2022-06-29 11:04:04
የብልት አለመቆም ችግር (Erectile dysfunction) ምንድን ናው? እንዴት ይከሰታል? መፍትሄዎች ምንድን ናቸው?
በዶ/ር ማትዎስ ሶቦቃ (PhD in Medical Research)
የብልት አለመቆም ከሰበት ዋና ዋና sexual dysfunction ችግሮች አንዱ ነዉ።
ይህ ችግር በዋናነት ወንዶች ላይ የሚታይ ችግር ነው።
ይህ ችግር ጉልህ የሆነ ጭንቀትን ወይም ከአጋር ጋር ያለ ግኑኙነት ላይ ችግር ይፈጥራል።
ችግሩ የዕድሜ ልክ ወይም በጊዜ ሂደት ዉስጥ የሚከሰት ሊሆን ይችላል።
የዕድሜ ልክ የወንድ የብልት መቆም ችግር ያለበት ሰው አንድም ቀን ከተቀራኒ ጾታ ጋር ስተኛ ብሊቱ በቂ ሆኖ አይቆምለትም፤ ግብረ ስጋ ግኑኙነት ማድርግ አይችልም። የዕድሜ ልክ የወንድ የብልት መቆም ችግር በብዘት ኣይታይም ነገር ግን በእድሜ እየጨመረ ይሄዳል።
በኋላ የመጣ የብልት መቆም ችግር ያለበት ሰው ህይወቱ ውስጥ በተወሰነ ጊዜ ተቀራኒ ጾታ ጋር ስተኛ ብልቱ በበቂ ሁኔታ ቆሞ ግብረ ስጋ ግኑኙነት ቢያደርግም በኋላ ግን ይህን ማድረግ አልቻለም። ይህ ችግር ከ 10 እስከ 20 በመቶው በሚሆኑ ወንዶች ላይ ይታያል።
ስንፈተ ወሲብ ከ50 በመቶ በላይ በsexual dysfunction ከሚታከሙ ወንዶች ሁሉ ዋና ችግር ነው።
ከሁሉም ወንዶች 75 በመቶው በ80 ዓመታቸው ስንፈተ ወሲብ ያጋጥማቸዋል።
የወንድ የብልት መቆም ችግር ኦርጋኒክ ወይም ሥነ ልቦናዊ ወይም የሁለቱም ጥምረት ሊሆን ይችላል።
ነገር ግን በወጣት እና በመካከለኛ ዕድሜ ላይ ባሉ ወንዶች መንስኤው ብዙውን ጊዜ ሥነ ልቦናዊ ነው። በስነ ልቦና ምክንያቶች ወይም በተጣመሩ ነገሮች ምክንያትም ሊሆን ይችላል።
ስንፈተ ወሲብ በብዙ ምክንያት ልመጣ ይችላል እነሱም
ብቃት የማጣት ስሜት፤
እንደ አጋር የማይፈለግ የመሆን ስሜት፤
አእምሮ ሕክምና መድኃኒቶች (የተወሰኑ ብቻ)፣
የደም ግፊት መድኃቶች (የተወሰኑ ብቻ)፤
የጨጓራ በሽታ መድኃኒቶች (የተወሰኑ ብቻ)፣
አካላዊ በሽታዎች ምክንያት (ለምሳሌ የልብ ሕመም፣ ከፍተኛ ኮሌስትሮል፣ የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ)፤
እምሮ እመም (ለምሳሌ ድባቴ፣ ጭንቀት፣ ውጥረት ወይም ሌሎች የአእምሮ ጤና መታወክ ሁኔታዎች)፤
ከመጠን ያለፈ ውፍረት፤
ስጋራ ማጨስ፣
አልኮልን በብዛት መጠቀም ፤
ጫት በብዛት መቃም እና ሌሎች ሱስ አምጪ ነገሮች መጠቀም ናቸው።
ቀጣይነት ባለው ግንኙነት ውስጥ ስንፈተ ወሲብ አጋሮች መካከል ያሉ ችግሮችን ሊያንፀባርቅ ይችላል፣ በተለይም አንድ ወንድ ፍላጎቱን ወይም ቁጣውን በቀጥታ እና ገንቢ በሆነ መንገድ ማስተላለፍ በማይችልበት ጊዜ።
የብልት መቆም ችግር ለውጥረት፤ድባቴ፣እና ጭንቀት ሊያመራ ይችላል።
ስለዚህ መታየት እና ህክምናን በጊዜ ማግኘት አስፈላጊ ነው።
የብልት ኣለመቆምን እንዴት መከላከል ይቻላል
ጤናማ ምግብ መመገብ።
ኮሌስትሮልን መቀነስ። በአመጋገብ፣ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና በመድሃኒት አማካኝነት ኮሌስትሮልን ዝቅ ማድረግ ይችላሉ።
ጤናማ ክብደትን መጠብቅ።
አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት።
ለስንፈተ ወሲብ ተብሎ በየቦታ የሚሸጥ መድሃኒት አለመጠቀም።
ከሴት ጓደኛ ጋር በግልጽ ማውራት።
ሕክምና
ብዙ የሕክምና አማራጮች አሉ።
በስነ-ልቦና ወይም በመድሃኒት ሊታከም ይችላል። ሐኪምዎን ያማክሩ። እራስዎ መድሃኒት አይግዙ።
References
American Psychiatric Association.(2013). Diagnostic and statistical manual of mental disorders (5th ed.).
@AllPharmacist
193 views08:04