Get Mystery Box with random crypto!

የትኛው ይሻለኛል…? (ምን መሰለኅ እኔ ዲፓርትመንት ልመርጥ ነው ከ ……... እና ከ | የሕይወት ምክር (PSYCHOLOGY)

የትኛው ይሻለኛል…?

(ምን መሰለኅ እኔ ዲፓርትመንት ልመርጥ ነው ከ ……... እና ከ ……. የትኛው ይሻለኛል ? ተምሬ ስወጣ ሥራ ላገኝበት የምችልበትን ነው የምፈልገው እባክኅ እርዳኝ የምትፈልጊውን ምረጥ እንዳትለኝ ምክንያቱም እኔ ሥራ ማገኝበትን ብቻ ነው የምፈልገው፡፡) ከቻናሌ አባል የተጠየቀ

ይህን ጥያቄ ከብዙ ሰው ሰማሁት በይበልጥ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ለከፍተኛ ትምህርት የታጩ የነገ ሀገር ተረካቢዎች ጭንቀት ነው በጣም ተቸግረው አይቻለው ይህ በኔ እይታ በግልም እንደ ቤተሰብም እንደ ሀገርም ትልቅ ኪሳራ ነው ፡፡ ለምን?

አንድ ተማሪ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ምን መሆን እንዳለበት ሳያውቅ ከተማረ እመኑኝ ቀሪ ዘመኖቹ በዚው ጉዳይ ዋጋ እየከፈለ እየተወዛገበ እንዲሔድ ያደርገዋል ወዴት መሄድ እንደምትፈልግ ሳታውቅ እንዴት ጉዞ ትጀምራለህ ይህ የጨለማ ጉዞ ምናልባትም መጨረሻው የከፋ ሊሆን ይችላል? አስታውሳለው የዲግሪ 1ኛ ዓመት ተማሪ ሆኜ እኔ ማነኝ ? ምን መሆን ነው የምፈልገው? ወዴት መሄድ ነው የምፈልገው..? እያልኩ መሐል መንገድ ቁጭ ብዬ በኃሳብ ጦርነት የተሰቃየሁበትን ቀን በፍፁም አልረሳውም ለኔ ይሄ በጣም ከባድና አስጨናቂ የውስጥ ጥያቄ ነበር በዚህ ጉዳይ እንደተሰቃየሁት የተሰቃየሁበት ኃሳብ ያለ አይመስለኝም ከድቅድቅ ጨለማ የመውጣት ያህል ለነፍሴ በጣም አስጨናቂ ነበር ለሁሉም እንደተሰጠው ለራሴም ለሰው ልጆችም አንድ የምጠቅምበት ነገር እንደተሰጠኝ እረዳለው ግን እንዴት ላግኘው? ለሕይወት አስፈላጊ ጥያቄ ግን ደግሞ መልስ ለመስጠት አንገትን የሚተናነቅ የበዛ ኃሳብ የሚያከናንብ ከባድ ጥያቄ ..፡

ብዙ ሰው ይሕን ጥያቄ ለመመለስ ይፈራል ለምን?
1. የሚወደውን ነገር እንዳያገኝ ሰይጣን ይሸፍንበታል ምክንያቱም ያን አገኘ ማለት የተፈጠረበትን የሚሞትበትንም ጸጋውን ሙያውን አገኘው ማለት ነው
2. መስዋዕትነት እንደሚከፈልበት ስለሚያውቀው ይህን ለመክፈል ዝግጁ የሆነ ማንነት ካልፈጠረ ይፈራል
3. የሰዎችን ኃሳብ እየሰማ ግራ መጋባት ውስጥ ይገባል እናቱን አባቱን ቤተሰቡን ጓደኞቹን መምሕራኖቹን ለማስደሰት በማሰብ የምርጫ መደበላለቅ ውስጥ ይገባል
4. ገንዘብ ባላገኝበትስ..? በማለት ገንዘብን የሕይወቱ ምሰሶ በማድረጉ ነገሮች ይቃወሱበታል
5. እና…እናንተ በምታውቋቸው መሰል ምክንያች ይፈራል

አንድ ትልቅ ነጥብ የምንስተው ተሰጥኦ ወይም ጸጋ የምንለውን ጉዳይ የተፈጥሮ እውቀት እንደሆነና ለእያንዳንዳችን ይሕ እንደተሰጠን መዘንጋታችን ነው፡፡ ትምህርት ቤት ገብተን የምናገኘው እውቀት በተፈጥሮ ለተሰጠን ተሰጥኦ የሚያጠናክር የሚያግዝ እንጂ በራሱ ሙሉ እውቀት አይደለም፡፡

ይህ ምን ማለት ነው ?

ምሳሌ ስኬታማ ሰዓሊ ወይም ደራሲ ወይም……ለመሆን የሚፈልግ ሰው በቅድሚያ ማየት ያለበት ፍላጎቱን እና ተሰጥኦውን ነው ወይስ ገንዘብ አገኝበታለሁ ወይም ሰዎችን አስደስትበታለሁ የሚለውን ? የቱን ነው ማየት ያለበት ?ስኬታማ ሰዐሊም ሆነ ደራሲ ትምህርት ቤት ገብተህ ስለተማርኅ አትሆንም ትመስላቸው ይሆናል እንጂ ለሌላውም መስክ እንዲሁ ነው ፡፡

ባለህ ተሰጥኦ ላይ ስትማርበት ስታነብበት ስትመራመርበት ያኔ አንተ የሕይወትን ቁልፍ አገኘህ ማለት ነው የስኬታማ ሰዎች መነሻም መድረሻም ይህ ነጥብ ነው፡፡
እንደ ሀገር ተምረን መኪና ጠገንን እንጂ መኪና አልሠራንም ተምረን ስልክ እንጠግናለን እንጂ ስልክ አልፈጠርንም ለምን ?

ሁለት ነገር ይታየኛል እንደ ሀገር ትምህርት ቤቶቻችን መርኃችንም በተፈጥሮ ለታደልነው ጥበብ ትኩረት የማይሰጥና ሀገር በቀል እውቀትን ባለማሳደጋችን ነው

ራስህንም ሀገርህንም ለመለወጥ ዋናው ጉዳይ ከአምላክህ ምን ተቀበልኅ አንተስ ምን ብትሠራ ደስ ይልሃል? ምን የመሥራት ፍቅር አለህ? የሚለውን መመለስ ነው ::


ገንዘብ መሰብሰብ የሕይወትህ መስመር አስማሪ (ትልቅ ሕልምህ) መሆን በፍጹም የለበትም ገንዘብ በየትኛውም መስክ ብትሠማራ ተርፎ ሊትረፈረፍ ወይም ደግሞ እጅህ ላይ አልገባ እያለ ሊያሰቃይህ ይችላል

እንግዲያውስ ገንዘብ የመሰብሰብ ራዕይ ወይም ሕልም አይኑርህ እርሱ አንተ ውስጥ ያለውን ጸጋ በጥንካሬ እና በትጋት እንዴት እንደምትሸጠው የማወቅ እና ለመትደክመው ድካም የሚሰጥ በረከት ብቻ ነው የትኛውም ፊልድ በራሱ ገንዘብ የማምጣት የማስቀረትም አቅም የለውም ለምን?፡

የትኛውም ነገር ውስጥ ብትገባ ኃሳብህን ወይም እውቀትህን ወይም እቃህን እንዴት እንደምትሸጠው ካላወቅኽ በምንም ተአምር ገንዘብ አንተ ጋር አይሰበሰብም ይሁንና ቢመጣም አያድግም ቢያድግም ያለ ማቋረጥ አያድግም ተመልሶ ይጠፋል ሀብታም መሆንህ ደሀ ላለመሆን ዋስትና አይሆንህም ዋስትና የሚሆንህ እውቀትህ ፍላጎትህ ትጋትህና የፈጠርከው የግንኙነት መረብ ነው መዋኀድ ነው፡፡

ከተረዳኸኝ ገንዘብ ማግኘት አንድን ነገር እንዴት እንደምትሸጠው እና ትርፍ እንዴት እንደምታገኝበት የማወቅ ዱዳይ ነው እንጂ ነጋዴ ወይም ተቀጣሪ አካውንታትን ወይም ዶክተር የመሆን ጉዳይ አይደለም ሕልምህ ግን የተፈጠርክበት እና የምትሞትለት ጉዳይ ነው፡፡

እና ምን ላድረግ ?
እነዚህ ጥያቄዎች እራስህን ጠይቅ ደጋግመህ እየጻፍክ ፈልጋቸው
1. እኔ ማን ነኝ ?(ምንድነው ዝናባሌዬ ምን ላይ ሥሠራ ደስተኛ ነኝ ? ምን ምን ላይ ብሠራ ለሰዎች አንድ ነገር አበረክታለሁ….?)
2. እንደ ማን ነው መሆን የምፈልገው? (የምትወደውን ሰው አርአያ የምታደርገውን ሰው ባህርያት ጻፋቸው እና አንብባቸው ታዲያ የሠውየው የምትወዳቸው ባህርያት የአንተው እንደሆኑ በእርግጠኝነት ልነግርህ እወዳለው)
3. የት መድረስ ነው የምትፈልገው ?(በየትኛው የስኬት ማማ ላይ ራስህን ከወዲሁ ታየዋለህ..?)
ስለዚህ አንተ የተፈጠርኅበትን እውነተኛ ጉዳይ (ሕልምህን) ለይ አዎ ይህን ስልህ ብዙ ተቃዋሚ ሊኖርብህ ይችላል ብዙ ሰው ሊያጣጥልብህ ይችላል ልትሠማራ ያሰብኅበትን ጉዳይ ሊያናንቅብህ ይችላል ይህ ያንተ ጉዳይ መሆን የለበትም የአንተን ሕይወት የምትወስነው ራስህ ነህ በቅድሚያ ግን መወሰን የምትችልበት ቁመና ላይ መሆንህን አረጋግጥ፡፡


ሲጠቃለል መቼም እየሔድን አይደለም የት መሄድ እንዳለብን የምንወስነው ወስነን ነው ጉዞ የምንጀምረው አንተም እንዲሁ አድርግ ከልብህ የምትወደውን የምትፈልገውን ሁን እርሱም ላይ ከልብህ ሥራ ኃሳብህን እና እውቀትህን ወይም ፈጠራኅን እንዴት ወደ ገንዘብ እንደምትቀይረው ተማር ሁሌም ለሰው ልጆች እንዴት አዲስ ነገር ለመፍጠር እንደምትችል ተመራመር


እንደዚህ ሲሆን አንተ የትም መሔድ አይጠበቅብህም ሰው ራሱ ያለህበት ድረስ ፈልጎህ አፈላልጎህ ይመጣል የትኛው ይሻለኛል ካልኸኝ የተፈጠርኅበትን ጉዳይ ለይ በርሱ ላይ ተማር ተመራመር ፣ ሥራ ፣ ሽጥ ፣ለውጥ…አለቀ ያኔ ካንተ በላይ ስኬታማ አይኖርም ፡፡
መልካም የምርጫ ጊዜ
https://t.me/alazarsayehiwotmiker
ጥያቄና አስተያየት ለመስጠት https://t.me/Josi0921


አልዓዛር