Get Mystery Box with random crypto!

ከስንፍና ሁሉ ትልቁ ስንፍና በቁርአን ትምህርት ብዙ አለመግፋት ነው። ሰላሳ ዓመት ሰግዶ ከቁ | አነል"ሙስሊም" የቁርአን ተፍሲር CHANNEL

ከስንፍና ሁሉ ትልቁ ስንፍና


በቁርአን ትምህርት ብዙ አለመግፋት ነው።
ሰላሳ ዓመት ሰግዶ ከቁል አዑዙዎች እና ከቁል ሁወሏሁ አሐድ አለማለፍን የመሰለ ድክመት ምን አለ!።
ይህን ያውቁ ይሆን?
1- ቁርኣን የሚቀራ ሰው ከተከበሩ የአላህ መላእክት ጋር እንደሚሆን፤
2- ቁርኣን ገርቶለትም የሚቀራዉም ሆነ ከብዶት ለመቅራት የሚታገለው ምንዳ እንዳላቸው፤
3- የዕድሜ ባለፀጋ ሙስሊምን እና ቁርኣን ተሸካሚን ማክበር አላህን ከማክበር እንደሆነ፤
4- ቁርኣን የሐፈዘ ሰው የቂያማ ቀን በሐፈዝከው ልክ የጀነትን ደረጃዎች ዉጣ እንደሚባል፤
5- ልጅ ቁርኣንን በመሐፈዙ ወላጆቹ የቂያማ ቀንእንደሚሸለሙ፤
6- ቁርኣንን የሐፈዘ በፍጥረታት ሁሉ መሃል የክብር ልብስ እንደሚለበስ፣ የክብር አክሊል እንደሚደፋ፤
ይህንንስ
* የቁርኣን ሰዎች የአላህ ልዩ ሰዎች ስለመሆናቸው፤
* አላህ በዚህ ቁርኣን አንዳንዶችን ከፍ ሌሎችን ደግሞ ዝቅ እንደሚያደርግ፤
* በላጫችሁ ቁርኣንን የተማረና ያስተማረ ነው ስለመባሉ፤
* ቁርኣን የትንሳኤ ቀን አዘውትሮ ለሚቀራው ሰው አማላጅ ሆኖ እንደሚመጣ፤
* በሶላት ሰዎችን ለመምራት ተገቢ የሆነው ሰው ይበልጥ ቁርአንን የሚያውቀው ስለመሆኑ ፤
* ሁለት ጀናዛ አንድ ላይ የመቅበር አጋጣሚ ቢፈጠር ቁርኣንን ይበልጥ የሚያውቀው በለሕድ እንዲቀድም እንደሚደረግ።
* አላህ ቁርኣንን ሰጥቶት ቀንና ማታ የሚያነበው ሰው ያስቀናል። በሐዲሥ እንደተገለፀው እንደሱ ባረገኝ ብሎ መቅናትም መልካም ቅናት እንደሆነ።
ይህ ሁሉ ስለ ቁርአን ክብር የተነገረ ነው።
ልጄን አስተምሬያለሁ ማለት ብቻ አይበቃም ፤ጊዜ ወስዶ መማር ያስፈልጋል!!! ኢንሻአሏህ።



@Ahlakii