Get Mystery Box with random crypto!

ከቦታ ቦታ ወድቀውም ሆነ በአስቸጋሪ ሁኔታ ተገኝተው በመነሳት አሁን በገበያ ላይ ከሚገኙ የተንቀሳቃ | AGARO DISH📡AND TECH.INFO/አጋሮ ዲሽና ቴክ መረጃ

ከቦታ ቦታ ወድቀውም
ሆነ በአስቸጋሪ ሁኔታ ተገኝተው በመነሳት አሁን በገበያ ላይ
ከሚገኙ የተንቀሳቃሽ ስማርት ስልኮች የላቀ አቅም እንዳለቸው
ያስመሰከሩ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን መያዝ፡፡ የስማርት ስልከ መያዝ
ወቅቱ ያፈራቸውን መረጃዎች በአቅራቢያችን እንዲኖሩንና
ሌሎች ተጨማሪ ነገሮችን ያለ ብዙ ድካም ለማግኘት
ስለሚረዱን በጥንቃቄ ከተያዙ የማይከፉ ቢሆንም ከላይ
በተጠቀሱት ምክኒያቶች አብዝቶ መጠቀሙ ጉዳቱ የሚያመዝን
መስሎ ስለሚታየን በተገልጋዮች ዘንድ የሚገኘውን የሲምካርድ
ቁጥር በኖርማል ሀንድሴትዎ፣ ለግላዊ ጉዳይ የሚጠቀሙበትን
ሲም ካርድዎ ደግሞ በስማርት ስልክዎ በማድረግ የተለመደ
ህይወትዎን ከቢዝነስ ህይወትዎ በተለያዩ ሁለት ሲም ካርዶች
አማካኝነት እንዲመሩ እንመክራለን፡፡
-አንድ ባለ አንድ አውትፑት (ገመድ ተቀባይ) LNB እና አንድ
ባለ ሁለት አወትፑት LNB ዎች ብንይዝ ለስራ በምንጓጓዝበት
ወቅት የተቃጠሉ፣ ጉዳት የደረሰባቸውን፣ የደከመ የምስል ጥራት
የሚያወጡ LNB ዎችን ለመለየትና በምትኩ በመግጠም
ከአላስፈላጊ ድካምና ወጪ ራሳችንን ማዳን እንችላለን፡፡
ያስታውሱ ሁሌም የተቃጠለ፣የተጎዳ ወይም የደከመ የምስል
ጥራት የሚያወጣ LNB በአዲስ በምንተካበት ወቅት ወዲያውኑ
በምትኩ ለራሳችን መግዛት እንዳለብን በፍፁም መዘንጋት
የለብንም፡፡
-በቤት ኪራይ ምክኒያት ሰዎች ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ ከዚህ
ቀደም የነበረው የዲሽ ገመድ ሳህኑን ከምንተክልበት አዲስ ቦታ
ራቅ ያለ ሊሆን ስለሚችልና በተለያየ አጋጣሚ ገመዶች
የመተጣጠፍና የመቀጥቀጥ አደጋዎች ስለሚደርስባቸው
ለመቀጠያና ለመተኪያ የሚሆን ከ20 ሜትር ያላነሰ የዲሽ
ገመድ ለአያያዝ አመቺ በሆነ መልኩ መያዝ፡፡ ከገመዱ
የሚጠቀሙትን በሜትር አስልተው ከሙያ ዋጋ ክፍያዎ ጋር
ማስከፈልዎንና በምትኩም አዲስ ገመድ መግዛትን አይርሱ፡፡
-ነፃ የኳስ ቻናሎችን ወይም ሁለት LNB የሚጠይቁ ስራዎችን
በምንሰራበት ወቅት ለተጨማሪው LNB ትክክለኛ መቀመጫ
ቦታ ይሆን ዘንድ በጋራጅ ቤቶች ለዚሁ አገልግሎት የተሰራ ዘንግ
(የገበያ ስሙም ዘንግ ነው) መግዛትና መያዝ፡፡
በተለያዩ ቦታዎች ለማጠናከሪያነት ሊጠቅሙን የሚችሉ የተለያዩ
አይነት ሚስማሮችን መያዝ፡፡
-ገመዶች እንዳይጠላለፉና ውበታቸውን ጠብቀው
በግድግዳዎች ላይ እንዲሄዱ የሚያስችሉንን ትክክለኛ መጠን
ያለቸውን የገመድ ክሊፖች መያዝ፡፡
የገመዶችን ርዝመት ለመለካትና ከዚያም በላይ ለተጨማሪ
የሚለኩ ነገሮች የሚያገለግል ሜትር፡፡
- የሳህኑን አናትና እግር ካሰርንና እንዳይነቃነቅ ካጠባበቅን
በኋላ በትንሽ መነካካት ኳሊቲያቸው ሊወርዱና ሊወጡ የሚችሉ
ሳህኖች በንፋስ ሀይል በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ኳሊቲያቸው
ሊወርድ ስለሚችል ይህንን እንዲቋቋምልን የሚያስችለንን ሽቦ
ከተመታው የቆርቆሮ ሚስማር ጋር መወጠር፡፡ እንደዚህ አይነት
አጋጣሚዎች ሊበዙ ስለሚችሉ የተጠቀለለ ሽቦ መያዝ፡፡
-ከላይ የተጠቀሱትን መሳሪያዎችና አንዳንድ ከቦታ ቦታ
ስንንቀሳቀስ የሚያስፈልጉንን የግል ንብረቶቻችን መያዣ የሚሆን
የጀርባ ሻንጣ ሊኖረን ይገባል፡፡ ከዚህ የጀርባ ሻንጣ አንድ
በአንድ የምናወጣቸውን የተለያዩ መሳሪያዎች ስራችንን
ከጨረስን በኋላ መልሰን ማስገባታችንን ሁሌም ቢሆን
ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡
-ለማስተካከል ወይም አዲስ ለመትከል እየተዘጋጀንለት ያለናቸው
ሪሲቨሮች አጠቃቀማቸውን በራሳችን ፍለጋ ማግኘት ወይም
አሰራሩ የተዋሀደው የዲሽ አሰሪ አካል ትብብር መጠየቅ (ብዙ
ጊዜ እጅግ ያረጁና አጠቃቀማቸው ግራ የሚያጋባ ሪሲቨሮች
ይገጥሙናል በዚህ ጊዜ ማድረግ የሚገባን አንድ ነገር ቢኖር
መጀመሪያ ራሳችንን ማረጋጋት ሲሆን ሲቀጥል እንደየ
እድሜያቸውና እንደኛ አቅም፣እና እንደየ ፋብሪካ ስሪታቸው
የሪሲቨሮቹን አሰራር መረዳት ሲሆን ብዙዎቹ ቆየት ያሉ ሪሲቨሮች
በመጠኑ አዳጋችና ለመረዳት ሰፋ ያለ ጊዜን የሚወስድ
ሶፍትዌር የተጫነባቸው ናቸው ይሁንና ያለንን መጠነኛ
የእንግሊዝኛ አቅም በመጠቀም እኚህን ሶፍትዌሮች በቀላሉ ከ
5 ደቂቃ ባለነሰ መልኩ ከራሳችን ጋር ማዋሀድ እንችላለን፡፡)
ይህንንም ድርጊት ማከናወን የአሰራር ፍጥነታችንን እጅግ
የሚያዳብረው ይሆናል፡፡
-በተለያዩ ምክኒያት የሚፈጠሩ የምስል ጥራት መጓደል፣ የኳሊቲ
ማነስና ሎሎች ተዛማች ችግሮችን በፍጥነት ለመለየት
የሚያስችል ከተለያዩ ምንጮች የተገኘ እውቀትና ራስን ሙሉ
በሙሉ ከዘመኑ ጋር እኩል ለማድረግ የሚያስችል ተጨባጭ
ክህሎት ለማዳበር ራስን በተለያየ መልኩ ማብቃት፡፡
-የዲሽ ስራ በባህሪው ከቦታ ቦታ መዘዋወርን የሚጠይቅ ስለሆነ
ሁሉም ቦታዎች ላይ ደግሞ በሚኒባስ፣ በባጃጅ ወይም በጋሪ
መድረስ ስለማይቻል የራሳችን የሆነ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀሻነት
የምንጠቀምበት ሞተር ሳይክል ቢኖረን ጥሩ ነው፡፡ አቅማችን
ሞተር ለመግዛት የማይፈቅድ ከሆነ ደግሞ በኤሌክትሪክ
የሚሰራ ቻርጅ ከተደረገ በኋላ ብዙ ኪሎሜትሮችን መጓዝ
የሚችል ካቴና በተመታ ቁጥር ተጨማሪ ሀይል የሚሰጥ
(Scooter) በመባል የሚታወቅ መንቀሳቀሻ በመግዛት መኪናና
ባጃጆች ሊገቡባቸው የማይችሉ ጉራንጉሮች ውስጥ ሁሉ
ሳይቀር የተቀላጠፈ ስራ መስራት ይቻላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም
ያሉበት ከተማ ዳገት የመይበዛበት ከሆነ ብስክሌት በመግዛት
የፈለጉበት ቦታ ድረስ በመሄድ ስራዎን ማከናወን ይችላሉ፡፡
ማንኛውም የዲሽ ባለሞያ ለስራ በሚንቀሳቀስባቸው ጊዜያት
ሊወስዳቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎችና የስነምግባር መመሪያዎች
-ከምንም ከማንም በላይ ለራሳችን ህይወት ከፍተኛ የሆነ
ጥንቃቄ ማድረግ፡፡ በመሰላል በምንወጣጣበት ወቅት ከሁሉም
አስቀድመን የመሰላሉ ማንኛውም አካል ለአደጋ የሚያጋልጥ
አለመሆኑን በተደጋጋሚ ማረጋገጥ፡፡ መሰላሉ የሚቆምበት ቦታ
የተደላደለ መሆኑን ማረጋገጥ፡፡ በምንወጣበትና በምንወርድበት
ጊዜ መሰላሉ ወደ ጎንና ወደ ኋላ እንዳይንሸራተት በሰው
ማስያዝ፡፡ የተበላሹ የሚነቃነቁ፣ በርጥበት የተጎዱና በምስጥ
የተበሉ መሰላሎች በሚኖሩበት ወቅት ከጎረቤት የተሻለና
አስተማማኝ መሰላል እንዲመጣልን የዲሽ አሰሪዎችን መልካም
ትብብር መጠየቅ፡፡ አስተማማኝ መሰላሎች በማይገኝበት ወቅት
እራስን አደጋ ውስጥ ከማስገባት በፊት ተለዋጭ ቀጠሮ
በመስጠት አስተማማኝ መሰላል ሲገኝ ስልክ እንዲደወልልን
ማድረግ፡፡ ብዙ የሆነ መውጣትና መውረድ ለአደጋ
እንዳያጋልጠን ነገሮችን አስቀድመን መሬት ላይ መጨረስ
ለምሳሌ የዲሹን እግር ከጣውላዎች ጋር መምታትና
የመሳሰሉት፡፡
-እንደሚታወቀው የአብዛኞቻችን የሀገራችን ቤቶች የተሰሩት
ከእንጨትና ከቆርቆሮ በመሆኑና የሚተከሉት የዲሽ ሳህኖችም
ምርጥ ኳሊቲ እንዲገባልን ሲባል ጣራ ላይ በመሆናቸው ጣራ
ላይ ከወጣን በኋላ አግዳሚ ማገር ላይ የተመቱትን የቆርቆሮ
ሚስማሮች እንደ አመላካች በመጠቀም በጥንቃቄ መራመድ
ይኖርብናል፡፡ ለሳህኑ እግር መቀመጫ ቦታ ስንመርጥም ሳህኑ
እንዳይንቀሳቀስ ለማጠናከር የምንጠቀምበትን ድንጋይ ወይም
ብሎኬት ጫና መቋቋም እንዲችል አግዳሚ ማገሩ ላይ መሆን
ይኖርበታል፡፡ ሌላው መውሰድ ያለብን ጥንቃቄ የቆርቆሮ
ጠርዞችን የተመለከተ ሲሆን በምንም አይነት መልኩ
እንዲቆርጡን መፍቀድ የለብንም፡፡ ቆየት ብለው የተሰሩና ያረጁ
ጣራዎች በብዛት በዝገት ስለሚጠቁ የእኛን ክብደት የመቋቋም
አቅማቸው እጅግ የተዳከመ ሊሆን ስለሚችል አስፈላጊውን
ጥንቃቄ መውሰድ ይገባናል፡፡ በስህተት ማገር ላይ ያልተመታ
ቆርቆሮ ላይ በምንረግጥበት ጊዜ የመሰርጎድና ከበድ ያለ
የሚንቋቋ ድምፅ ስለሚሰጠን ፈጠን ብለን እግራችንን ማገር
ላይ ወደ ተመታው ቆርቆሮ መመለስ ይኖርብናል፡፡ እንደ
ድንጋይ፣ብሎኬትና የመሳሰሉትን ከበድ ያሉ ነገሮችን ወደ ጣራ
ይዘን በምንወ