Get Mystery Box with random crypto!

#ህብረትን_መምረጥ መልካም ፍፃሜ የመልካም ህብረት ውጤት ነው፡፡ ያላችሁበት ህብረት ወይ ይሰራች | Agape-True Love

#ህብረትን_መምረጥ

መልካም ፍፃሜ የመልካም ህብረት ውጤት ነው፡፡ ያላችሁበት ህብረት ወይ ይሰራችኀል ወይ ያፈርሳችኀል፡፡ከጠቢባን ጋር ከተጓዛችሁ ጠቢብ ትሆናላችሁ የሞኞች ጓደኛ ከሆናችሁ ግን ራሳችሁን ለጥፋት እያዘጋጃችሁ ነው፡፡

“ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል።”
— ምሳሌ 13፥20

እያንዳንድ የከበረ ፍፃሜ የተወለደው ከመልካም ህብረት ነው፡፡በተመሳሳይ ክብር አልባ የሆኑ ፍፃሜዎቸ የሚወለድት ከክፉዎች ህብረት ነው፡፡

አንድ ግልፅ እና አጭር ምሳሌ ልስጣችሁ
#ከ 5 ጎበዞች ጋር ከሆንክ 6 አንት ነክ
#ከ 5 ሰነፎች ጋር ከሆንክ 6 አንተ ነክ
#ከ 5 ሚፀልዩ ጋር ከሆንክ 6 አንት ነክ
#ከ 5 ሰባኪዎች ጋር ከሆንክ 6 አንተ ነክ
“አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥33

ከዚህ ቀን ጀምሮ ጌታ መንፈስ ቅዱስ ራዕያችሁን ወደ የሚያፈጥን ወደ ትክክለኛ ህብረት ይምራችሁ!በኢየሱስ ስም አሜን!


Share. ... #ሼር አድርጉ
Join
@agapetruelove
@agapetruelove