳለፈባቸው የስራ ቦታዎች እንዲሁም ኑሮውን ባሳለፈበት መንደር ትቶት ያለፈውን የህይወት ጠረን ጥሩ ይሁን መጥፎ ማሽተት ያስፈልጋል፡፡

፨ መልካም ሽታ የመልካም ስነምግባር ውጤት ሲሆን መጥፎ ሽታ የመጥፎ ስነምግባር ውጤት ነው፡፡

5) ተቀዳሚ ምልከታሽ ዲን ይሁን ፤ ገንዘብን ወይንም ማህበራዊ ክብርን ከዲን አታስቀድሚ፤ የነብዩ /የአላህ ሠላም እና ሰላት በእርሳቸው ላይ ይሁን/ የምክር ቃል ይህን ይላል፦

قال النبي صلى الله عليه وسلم: «إذا أتاكم من ترضون دينه وخلقه فانكحوه» الحديث

«እምነቱን እና ስነምግባሩን የወደዳችሁት ሰው የትዳር ጥያቄ ሲያቀርብ ተቀበሉት»

አደራ የምንልሽ ቤተሰቦችሽ የትዳር ጥያቄ ያቀረበውን ሰው አስመልክቶ የሚሰጡትን አስተያየት ቦታ እንዳትነፍጊው ነው። አስተያየታቸው በህይወት ተሞክሮዎች የተፈተሸ በመሆኑ ጠቃሚነቱ አያጠራጥርም፡፡
የምታማክሪዉን ሰው ልታውቂ ይገባል። በእድሜ ላንቺ እኩያ ወይም ካንቺ ያነሱ ያልበሰሉ ወጣቶችን ካማከርሽ፤ ቁሳዊ መመዘኛን ተጠቅመው ወይም ከቅናት ስሜት በመነሳት የማይበጅሽን ሀሳብ ሊለግሱሽ ስለሚችሉ ተጠንቀቂ።

ሁልጊዜም ለአላህ ትእዛዛትና ገደቦች ጥንቁቅ ሁኝ፡፡ አላህን መፍራት ያማረ ፍፃሜ የሚገኝበት ብቸኛ መንገድ ነው።

ﻭَاﻟْﻌَﺎﻗِﺒَﺔُ ﻟِﻠﺘَّﻘْﻮَﻯٰ

«መልካም መጨረሻም ለጥንቁቆቹ ናት!» ጣሀ 132

ተንቢሐት
↷⇣ ⇣↷
https://t.me/Alselfiy