Get Mystery Box with random crypto!

የአላህ መልእክተኛ ﷺ ለሙአዝ እንዲህ ብለውታልል። ሙአዝ ሆይ! በአላህ ይሁንብኝ እወድሀለሁ። | የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች

የአላህ መልእክተኛ ﷺ ለሙአዝ እንዲህ ብለውታልል።

ሙአዝ ሆይ! በአላህ ይሁንብኝ እወድሀለሁ። ሙአዝ ሆይ! አንድ ነገር አደራ ልበልህ ከእያንዳንዱ ሰላት በኋላ
"اللهم أَعني على ذڪرك، وشڪرك، وحسن عبادتك
" አሏሁመ አዒኒ ዓላ ዚክሪክ ወሹክሪክ ወሁስኒ ዒባደቲክ"
"አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና አንተን በመልካም በማምለክ ላይ አግዘኝ" ማለትን እንዳትተው።
(صحيح الجامع للألباني ٧٩٦٩)
ሸዳድ ብኑ ዓውስ (አሏህ ስራውን ይውደድለትና) ነብዩ (ሶሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰማሗቸው ይላል "
وفي حديث شدَّاد بن أوس رضي الله عنه: سمعت رسول الله صلى الله عليه وآله وسلم يقول: ((إذا كنز الناس الذهب والفضة، فاكنزوا هؤلاء الكلمات: اللهمَّ إني أسألك الثبات في الأمر، والعزيمة على الرشد، وأسألك شكر نِعمتك، وأسألك حسن عبادتك، وأسألك قلبًا سليمًا، وأسألك لسانًا صادقًا، وأسألك من خير ما تعلم، وأعوذ بك من شرِّ ما تعلم، وأستغفرك لما تعلم، إنك أنت علام الغيوب))
"ሰዎች ወርቅና ብር ሲያከማቹ እናንተ እነዚህን ንግግሮች አከማቹ:-
አሏህ ወይ!
በነገሮች ላይ ፅናትን፣ቅኑ መንገድ ላይ ቁርጠኝነትን እጠይቅሃለሁ፣
ፀጋህን ማመስገንን እጠይቅሃለሁ፣አንተን በመልካም ማምለክን እጠይቅሃለሁ፣
ንፁህ የሆነች ቀልብን እጠይቅሃለሁ፣እውነተኛ ምላስን እጠይቅሃለሁ፣
አንተ ከምታቀው መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ፣አንተ ከምታቀው ሸር ነገር ባንተ እጠበቃለሁ፣
ለምታቀው ነገር ምህረትክን እጠይቅሃለሁ፣ አንተ ኸይብን እጅግ በጣም አዋቂ ነህ"።
ኢማሙ አህመድ(4/123) እና ሌሎች ዘግበውታል
https://t.me/Adnan567mh