Get Mystery Box with random crypto!

የነዳጅ ዋጋ ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ም | All Pharma

የነዳጅ ዋጋ

ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጭማሬ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታና የትርፍ ህዳግ አሰራር እና የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም ውሳኔ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራ ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በዚህ መሰረት÷

ቤንዚን 47. 83 በሊትር
ነጭ ናፍጣ 49.02 በሊትር
ኬሮሲን 49.02 በሊትር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ 53.10 በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ 52.37 በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ 98.83 በሊትር መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከላይ የተገለጸው የቤንዚን፣ የኬሮሲንና የነጭ ዋጋ ላይ ለህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ወይም የታለመ ድጎማ ተጠቃሚ ተሸከርካሪዎች 15 በመቶ በመንግስት እንዲደጎሙና ቀሪውን 10 በመቶ እንዲከፍሉ በማድረግ የድጎማ መጠኑን በቴሌ ብር ተመላሽ እንዲሆንላቸው ይደረጋል ተብሏል።

የተደረገው የዋጋ ማስተካከያ የተደረገባቸው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዝርዝር ከነገው /ሰኔ 29/2014 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ማደያዎች ሁሉ ተግባራዊ እንደሚሆን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

@tikvahethiopia