አንድ ሰው ቤቱን ሳይረከብ፣ የሱ የቱ እንደሆነ ሳያውቅ በፊት በካርታ ወይም በፕላን ላይ ያለን ቤት መሸጥ አይፈቀድለትም። መልዕክተኛው ﷺ "ያንተ ያልሆነን ነገር አትሽጥ" ብለዋል። 105/ የተወሱልን ትርጉም እያወቀ በመልዕክተኛውም ﷺ ሆነ በተከበሩ ወራቶች ለመጥፎ ነገር ተወሱል የሚያደርግ (የሚመጀን) ሰው ይከፍራል። 106/ ሶላት ግዴታ ባይሆን ኖሮ! ብሎ የተመኘ ሰው ፍርዱ ምንድነው? ሸይኽ ረሒመሁሏህ እንዲህ አሉ፦ "ሶላትን ጠልቶ ከሆነ ይከፍራል፣ ነገር ግን በጣም ከመሳነፉ የተነሳ ከሆነ አይከፍርም"። 107/ ሸይኽ ረሒመሁሏህ እንዲህ አሉ፦ አንድ ሰው በፎቶው አማካኝነት የሰው ዓይን ሊበላው ይችላል። እናም የናንተንም ሆነ የቤተሰቦቻችሁን ፎቶ አታሰራጩ። 108/ የመልዕክተኛው ﷺ የቀብር አፈር እና የዘመዘም ውሃ መድሃኒቶች ናቸው። ሁለቱም ግን የሚበላለጡበት መንገድ አለ። 109/ መላኢካዎች በፈረስ ወይም በግመል ሊመሰሉ ይችላሉ። ነገር ግን መግደላችን ሱና በሚሆንልን እንስሳዎች አይመሰሉም። 110/ ፉቀሃዎች "እንስሳን በክብደት መሸጥ አይፈቀድም" ብለዋል። 111/ ቁርአን ላይ የጽፈትም ሆነ የድምፅ መቅጃ መሳሪያ የመሳሰሉትን ማስቀመጥ ሐራም ነው። .......ይቀጥላል ....... #ምንጭ፦ ከክቡር ዶ/ር ሸይኽ ነቢል ሸሪፍ አል-ሑሰይኒይ (ሐፊዘሁሏህ) ☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ ተማሪ ነኝ። Telegram የምጠቀመው «✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ ለማድረስ ብዮ ነው። ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot አላህ ይ ቀበለን JOIN @Adnan567mh 664 views15:24