Get Mystery Box with random crypto!

ነገረ ካካ (አሌክስ አብርሃም) ይች ምስሏን ከታች የምትመለከቷት ቆንጆ ሴት ጆኒ ዲፕ የተባለ | Alex Abreham በነገራችን - ላይ

ነገረ ካካ
(አሌክስ አብርሃም)

ይች ምስሏን ከታች የምትመለከቷት ቆንጆ ሴት ጆኒ ዲፕ የተባለ ታዋቂ የፊልም ተዋናይ የቀድሞ ባሏ ጋር ተካሳ ችሎት ስትመላለስ ነበር! (ያው ነገሩን ታውቃላችሁ) ታዲያ የጓዳ ገመናቸውን እያወጡ ሲጠዛጠዙ ሚስኪን ባሏ ምን አለ? "ከሁሉም ከሁሉም የሚያሳዝነው ሆነ ብላ ለሞላ ሽንት ቤት ...አልጋየ ላይ... እኔ በምተኛበት በኩል ካካ ብላ እንደደህና ነገር ካካዋን አንሶላ ለበስ አድርጋ አሰቀምጣልኝ ታውቃለች" አለ! ዓለም በሙሉ ይሄን ሲሰማ አፍንጫውን ይዞ "ምኗ ካካም ናት ...ይድፋሽ እቴ" አለ! በኋላ እሷ "አይ ውሻችን ነው ካካ ያለበት እኔ አይደለሁም " ብላ ካደች! ...ጆኒ ዲፕ ታዲያ በስልኩ ያነሳውን የካካ ፎቶ(ምን ሲሆን ፎቶ አነሳው እስቲ?) መዝረጥ አድርጎ "አሁን ማን ይሙት ይሄ ካካ ምኑ ነው የውሻ የሚመስለው ወገኖቸ? የራሷ ነው! " አለ ! የጆኒ አድናቂዎች በሙሉ "ይሄማ የራሷ ነው ቁርጥ እናቱን" አሉ! በአጭሩ የዚች አገር ባለስልጣናት ምንም ቢሽቀረቀሩና ወሬ ቢያሳምሩ ወደፊት ለህግ ሲቀርቡ ክሳቸው ከዚህም የሚያስፀይፍ ይመስለኛል "አገር ላይ በመፀዳዳት" የኛ አይደለም ቢሉም ቆሻሻ ስራቸውን እየደበረውም ቢሆን ፎቶ አንስቷል ህዝቡ!