Get Mystery Box with random crypto!

ይድረስ ለአህለል ሱና ወልጀምዐው! == ✿❀ === ✿❀ === ✿❀ == * ይድረስ ለነጃሺ፣ ለጦልሃ | Μ@ አል_ሪጃሉላህ_የሐድራ_ጀመአ

ይድረስ ለአህለል ሱና ወልጀምዐው!
== ✿❀ === ✿❀ === ✿❀ ==
*
ይድረስ ለነጃሺ፣ ለጦልሃ ጃዕፈር ፣ ለሸህ ኑር ሁሴን ፣ ለከቢር ሃሺም፣ ለእስማኢል ጀበርቲ፣ ለአህመደ ቲጃኒይ፣ ለሸህ አባድር፣ ለሰይድ ቡሽራ (ገትይ)፣ ለሸህ አሊ ጎንደር ፣ ለጌታው ሸረፈዲን፣ ለፈቂህ ዙበይር፣ ለአህመድ ኢብኑሷሊህ፣ ለንጉስ ሙጃሂዱ፣ ለጌታው ሰይድ ፣ለጀማሉል አኒይ ፣ ለሸሃቡ ዳኒይ፣ ለሸህ ጫሊይ ፣ ለሸህ ሾንኬ ፣ ለዳንግላው ሸህ ፣ ለገረውዬች ፣ለአብሬትዬች፣ ለቃጠባርዬች፣ ለአልከስዬች፣ ለዘቢ ሞላዎች ... በአጠቃላይ ለመሻኢህ ወዳጆች እና ሙሪዶች ...
*
ያ ጀምዐ ... ቀደምት መሻኢሆቻችን ከአሽረፈል ኸልቅ ﷺ ተቀብለው በቅብብሎሽ ያልተበረዘውን የአህለል ሱና ወልጀምዐ መስመር በአጥንታቸውና በደማቸው ጠብቀው ለእኛ አቀብለውናል ... ይህንን አማና ለእኛ ያቀበሉበትን የትግል ታሪክ መልሰህ የምታስታውስበት ፣ በአፅንዖት የምታስተነትንበት እና በፅሞና የምታስተውልበት ወሳኝ ወቅት ላይ ትገኛለህ ... ቀደምት አባቶቻችን እና መሻኢሆቻችን የተለያዩ መከራዎች እና ግፎች ሳይበግሯቸው ተስፋቸውን እና መመካታቸውን በአላህ ሱብሃነሁ ወተአላ ላይ አድርገው በፅናት፣ በጀግንነት፣ በአደብ፣ በኢህላስ እና በሒማ ታግለው ለእኛ ያደረሱልንን አማና እንደምን በስንፍና ፣ በቸልተኝነት ፣ በዝንጋቴ እና በፍርሃት አሳልፈን እንሰጣለን...
*
"እውነት" ሳንፍረከረክ እና ሳናፈገፍግ በልበ ሙሉነት የምንቆምለት ነገር ነው ... በ1966 ዓ.ም ሀገራዊ ለዉጡን ተከትሎ ለምዕተ አመታት ሲወርድ ሲወራረድ የነበረዉን የኢትዮጵያ መሻኢኮችን አደራ ተቀብሎ የሃይማኖቱን ቅብብሎሽ ለማዘመንና ለማሳለጥ ያለሙ የአህለል ሱና ወልጀምዐ የኃይማኖት አባቶች ባደረጉት ጥረት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ጉባኤ መጅሊስን መመስረታቸው እና ምስረታውን በመውሊድ እለት ይፋ ማድረጋቸው የማይካድ ሀቅ ነው...
*
ይሄ የአህለል ሱና ወልጀምዕ መጅሊስም ... ከሶስት ዓመት በፊት በስመ አንድነት በተጀመረ ቁማር ፣ በሸፍጥ፣ በአሰልቺ ድራማ እና በስተመጨረሻ በመንግሥት ድጋፍ በአፈሙዝ ከባለቤቶቹ መነጠቁም ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ሀቅ ነው... እና የአቂዳ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ይህንን ተቋማችንን ... ተውሒዱ ለተበላሸ፣ አላህን በቦታና በአቅጣጫ ገድቦና አቅልሎ በፍጡርኛ ለሚገልፅ፣ ስለ አላህ ያለው እሳቤ ከጣዖታዊ እሳቤ ላልተላቀቀ ቡድን ትተን እንዴት በስንፍና ፣ በቸልተኝነት ፣ በዝንጋቴ እና በፍርሃት እንቀመጣለን...
*
ላለፉት ሶስት አመታት አታካች በሆኑ መተጋገል ውስጥ ብናልፍም ... ትግላችን ግን አሁን ገና ነው የሚጀምረው... መንግሥት አቅም እንዳጣ ታማሚ ብብት እና ብብቱን ደግፎ ይዞ መጅሊሱ ውስጥ የዶለው ልዝብ ሸያጢን በአፉ ስለ ሐሳዊ "አንድነት" ቢያወራም ያለፈው ታሪኩ በተጨባጭ የሚያሳያው ግን ተቃራኒውን ነው ...
*
የዛሬ 260 አመት ገደማ ዛሬ ሳውዲ ብለን በምንጠራት ሀገር ሪያድ አካባቢ የተነሳው ሙሀመድ ኢብኑ ዐብዱል ወሃብ በጀመረው የወሃ^ቢያ ንቅናቄ “እስልምናን” አንደ መፈክር ቢጠቀምበትም በመካ፣ በመዲና፣ በድፍን ሳውዲና በአጎራባች ሀገራት፣ በሶሪያ፣ በየመንና በዒራቅ ሙስሊሞች ላይ ለመስማት የሚዘገንን ሰቅጣጭ ጭፍ^ጨፋን አካሄዷል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ዑለሞችና ሙስሊሞች መካንና መዲናን ጨምሮ በተጠቀሱት ሀገራት ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ታርደ^ዋል፡፡ መስጂድ ውስጥ ቁርአን እየቀሩና እየሰገዱ የነበሩ፤ ሰላት ላይና ቁርአን ላይ ሳሉ ‹‹ሙሽ^ሪኮች ናቸው›› በሚል ፍረጃ የታረ^ዱ በሺ ሚቆጠሩ ሙስሊሞችና ዓሊሞች አልፈዋል፡፡ ጡት ያልጣለ ህፃን ልጅ በእናቱ እቅፍ ላይ እንዳለ ከእናቱ ጋር ተዘል^ዝሏል... ይህ እንግዲህ በወቅቱ የተረፉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዑለሞች በኪታቦቻቸው ላይ ያሰፈሩት ዕውነታ ብቻ ሳይሆን በሙሀመድ ኢብኑ ዐብዱልወሃብ በህይወት ዘመን የግል ታሪክ ፀሐፊዎቹ የነበሩ ባልደረቦቹ ጭምር ይህን ጭፍ^ጨፋ በሀፍረት ሳይሆን በኩራት ፅፈውታል...
*
እናም ወዳጄ ወሃ^ቢያ በብልሹ አቂዳው ልጆቻችን እና ቤተሰባችንን ሳያጠምቅ ... ሐሪማዎቻችንና መሳጂዶቻችን በነጅዳዊ ሃረካቱ ሳይበክል የሚቆም አን'ጃ አይደለምናን ... በስንፍና ፣ በቸልተኝነት ፣ በዝንጋቴ እና በፍርሃት ተይዘን የዲን አማናችንን አንብላ ... ትግላችን ገና አሁን እየጀመረ ነውና ቀበቷችንን ፣ ያሲናችንን እና ዱዐችን እናጥብቅ!
*