Get Mystery Box with random crypto!

++ኦርቶዶክሳዊ ስነ ተግባቦት++ (በሰንበት ትምህርት ቤታችን በተዘጋጀው ስልጠና ላይ 'ኦርቶዶ | ባሕራን ሚዲያ አ/ኅ/ደ/ም/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ሰ/ት/ቤት

++ኦርቶዶክሳዊ ስነ ተግባቦት++

(በሰንበት ትምህርት ቤታችን በተዘጋጀው ስልጠና ላይ "ኦርቶዶክሳዊ ሥነ ተግባቦት" በሚል ርእስ በዶክተር ዲያቆን ዳዊት ከበደ ከተሰጠው ትምህርት ላይ የተወሰዱ አስተማሪ ነጥቦች)

፩:-የስልጠናው አስፈላጊነት

1.1 በሰንበት ተምህርት ቤት አገልግሎት ትልቁ ችግር የተግባቦት ክህሎት አናሰ መሆን ነው። ተግባቦት ክህሎት ከቤተክርስቱያን ውጪ በቤተሰብ በሥራ በትዳር ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ነው። ወደ ቤተክርስቲያን ስንመለስ ደግሞ የዳበረ የተግባቦት ክህሎት ወሳኝ ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን።

1.2 ለመዳንም አስፈላጊ ነው ክርስትና በቃልም በህይወትም ይሰበካል። ስለዚህ ሌሎችንም ለማዳን የሚያስብ ሰው ጥሩ የሆነ የስነ ተግባቦት ክህሎት ሊኖረው ይገባል። "ስለ ወንድሙ መዳን የማይደክም ሰው ድኗል ብዬ አላምንም" እንዳለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ።

1.3 ስብከተ ወንጌልን ለማስፉፉት እና ቃለ እግዚአብሔር ተደራሽለማድረግም ያስፈልጋል። በህይወታችን ውጤታማ ደስተኛ ለመሆን እጅግ አስፈላጊው ነገር መልካም ተግባቦት ነው። በእኛ መጥፎ ንግግር ብዙዎች የጠፉ ያዘኑ አሉ።።

፪:-ትርጉም

2.1 ተግባቦት መልካም ግንኙነት የመግባባት ክህሎት የንግግር ክህሎት በማለት ይፈታል። ሰው በአካላዊ እንቅስቃሴ በሶሻል ሚድያ እና በመሰል ጉዳዮች ተግባቦት ይፈጥራል።ከእነዚህ ውስጥም አንዱ የንግግር ክህሎት ነው። ለተግባቦት መሠረታዊ ነገርም የንግግር ክህሎት ነው። የቀደሙ አባቶችም ለዚህ ነገር ትኩረት ሰጥተው ሰርተዋል። በተለይ በዘመነ ሊቃውነት አንዱ የትምህርት ዘርፍ ነው።

2.2 እግዚአብሔር ንግግር ላይ ጥሩ የሆኑትን ለስራው ይጠቀምባቸዋል ለዚህም በሙሴ ታሪክ የተገለጸው አሮን ምሳሊያችን ነው።
"ሙሴም እግዚአብሔርን፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ አፌ ኰልታፋ ምላሴም ጸያፍ የሆነ ሰው ነኝ፤ ትናንት ከትናንት ወዲያ ባሪያህንም ከተናገርኸኝ ጀምሮ አፈ ትብ ሰው አይደለሁም። እግዚአብሔርም፦ የሰውን አፍ የፈጠረ ማን ነው? ዲዳስ ደንቆሮስ የሚያይስ ዕውርስ ያደረገ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?"......“የእግዚአብሔርም ቍጣ በሙሴ ላይ ነደደ እንዲህም አለ፦ ሌዋዊው ወንድምህ አሮን አለ አይደለምን? እርሱ ደህና እንዲናገር አውቃለሁ፤ እነሆም ደግሞ ሊገናኝህ ይመጣል፤ ባየህም ጊዜ በልቡ ደስ ይለዋል።”ዘጸ 4:10

ይህ የሚያሳየን ለሰው ልጆች ለመዳን የሚናገር ሰው እንደሚያስፈልግ ስለተረዳ አሮንን መድቦላቸዋል ስለዚህ የተግባቦት አንዱ ክህሎት ንግግር ነው። ክርስቶስመ በቃሉ በንግግሩ ብዙዎችን አስተምሮ መልሷል።

፫:-የውጤታማ መግባባት ክህሎት

3.1 ማዳመጥ:-

ቦዙዎቻችን ለመናገር እናጂ ሰዎችን ለመረዳት ለማዳመጥ የተዘጋጀን አይደለንም። ተፈጥሮ እንኳን ብዙ እንደንሰማ ነው ሚያስገድደን። አለመስማት አይቻለም አመናገር ግን ይቻላል። “ሳሙኤልም፦ በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።" — 1ኛ ሳሙኤል 15፥22

3.2 አለማቋረጥ

ሰውን በትክክል እስኪጨርስ ድረስ አለመጠበቅ መልስ ለመስጠት አለመቸኮል አንዱ የተግባቦት ክህሎት አለ። "ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለው በመናገሬም አዝናለው በዝምታዬ ግን የዘንኩበት ጊዜ የለም።" አባ አርሳንዮስ

3.3 ጤናማና የማይነቀፍ ንግግሮች መናገር

“የሚቃወም ሰው ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር ሲያጣ እንዲያፍር፥ በነገር ሁሉ መልካምን በማድረግህ ምሳሌ የሚሆን ራስህን አሳይ፤ በትምህርትህም ደኅንነትን፥ ጭምትነትን፥ ጤናማና የማይነቀፍ ንግግርን ግለጥ።”— ቲቶ 2፥7-8

" በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤"1ጴጥ3:5

“ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፤ የጠማማ ምላስ ግን ነፍስን ይሰብራል።”— ምሳሌ 15፥4

"ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው። እነሆ፥ ፈረሶች ይታዘዙልን ዘንድ ልጓም በአፋቸው ውስጥ እናገባለን፥ ሥጋቸውንም ሁሉ እንመራለን።"ያዕ3:1-6

፬:-የመግባባት ክፍተቶች

4.1 ቁጣ

ቁጣ ከዝሙት ጋር ይነጻጸራል። ቁጡ ሰው የዝሙት ጾር ቢነሳበት መመከት አይቻለውም ይባላል።እኔ እናገራለው እንጂ ውስጤ ባዶ ነው የሚል አለ የሰው ልብ ካሳዘንን ከበደልን በኋል ይህን ማለት የሚረባ አይደለም።አንድ አባት እባብም እኮ መርዙን ከተፋ በኋሉ ንጹህ ነው። በማለት ተናግረዋል።

“መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።”
— ኤፌሶን 4፥31

ባስልዮስ ስለ ሰው ልጆ ባሕርይ በጻፈበት ድርሰቱ ላይ እንዲህ ይላል ሰው የእግዚአብሔርን መልክ እንዴት ይመስላል.......የሰውም ልጅ የሰማይ አእዋፍትን ይግዛ ይላል መመስሎ በገዢነት ነው። የሰው ልጅ አራዊትን እንዴት ነው ሚገዛው የሰው ልጅ በምክንያታዊና በብልሀትነቱ ይገዛል። አራዊቶችን ስላልገዛ አይጠየቅም ነበውስጡ ያሉን ክፉ አውሬዎችን ቁጣንና ንዴትን መግዛት አለበት።"

አንድ የራሽያ አባት ደቀ መዛሙርቶቻቸውን ስንናደድ ለምን እንጮሀለን ብለው ጠየቋቸው። ራሳችችንን መቆጣጠር ስለማንችል አሏቸው። እሳቸው ግን በተቃራኒው ስንናደድ የምንጮህው በልባችን መካከል ያለው ርቅት ስለሚጨምር ነው። ሰዎች ሲዋደዱ ደግሞ ዝቅ ብለው በሹክሹክታ ያወራሉ በጣም ሲግባቡ ደግም በዓይን ይግባባሉ። ብለዋቸዋል

4.2 ወቀሳ እና መፍረድ

“ስለዚህም በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።”— 1ኛ ቆሮንቶስ 4፥5

“አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም፤ አትኰንኑ አትኰነኑምም። ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ።” — ሉቃስ 6፥37 ሰውን ለመውቀስ ማስተማር ይቀድማል።

አባ መቃርስ በአበ ምኔትነት በሚያገለግልበት ገዳም አንድ ታውሚጦስ የሚባል መነኮሴ ይኖር ነበር፡፡ በገዳሙ የነበሩት መነኮሳትም አባ ታውሚጦስን ለመክሰስ አባ መቃርስ ፊት በመቆም ይህ ታውሚጦስ የተባለ ሰው እየወጣ ይውላል ከሴት ይገናኛል አሉት፡፡ አባ መቃርስም ልጄ ንጹህ ነው ያለበደሉ አትውቀሱት ብሎ መለሰላቸው፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ታውሚጦስ በድብቅ ሴት ይዞ ሲገባ የተመለከቱ መነኮሳት ወደ አባ መቃርስ በመሔድ ይህው እንዳልነው እንደቀድሞ ግብሩ ሴት ይዞ ገባ በማለት አባ መቃርስን አስከትለው ወደ አባ ታውሚጦስ በዓት ሔዱ፡፡ አባ ታውሚጦስም እንደመጡ ባወቀ ጊዜ ሴቲቷን ከቅርጫ ስር ደበቃት በዓቱንም ከፍቶ መነኩሳትንም ሁሉ ወደ በዓቱ አስገባቸው፡፡ የአባ ታውሚጦስን ስህተት የተረዱት አባ መቃርስም ሴቲቷ የተደበቀችበት ቅርጫት ላይ ከተቀመጥ በኋላ በሉ እንግዲ ያላቹት ሁሉ ውሸት ነው ያልተገባ ፍርድ ነው የፈረዳችሁት ብሎ መነኩሳቱን አሰናበታቸው፡፡መነኮሳቱም ከወጡ በኋላ አባ መቃርስ ከአባ ታውሚጦስ ጋር ጨዋታ ይጀምራል ሰላምታ ከተለዋወጡና ጥቂት ከተነጋገሩ በኋላ የገዳሙ አበ ምኔት አባ መቃርስ እግዚአሔር ሳይፈርድብህ እራስሀ ላይ ፍረድ ብለው ቢነግሩት እኔስ ፈርቼ ነው