Get Mystery Box with random crypto!

#የተከታታይ_የሙያ_ማሻሻያ_ስልጠና( CPD-Training ) #ከየካቲት_1_ጀምሮ በአዲስ አበባ # | አፍሪኬር ቤት ለቤት ህክምና Africare Home Health Care

#የተከታታይ_የሙያ_ማሻሻያ_ስልጠና( CPD-Training )
#ከየካቲት_1_ጀምሮ በአዲስ አበባ
#የጤና_ባለሙያዎች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና መውሰድ እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

የጤና ባለሙያዎች ከየካቲት 1 ቀን ጀምሮ ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ (CPD) ስልጠና መውሰድ እንዳለባቸው ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡

ባለስልጣኑ ከጤና ሚኒስቴር በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ማንኛውም የጤና ባለሙያ ከየካቲት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ (CPD) ስልጠና መውሰድ እንዳለበት አስታወቀ፡፡

በባለስልጣኑ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አምደየሱስ አድነው እንደገለጹት፥ የጤና ባለሙያዎች ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ዋና ዓላማ የጤና ባለሙያዎች ዕውቀታቸውን በማሳደግ ለህብረተሰቡ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ነው፡፡

የባለሙያዎች የሙያ ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ ዳይሬክተር ሙሉጌታ ወንድሜነህ በበኩላቸው፥ የስራና የሙያ ፈቃድ ለማደስ ከሚያስፈልጉ መስፈርቶች በተጨማሪ ተከታታይ የሙያ ማጎልበቻ (CPD) ስልጠና ማንኛውም የጤና ባለሙያ መውሰድ እንዳለበት የጤና ሚኒስቴር ደንብና መመሪያ ማውጣቱን አብራርተዋል፡፡

በዓመት 30 ዩኒት(CU) መውሰድ እንደሚገባ አስገንዝበው ባለሙያዎችም ይህን አሟልተው ሲመጡ የስራና የሙያ ፈቃድ ማደስ እንደሚችሉ ገልፀዋል። ይህን አሟልተው ካልመጡ ግን ጊዚያዊ የስራና የሙያ ፈቃድ በመስጠት እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014ዓ.ም ግን ተከታታይ የሙያ ማጎልበቻ ስልጠና የሚጠበቅባቸውን 30 ዩኒት ሲያሟሉ ቋሚ የስራና የሙያ ፈቃድ ለ3 ዓመት እንደሚሰጥ አብራርተዋል፡፡