Get Mystery Box with random crypto!

አህሉል ሀዲስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ akidatliislamya — አህሉል ሀዲስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ akidatliislamya — አህሉል ሀዲስ
የሰርጥ አድራሻ: @akidatliislamya
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 391
የሰርጥ መግለጫ

ተውሂድ ሊቀደም ግድ ነው
ወገንተኝነት በኢስላም የለም
ለጥቆማ እና አስተያየት @Onlyhumanty
የመረጃ ክፍተት እንዳይኖር እንሰራለን ።
ሀቅ በሀቅነቱ ብቸ ይወራል ይዳሰሳል ።
በኢስላም እና በሙስሊሞች ላይ የሚሰሩ ሴራዎች ይጋለጡበታል ።
ከ አላህ ዉጭ በእዉነት የሚመለክ አምላክ የለም።
በትክክለኛዉ አንድነታችን ስለ ሁለንተናችን ።
Share በማድረግ እና እራሶት በመጠቀም በዱዐ ይገዙን ።

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-21 07:58:24 # Stop Dismemberment of wollo#
በዚህ ሰዓት የሚደረግ ወሎን የመከፋፈልና የማዳከም ስትራቴጅ ለማንም ለምንም አይጠቅምም የወሎን ታሪክና ማንነት ለማጥፋት የተደቀነ አደጋ ነው። ለወሎ ካሰቡ ዛሬ ዞን እንስጥህ ብሎ ራስጠይቆ ከመምጣጥ ይልቅ በህዋህት ወራሪ ሀይል የደረሰበትን ጉዳት መልሰን እንዴት እንጠግነው ነበር መባል ያለበት ዛሬ ገበሬው ቤቱ ተቃጥሎ በዚህ ክረምት መጠጊያ (መጠለያ) አጥቶ በዳስ ውስጥ ባለበት ጊዜና በሬው ታርዶ ተበልቶበት መሬቱን ማረሻ በሬ አጥቶ ፆም ባደረበት ሰዓት የሚቀድመው ለገበሬ በሬ ገዝቶ መስጠትና መጠለያ ቤቱን መስራት ነው የሚያስጨንቀው ወይንስ ዞን መስጠት?? ተሰጠን ብላችሁ የምትደሰቱም ለምን ለኛ አልተሰጠም ብላችሁ የምትበሳጩም ቆም ብላችሁ አስቡበት። የተያዘው ወሎ የኢትዮጲያ ተምሳሌት የሆነ ማንነት እና እሴት ያለውን ህዝብ ከፋፍሎ ማንነቱን ና እሴቱን አጥፍቶ ወሎ ታሪክ ብቻ ሁኖ እንድቀር ነው እየተሰራ ያለው። ከታሪካዊ ስህተት እንቆጠብ
https://t.me/Akidatliislamya
https://t.me/Akidatliislamya
18 views04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 21:59:22 አባቴ ተሠቅሎ ወንድሜ ተቃጥሎ
እህቴ ታግታ እናቴ ተቀልታ
አያቴ ተሠዶ ሕፃን ልጄ ታርዶ
አሞኛል፣ አሞኛል ወገን ሞቶብኛል
ሠው ተገሎብኛል

https://t.me/Akidatliislamya
https://t.me/Akidatliislamya
26 views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 17:14:37 አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሉሙጥ ባንድራ! ።
ሀገራችንን ከሚያዉኩ ፅንፈኞች መካከል ሉሙጥ ባድራ ይዘዉ የሚንቀሳቀሱ አብ ወልድ መንፈስ ቁዱስን ይወከላል ብለዉ የሚለፍፉ የአፄ አቀንቃኞች እንዲሁም የአፄ የመንፈስ ልጆች አሀዳዊ እሳቤ ነዉ።
ይህ የአንባ ገነኖች ባንድራ በየትኛዉም መንገድ ሀገራችን ላይ መዉለብለብ አይችልም።
ሉሙታዉያን እና የሀገራችን ጨቁኝ እንዲሁም አግላይ አሀዳዉያንን መታገል አለብን።
በኢፋ ዛሬም አዉርደን ጥለነዋል ።

አብዱልመጂድ መለሰ
29 views14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 15:57:55 መጅሊሱ በአዋጅ ሲቋቋም እና ህጋዊ ሰውነቱን ሲያገኝ ከተሰጠው መብቶች ውስጥ አንዱ የመክሰስ እና መከሰስ መብት አንዱ ነው::

ዛሬ ላይ በመጅሊሱ የውስጥ ስራ ጣልቃ እየገቡ የሚበጠብጡ የህዝበ ሙስሊሙን ሰላም የሚያውኩ እና እያወኩ ያሉ ዱርየዎችን ስርአት ማስያዝ የተገባ ነው::

በመጅሊሱ አሰራር እጃቸው በመላክ የተከበሩ ኡለሞችን ስም በማጥፋት

ኢትዬ360 እና ጋዜጠኞች
የኔታቱዮብ እና ጋዜጠኞች
ዲ/ን አባይነህ ካሴ
ዲ/ን ዘመድኩም በቀለ

ህዝበ ሙስሊሙን በማወክ እና በማሰገደል
የጎንደር ከተማ ከንቲባ
የጎንድር ከተማ ፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ
ዲ/ን ዮርዳኖስ
ዲ/ን አባይንእህ ካሴ
ዲ/ንዘመድኩን በቀለ
አባ ዮሴፍ ሌሎችን ጨምሩበት
ባስቸኳይ ሊከሰሱ ይገባል ::

ይህ ሲሆን ማንም እየተነሳ በኢስላም እና ሙስሊሞች ላይ አፍ መክፈቱን ያቆማል
67 views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 11:27:26 ➽#የሚጠላን_መውደድ_!!
◄--------------------------------->
ከተራራ በላይ ክብደቱ ይገዝፋል፡
ከሰማይ ትልቅ ነው እጂጉን ይሰፋል፡
ጉልበቱ ምጡቅ ነው ማዕበል ያቆማል፡
ጥርስን እያሳቀ አዕምሮን ያደማል፡
ሰው ወዶ መለየት እጂግ በጣም ያማል፡
<~~>
መቃጠል ነው ትርፉ እንጨት ሆኖ መንደድ፡
እንደማይሆን አውቆ የሚጠላን መውደድ፡
ጉዞው አሰልች ነው ያደክማል መንገዱ፡
የራስ የማይሆን ሰው ወዶ ማሳደዱ ..፡
<~>
ሞራል ይፈትናል ውስጥን ረብሾ፡
ባይኖረውም መጠጥ አረቂና ጌሾ፡
ከልብ ማሳ ላይ ያስቀምጣል ቁርሾ፡
የሚጠላን መውደድ አዕምሮን ያውራል፡
ለመልካም ሰላምታ መጥፎ ያናግራል፡
የሚጠላን መውደድ ሲያስቡት ይደንቃል፡
ጠላት ስትከተል ከወዳጅ ያርቃል፡
ኪሳራው ብዙ ነው ያለካም በቃል፡
<----------------------------------------->
የሚጠላን መውደድ ያተርፋል ጠባሳ፡
ለዳማ ነው ትርፉ በዕንባ አይወጣም ባሳ፡
የሚጠላን መውደድ ከባድ ነው አደጋው፡
ኑሮን ያቃውሳል ክረምቱን ከበጋው፡
ያቀላቅለዋል ቆላውን ከደጋው፡
የሚጠላን መውደድ ክብርን ያራክሳል፡
ግዙፉን አሟምቶ ወፍራሙን ያከሳል፡
◄----------------------------------------->
ክብር እየሰጠን እኛን ለሚጠላን፡
አለን ዛሬ ድረስ መከራ እየበላን፡
ጠላት እየወደድን ወዳጅን በመተው፡
አለን ዛሬ ድረስ ህይወትን ስንዘምተው፡
የተቃርኖ ጉዞ መንገዱ ባያልቅም፡
የየብቻ አላማ ፍፃሜው ባይደንቅም፡
የፍቅርን ደረጃ ክብሩን ባናልቅም፡
ጀርባ ተሰጣጥተን ኑሯችን ባይደምቅም፡
አልቅሰን ባናውቅም ስቀን ግን አናውቅም፡
<-------------------------------------------------->
በማይግባባ እቅድ ለየቅል ተጋምደን፡
ጋራ ሸንተረሩን ለብቻ ተሰደን፡
ሁላችንም ሌላ የሩቅ ወዳጅ ለምደን፡
ለቀረበን የዋህ በርሱ ላይ ግፍ ፈርደን፡
አለን በህፀፅ ውስጥ የጠላንን ወደን፡
<------------------------------------------------->
ጠላት ከጀርባ እንጅ ከጀርመን ባይመጣም፡
የሚጠላን መውደድ ፈፅሞ አያዋጣም፡
ለወዳጅ ቦታ ስጥ አስተውል ተመለስ፡
ጠላት አትከተል ወደ ወዳጅ ፍለስ፡
በማያውቁት ሐገር በጫካ መሰደድ፡
ሁሌ እየከሰሉ እየሳቁ መንደድ፡
ፍፃሜው ከንቱ ነው የሚጠላን መውደድ፡
<-------------------------------------------->
#ኑረዲን_አል_አረቢ
<-------------------------------------------->
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
<~~~>
39 views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 10:45:31 ውልድና እድገታችን ወሎ ነው። ማንነታችን ወሎየነት!
ወሎን የሚያውቅ ይፍረደን! የወሎን ሰው ረህማ የሚያውቅ ይፍረደን!

ወሎ እንግዳን አርሂብ ማለቱ ብቻ አይደለም ከፍታው። የንግዳውን ብቻ አይደለም አሸናፊም ተሸናፊም ሆኖ የመጣውን ሁሉ ተቀባይ ነው። የጠላቱን ባህልና ወግ እንኳ ተቀብሎ ራህመት ያክልበታል፣ ወዝ ይቀባዋል።

ለዚህም ነዉ Yates የተባለው ተመራማሪ considered Wollo as a 'sponge' Which takes in all the cultural practices of the areas. ወሎ ሰው አክባሪው፣ ወሎ ውለኛው የነሱ ብሎ መጠየፍን የማያውቀው ወገኔን የሚያውቅ ይፍረደን!!

ኢትዮጰያ ስትሰለጥን ወሎን ትሆናለች! የምንለው እንዲሁ ነውን? ስለ ወሎ የተመራመሩ የፃፉ፣ በወሎ የተገረሙ ሁሉ የወሎ መዋሀድና የተፈጠረው መስተጋብር እጅጉን አስደንቋቸዋል።

Brian J. Yates ነገረ ወሎ ቢገርመው ያለውን አላወቁምና አውፍ ብለናቸዋል። ያቴስ ይህን ብሏል፦
"Wollo is an Amhara, Oromo, Muslim and Christian altogether ...while Ethiopia is diversity in diversity, Wollo is diversity in Unity."

ኢትዮጵያ የብዙሃን አገር ብትሆንም ልዩነቶቹ መታረቅና መዋሀድ ላይ ገና አልደረሰችም። ወሎ ግን ይህን አልፋዋለች! ለዚያ ነው ያቴስ ይህን በጥናቱ የመሰከረው።

አብዱጀሊል
46 views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 07:52:47 የፖለቲካ ንግድ አትራፊው ቀጠና
★★★//★//★★★

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቆለኛው አርብቶ አደሩ ህዝብና በደገኛው አርሶ አደሩ የወሎና የሰሜን ሽዋ ቀጠና ህዝቦች መካከል ታሪካዊ፣ዴሞግራፊያዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ልዩነቶች መኖራቸው ሀቅ ነው፡፡ ደገኛው አርሶ አደር (አግራሪያን)፣ ቀለም ቀመስ፣ በሃይማኖቱም ክርስቲያን በዝ፣ በባህሉ አማራ ኦርቶዶክስነት ሲሆን በአንጻራዊነት የተሻለ መሰረተ ልማት የተዘረጋለት ቀጠና ሲሆን ቆለኛው ደግሞ በዋናነት አርብቶ አደር፣ በሃይማኖቱም ሙስሊም በዝ፣ በቋንቋውና ባህሉ ኦሮሞ ኢስላማዊ ሲሆን በአማራ ክልል በዋና መሰረተ ልማቶች የተነፈገ (ማርጂናላይዝድ የተደረገ) አሳሳቢ የሰው ኃይል ስደት የተጋረጠበት ቀጠና ነው፡፡

በደገኛውና በቆለኛው መካከል በንግድ መስመር፣ በግጦሽ ሳር፣ በምንጭ ውሐ ወዘተ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ሳቢያ መጠነኛና ወቅታዊ ግጭቶች ለዘመናት ነበሩ፡፡ ምንም እንኳን በዋናነት ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን መሰረት ያደረገ አልፎ አልፎም ሃይማኖታዊ መልክ ያላቸው በርካታ ግጭቶች በየወቅቱ ቢነሱም ግጭቶቹ በቀጠናው ሽማግሌዎች እየተፈቱ ቆለኛውና ደገኛውም በኢኮኖሚ እየተታለዋወጡ በአንጻራዊነት ለዘመናት የቀጠለ የመጠቃቀም መኗኗር አላቸው፡፡

ዛሬ ምን ተፈጠረ?
ከሽዋ ሮቢት እስከ ባቲ ባለው ቀጠና በሁለት ዓመታት ውሥጥ እጅግ ዘግናኝ የሆኑ በመጠናቸውም ሆነ በአይነታቸው ከፍተኛና ፖለቲካዊ የሆኑ ግጭቶች ተፈጥረዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ በርካቶች ተገድለዋል፣ በርካቶች ቆስለዋል፣ በርካቶች ታስረዋል፣ ተንገላተዋል፣ ቀጠናውም የዘርና የሃይማኖት ፍጅትን አስተናግዷል፡፡ የግጭቶቹ መሰረታዊ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ተዋናዮች እነማን ናቸው?
ተዋናያኑ

1 በቀጠናው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስተዋለ ያለ አክራሪ ኦሮሞነት እና ጽንፈኛ ኦሮሞዎች

2 በቀጠናው ላይ የርስት ተስፋፊነት ፍላጎት ያላቸውና የቀጠናውን በልሙጥ አማረራነት መጠቅለል የሚፈልጉ የአማራ ኃይሎች

3 የክልሉ ፖለቲካና የኦሮሚያ ፖለቲካ

1 በቀጠናው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስተዋለ ያለ አክራሪ ኦሮሞነት እና ጽንፈኛ ኦሮሞዎች

ቀጠናው ሆነ ተብሎ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት መገለል የደረሰበት፣ የሰው ኃይሉም በአገሩ ሳይሆን የስደት ተስፈኛ የሆነበት፣ የከብትና የግመል ጭራ ተከትሎ የግጦሽ መሬትና ውሃ ፍለጋ የሚኳትን ህዝብ ያለበት፣ በቋንቋው ኦሮሞ በሃይማኖቱ ሙስሊም በዝ የሆነ ቀጠና ነው፡፡ የአማራ ክልል የፌደራሊዝምን መርህ ተግባራዊ ለማድረግ ቀድሞ አቋም የወሰደ ክልል በመሆኑ ምስጋና የተገባው ይሆናል፤ ግና የክልሉ የኦሮሞ ማህበረሰቦች፣ የአገው ማህበረሰቦች ይህንን ራስን በራስ የማስተዳደር እድል ያገኙት ከፍተኛ ዋጋ ከፍለው እንጅ እንዲሁ በስጦታም የተበረከተላቸው አይደለም፡፡

ይሁን እንጅ ራስን በራስ የማስተዳደሩ እድል ቢፈቀድም ዋናው ተግዳሮት ለዘመናት ከትምህርትና ከቢሮክራሲ የተገፋ ቀጠና ራሱን በራሱ በየትኛው የአመራር ልምዱና እውቀቱ ሊያስተዳድር ይችላል? የሚለው አስቸጋሪው አጣብቂኝ ነበር፡፡ ቀጠናው ራሱን በራሱ ሊያስተዳድሩለት የሚችሉ የተማሩና ልምዱ ያላቸው ልጆችን ማፍራት እንዳይችል ተደርጎ የተሰራ ወይም የተረሳ ቀጠና ነበርና ይህን ክፍተት ለመሙላት በወቅቱ የአማራ ክልል አመራሮች መፍትሔ ያሉትን አማራጭ ወስደዋል፡፡ ይህም ከኦሮሚያ ክልል ቢሮክራቶችን በማምጣት ቀጠናው እንዲደራጅና በራሱ ቋንቋ እንዲተዳደር የማድረግ አማራጭን ተከትለዋል፡፡

ይህ አማራጭ ለጊዜው መፍትሄ ቢሆንም ከኦሮሚያ ክልል ተመድበው ወደ ቀጠናው የመጡት ቢሮክራቶች የወቅቱን የብሄር ፖለቲካ ጡዘት፣ የነበረውን የክልሉን የክትትል ክፍተት ተጠቅመው ህዝቡን ከአማራው ክልል ህዝብ ስነ-ልቦና በተለይም የወሎውን ኦሮሞ ከወሎየነት ስነልቦና፣ የሽዋውን ኦሮሞ ከሸዌነት ስነ-ልቦና የመነጠል እና ከኦሮሚያ ክልል ጋር የማነፋፈቅ ሥራ በሰፊው መስራታቸው የማይካድ ሀቅ ነው፡፡ቀጠናው ከወለጋና ከአርሲ በመጡ ቢሮክራቶች ሲታመስ መኖሩም ያደባባይ ምስጢር ነው፡፡

እነዚህ በተውሶ ከሌላ ክልል የመጡ ቢሮክራቶች ከፈጸሟቸው ስህተቶች አንዱ ቀጠናው በልማት እንዳያድግ በሞግዚት እያስተዳደሩ፣ ለህዝቡ የሚጠቅመውን የመሰረተ ልማት በተለይም ተተኪ አመራር ለማምረት የትምህርት ስርጭትና ጥራት ላይ ስራ ከመስራት ይልቅ በምንቸገረኝነት ከአባይ ማዶ አመራሮች ጋር በተመሳሳይ መልኩ እኔ ምን አገባኝ አቋም በማራመድ ቀጠናው የመከራ መናኸሪያ እንዲኖረው አድርገዋል፡፡ በቀጠናው የተወለዱ አማርኛ ተናጋሪዎች በተወለዱበት ቀጠና ሥራ እንዳያገኙ አግላይ አካሄድን ተከትለዋል፡፡ የቀጠናው ኦሮምኛ ተናጋሪ ግና በቁቤ የማይጽፉ ኦሮሞዎች ጭምር የሥራ እድል እንዳያገኙ አድርገዋል፡፡

ወጣቶች በተወለዱበት ቀጠና ያጡትን ህይዎት በስደት ሊፈልጉ በአየር፣ በየብስም፣ በውሃም ተሰደው መላ አረቢያን አጥለቅልቀዋል፡፡ ተተኪ አመራር ማፍራት እንዳይቻል አድርገው ትውልድን ገድለዋል፡፡ የጫት ሱስ ተጠቂ የሆነ ቀጠናም ፈጥረዋል፡፡ ጎን ለጎን ግን ቁጥራቸው አናሳ ቢሆንም ወሎና ሽዋ እየኖረ የኦሮሚያ ክልል ፖለቲካ የሚናፍቀው ወሎ ተቀምጦ ወለጋን የተስፋዋ ምድር አድርጎ የሚያስብ ብኩን ወጣትም ፈጥረዋል፡፡

የተጠረነፉበትን የአማራ ክልል ፖለቲካ፣ ያካበቧቸውንና የተጎራበቷቸውን ህዝቦች ስነ-ልቦና፣ የኦሮሚያ ክልልን ፖለቲካ፣ በጂኦግራፊ የሚገኙበትን ቀጠና፣ የአገሪቱን ጠቅላላ የፖለቲካ እና አስተዳደራዊ ውርስ መረዳት በማይችሉ ትቂት ጽንፈኞች የሚቀነቀነው ፖለቲካ ለቀጠናው ይዞበት የሚመጣውን መዓት መገንዘብ አይችሉምና ለራሳቸውም ሆነ ለጠቅላላው የኦሮሞ ዞን ማህበረሰብ አደጋን ተጣርተው አምጥተዋል፡፡

2 በቀጠናው ላይ የርስት ተስፋፊነት ፍላጎት ያላቸውና የቀጠናውን በልሙጥ አማረራነት መጠቅለል የሚፈልጉ የአማራ ኃይሎች

እነዚህኞቹ በኦሮሞ ዞን የአማራዎች በኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ፣ አስተዳደራዊና ማህበራዊ መገለል ቁጭት ብቻ ያለባቸው አይደሉም፡፡ ይህን ቁጭት ሥርዓት ባለው መልኩ መፍታት ይቻል ነበርና! እነዚህኞቹ ቀጠናው የአማራ ርስት ነው፤ ኦሮሞዎቹ መጤዎች ናቸው የሚል ዘርዓ ያዕቆባዊ ትውፊት ያለባቸው፣ ቴዎድሮስን መሆን የሚሹ የኦሮሞ ጥላቻ ያሰከራቸው ከንቱዎችም ናቸው፡፡ በኦሮሚያ ክልል ፖለቲካ ብሶት የአማራ ክልል ኦሮሞዎችን መበቀል የሚሹ "ጓዱ ቢያሸንፈው ወደ ሚስቱ ሮጠዎች" ናቸው፡፡ ወሎየነትን ገድለው አማራነትን ብቸኛ አማራጭ በማድረግ የዘመናት የወሎ ኦሮሞዎችን አማራ ለማድረግ የሚጋጋጡ ወለፈንዲዎች ናቸው፡፡

የቀጠናው ኦሮሞዎችን ስደተኛ፣ ወራሪ፣ መጤ አድርገው የሚያስቡና ያባቶቻችንን ርስት ብለው የሚጮኹና አጋጣሚውን ሁሉ ተጠቅመው ቀጠናውን የደም መሬት የሚሹ ናቸው፡፡ በርካቶቹ ፋኖ ሆነው ወደ ልዩ ኃይል የገቡ አሊያም በልዩ ኃይል ሽፋን የሚሰርጉ ናቸው፤ በርካቶቹም የልዩ ኃይሉን ዱካ ተከትለው ክብሪትና ጋዝ ይዘው የኦሮሞ ገበሬን ቤት "እስላም ጋላ ሽርጥ ለባሽ" እያሉ የሚያነዱ ናቸው፡፡ በአመለካከትም ያ ቀጠናና ህዝቡ የአማራ ክልል ህዝብ ነው ብለው የማያምኑ፣ ህዝቡና ቀጠናው የጎደላቸውን ያስኮረፋቸውን ለይተው የሚያወጡበት እና የሚያክሙበትን ሞራል በዘራፍ የገደሉ ድኩማኖች ናቸው፡፡
28 views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 22:12:58 ለ ዘመነ ካሴ ንገሩት መጂሊሳችን ሁለት ሳይሆን አንድ ሆኖ ቀጥሏል! !።
እኛን ደም ለማፋሰስ ለሞከረ ሁሉ እንደማይሳካ ይወቀዉ።
31 views19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:58:04 የዛሬ ውሎ አጭር ቅኝት
==================
« የዛሬው ሀምሌ11/2014 "የኢትዩጵያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥ እና አንድነት 2ኛ ጉባኤ" ውሎ አጭር ጥንቅር

ፕሮግራሙ በሽ/ዐብዱልሐሚድ አሕመድ (ከጅማ) መድረክ መሪነት ከረፋዱ 4:30 ላይ ጀምሯል።

የታላቁ አንዋር መስጅድ ሸ/ጧሀ ሀሩን የሚከተሉትን የቁርአን አንቀፆች አንብበዋል:-

" لا يكلف الله نفسا إلا وسعها لها ما كسبت وعليها ما اكتسبت ربنا لا تؤاخذنا إن نسينا أو أخطأنا ربنا ولا تحمل علينا إصرا كما حملته على الذين من قبلنا ربنا ولا تحملنا ما لا طاقة لنا به واعف عنا واغفر لنا وارحمنا أنت مولانا فانصرنا على القوم الكافرين "

" الله الذي خلق سبع سموات ومن الأرض مثلهن يتنزل الأمر بينهن لتعلموا أن الله على كل شيء قدير وأن الله قد أحاط بكل شيء علما "

በመቀጠል ዶ/ር ጀይላን ኸድር እና ሸ/ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እንዲሁም ሸ/ዐብድልከሪም ሸ/በድረዲን በየተራ የጉባኤውን መርሃ ግብር አንደሚከተለው አስረድተዋል:-

1ኛ/የዶ/ር ጀይላን ኸድር መልዕክት:-
የሚከተሉትን አንቀፆች አስታውሰዋል
" واعتصموا بحبل الله جميعا.."
" إن الذين فرقوا دينهم وكانوا شيعا لست منهم في
شيء إنما أمرهم إلى الله ثم ينبئهم بما كانوا يفعلون "
" ዛሬ እዚህ የታደማችሁ ሚያዚያ 23/2011 ያስረከባችሁንን ስልጣን መሠረት አድርገን መንግሥታችን ባደረግልን ድጋፍም ጭምር ኢስላማዊ ባንክን ማቋቋም ችለናል፣ ሕዝበ ሙስሊሙን የሚመጥን መሀል መዲናዋ ላይ ሰፊ መሬትም ተቀብለናል..
ሆኖም ከዚህ በላይ ብዙ ስራዎችን መስራት ሲገባን የተመረጥነው ለ6 ወራት ሳይሆን እስከመጨረሻው አንድንቀጥል ነው በሚል ንትርክ እየተስተጎጎልን ለዛሬዋ እለት በቅተናል።
ዛሬ የተገኘነው ጉዳዩን ወደናንተው ለመመለስ ነው። ምክንያቱም የኢትዩጵያን ሙስሊም የምትወክሉት እናንተ እንጂ መስማማት ያልቻልነው እኛ ጥቂት ዑለሞች ስላልሆንን።"

2ኛ/የሸ/ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ መልዕክት:-
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አሕመድ በሰጡን ምክር መሠረት እሰከ ዛሬ ሀምሌ 11/2014 ድረስ ብቻ እኔና ሙፍቲ መጅሊሱን በጊዜያዉነት እየመራን ነበር ፣ የዛሬውም ፕሮግራም የዘገየው ሙፍቲን እየጠበቅን ስለነበር ነው።
እሳቸው ባለመገኘታቸው የእሳቸው ምክትል የነበሩት ዶ/ር ጀይላን ኸድር መድረክ ላይ እንዲመጡ ሆኗል።
የዛሬው አብይ አጀንዳችንም ለ3 ዓመታት መጅሊስን የሚመሩ አዲስ አባላትን መምረጥ ይሆናል።
ይህንን ለማድረግ በሚያስችል መጠን እስከ አሁኑ ሰዓት ከ 300 አባላት 250 በመገኛተችውና ምልአተ ጉባኤው በመሟላቱ ወደ ምርጫችን እናመራለን (እስከ ፕሮግራሙ ፍጻሜ ድረስ የጉባኤተኛው ቁጥር ወደ 261 ከፍ ማለቱን ልብ ይሏል) ።
ይሀንን የሚመሩ የአስመራጭ ኮሚቴ አባላትም ይኖሩናል።

3ኛ/የሸ/ዐብድልከሪም በድረዲን መልዕክት:-

ዛሬ እዚህ የተገኘነው አማናውን ለሚገባው አካል ለማስተላለፍና፣የሰላም አጋር መሆናችንን በተጨባጭ ለማስመስከር ነው።
ይህን የምናደርገው እንኳን ደም ይቅርና አንባም ሳይፈስ ነው።
የሰላም ጉዳይ የዑለሞች ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነው።
በሰላም ጉዳይ ከማንም ጋር አንደራደርም።
በመቀጠል የሚከተሉት አስመራጭ ኮሚቴ አባላት መድረኩን ተረክበዋል:-
1_ ሐጂ/ሙሐመድኑር ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ (የሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ ልጅ)
2_ ሐጂ/ ዐብዱልቃድር
3_ ኡ/ዐብዱልዐዚዝ ኢብራሂም
4_ አቶ/ባሕረዲን አወል
5_ ሐጂ/ኻልድ ሙሐመድ

በመቀጠልም አስመራጭ ኮሚቴው የምርጫ ሂደቱን አፈጻጸም እንደሚከተለው አብራርቷል:-

የሁሉም ክልል ተወካዩች በተሰጣቸውና እንደሚከተለው በተዘረዘረው ኮታ መሰረት የጠቅላላ ጉባኤ አባላት የሚሆኑ በድምሩ 30 የሚሆኑ ተወካዩቻቸውን ይመርጣሉ።
* ኦሮሚያ 5
* አማራ 3
* አ/አ 3
* ደቡብ 3
* ሶማሌ 3
* ዐፋር 3
* ድሬዳዋ 2
* ትግራይ 2
* ሀረሪ 1
* ቤኒሻንጉል 2
*ጋምቤላ 1
* ሲዳማ 1
* ደቡብ ምእራብ 1

የሚመረጡ አመራሮች መስፈርት:-
1_ ዕድሜው ከ30 በላይ የሆነ፤
2_ ኢትዩጵያዊ የሆነ፤
3_ በሚመረጥበት ክልል ነዋሪ የሆነ፤
4_ ሕዝበ ሙስሊሙን ለማገልገል ቅን ፍላጎት ያለው፤
5_ ለእምነቱ ተማኝ የሆነ ተቅዋ ያለው፤
6_ ለቦታው የሚመጥን ብቃትና ክህሎት ያለው፤
7_በመልካም ሥነ ምግባር የሚታወቅ፤
8_ የተላያዩ ማህበራዊ ተሳትፎዎችን ያደረገ፤
9_ መሠረታዊ የሃይማኖቱን መርሆች አክብሮ የሚተገብር፤
10_ የየትኛወም ፖለቲካ ፖርቲ አባል ያልሆነ።

በመቀጠል የእያንዳንዱ ክልል ተወካዩች የተለያዩ ቦታዎች ላይ በመሆን ከተጠቆሙት እጩዎች መካከል የሚከተሉትን የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በድምጽ ብልጫ መርጠዋል:-

ከኦሮሚያ
1_ሸ/ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ
2_ሸ/ዐብዱልሐሚድ አሕመድ
3_ ኡ/ጋሊ አባቦር
4_ ኡ/ዚያድ ዐሊ
5_ ሸ/ሙሐመድ ዐሊ ኸድር

ከአ/አበባ:-
1_ ሸ/ጧሀ ሀሩን
2_ ሸ/ኑረዲን ደሊል
3_ ሸ/ሐሚድ ሙሳ

ከአማራ:-
1_ ሸ/ኡድሪስ ደጋን
2_ ኡ/ዐብዱረሕማን ሱልጣን
3_ ሸ/ሙሐመድ ኢብራሂም

ከደቡብ:-
1_ ሸ/ዐብዱልከሪም ሸ/በድረዲን
2_ሸ/ሙሐመድ ሙስጠፋ
3_ ሸ/ዐብዱልሀዲ

ከሶማሌ:-
1_ሸ/ዐብዱልዐዚዝ ሸ/ዐብዱልወሌ
2_ሸ/አሕመድ ሙሐመድ
3_
ከድሬዳዋ:-
1_ሸ/አሚን ኢብሮ
2_ሸ/ሙሐመድ ዑመር

ከትግራይ:-
1_ ሸ/ዐብዱልመናን ማሕሙድ
2_ ኢንጂነር/አንዋር ሙስጠፋ

ከቤኒሻንጉል:-
1_ ሸ/ዐለሙዲን
2_ሸ/አልመርዲ

ከጋምቤላ:-
1_ ሸ/ዛኪር ኢብራሂም

ከዐፋር:-
1_ ዶ/ር ሙሐመድ ሑሴን
2_ ሸ/መሐመድ አሕመድ ያሲን
3_
ከሲዳማ:-
1_ሸ/ሙስጠፋ ናስር

ከደቡብ ምእራብ:-
1_ሸ/ሑሴን ሐሰን

ከሀረሪ:-
1/ሸ/ሙሐመድ አሚን ዐያሽ

በመቀጠል ከእነዚህ 30 የጠቅላላ ጉባኤ አዲስ አባላት 14 የስራ አስፈጻሚ አመራሮችን አንደሚከተለው መርጠዋል:-
1_ ሸ/ ሐጂ ኢብራሂም (ፕሬዚዳንት)
2_ ሸ/ ዐብዱልከሪም ሸ/በድረዲን (ተ/ም/ፕሬዚደንት )
3_ ሸ/ ዐብዱልዐዚዝ ዐብዱልወሌ (ም/ፕሬዚደንት)
4_ሸ/ ሐሚድ ሙሳ (ዋና ፀሃፊ)
5_ሸ/ ዐብዱልሐሚድ አሕመድ (አባል)
6_ሸ/ እድሪስ ዐሊ (አባል)
7_ ሸ/መሐመድ አሕመድ ያሲን (አባል)
8_ሐጂ/ሙስጠፋ ናስር (አባል)
9_ሸ/ አልመርዲ ዐብዱላሂ (አባል)
10_ ሸ/ ሑሴን ሐሰን (አባል)
11_ ሸ/ ዛኪር ኢብራሂም (አባል)
12_ ሸ/ ሙሐመድ አሚን ዐያሽ (አባል)
13_ ሸ/ አሚን ኢብሮ (አባል)
14_ኢንጂነር/ አንዋር ሙስጠፋ (አባል)
33 views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 19:32:17 #ወዳጄ_ሆይ__!!

የህይወትህ መርከብ ካፒቴን አንተ ብቻ ነህ መርከብህን ፈጣሪህ ካሰመረልህ መስመር ውጭ አታሽከርክር መስመር እስካልሳትክ ድረስ ማዕበሉን ትቋቋማለህና!!

https://t.me/Akidatliislamya
https://t.me/Akidatliislamya
32 views16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ