ከ̎ነ̎ብ̎ዩ̎ ﷺ̎ የተነገሩ ለሰው ልጅ መድሃኒት የሆኑ 30 ንግግሮች =============================================================== 1 " [ፀሐይ በመግቢዋ እስከምትወጣ ድረስ ወደ አላህ የተመለሰ (የተፀፀተ) አላህ ይቀበላዋል ] . 2 " [እውቀትን ፈልጎ መንገድን የገባ ሰው፤ አላህ ወደ ጀነት የሚወስደውን መንገድ ያገራለታል] . 3" [ከመልካም ነገር ምንንም አትናቅ፤ ወንድምህን በፈገግታ ፊት መገናኘት እንኳን ቢሆን] . 4" [ ከኔ አንድንም አንቀፅ ብትሆን አድርሱ] . 5" [ ወደ መልካም የተጣራ የተከተሉት ሰዎች ምንዳ ሳይቀነስ የነሱንም ምንዳ ለሱ ይሆንለታል ፤ ወደ ጥመት የተጣራ የተከተሉት ሰዎች ወንጅል ሳይቀነስ የነሱን ወንጀልም በሱ ላይ ይሆናል] . 6" [ ከእናንተ መካከል መጥፎን ነገር ያየ በእጁ ይቀይር፣ ያልቻለ በምላሱ ፣ ያልቻለ በልቡ , ይህም የእምነት ደካማው ደረጃ ነው] . 7" [ ከእናንተ በላጫችሁ ቁርአን የተማረና ያስተማረ ነው] . 8" [ ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለው እስካላመናችሁ ጀነት አትገቡም፣ እስካልተዋደዳችሁ ድረስ አታምኑም ። ብትሰሩት የምትዋደዱበት የሆነን ነገር ላመላክታችሁን? በመካከላችሁ ሰላምታን አብዙ ] . 9" [ ከተቸገረ ሰው ላይ ችግሩን ያቀለለ አላህ በዱንያም በአኼራም ያቀለለታል ] . 10" [ ሲሸጥ ፣ ሲገዛ ሆነ ሲፈርድ ይቅር ያለ አላህ ይዘንለት] . 11" አንድ ባሪያ አንድን ባሪያ በዱንያ ላይ ገመናውን አይደብቅለትም አላህ በአኼራ የደበቀለት ቢሆን እጂ] . 12" [ ዝምድና ከዓርሽ ተንጠልጥላ፥ የቀጠለኝ አላህ ይቀጥለው የቆረጠኝ አላህ ይቁረጠው ;ትላለች] . 13 " [ በእውነት ላይ አደራ ፤ እውነት ወደ መልካም ይመራል መልካምም ወደ ጀነት ይመራል ] . 14" [ እኔና የቲሞችን የሚንከባከብ በጀነት ውስጥ እንደዚህ ነን ፥ -መካከለኛዋን እና ጠቋሚ ጣታቸውን አጣምረው እያመላከቱ] . 15 "[ እሱ የሚወሳበትን የአላህን ቤት ያስገነባ ሰው አላህ ለሱ በጀነት ውስጥ ቤትን ይገነባለታል] . 16 "[ ህዝቦቼን አስቸግራለሁ ብየ ባልሰጋ ኖሮ፥ ከሁሉም ሰላት (በፊት) በሲዋክ ባዘዝኳቸው ነበር] . 17 "[ ሁለት ብርዳማ ሳላቶችን የሰገደ ጀነት ገባ ; (የፈጅር እና ዓስር ሰላት)] . 18 "[ አንድ ሰው ወንጀል ሰርቶ;ከዚያም ታጥቦ ሰላት ሰግዶ ምህረትን አይጠይቅም ምህረት የተደረገለት ቢሆን እንጂ] . 19 " [ አንድ ባሪያ ለአላህ ብሎ አንድ ቀን አይፆምም አላህ ሰባ አመታትን ከጀሃነም ያራቀው ቢሆን እንጂ] . 20" [ ምፅዋት ስህተትን ታጠፋለች ውሃ እሳትን እንደምታጠፋው] . 21" [ ከዑምራ እስከ ዑምራ በመካከላቸው ያለውን ያስምራል; ትክክለኛ ሐጅም ምንዳው ጀነት ነው] . 22 " [በሁለት እግሮቹና በሁለት ፂሞቹ (ከንፈሮቹ) መካከል ያሉትን ዋስትና የሚሰጠኝ ጀነትን ዋስትና እስጠዋለው] . 23 " [ አንድ ሰው የተጠማን ውሻ አይቶ ከመጣማቱ የተነሳ አፈር ሲልስ ተመልክቶ በጫማው ውሃ በመቅዳት አጠጣው አላህም ስራውን ወደደለት ጀነትም አስገባው] . 24 " [ ሴት ልጅ አምስት ወቅት ሰላቷን ከሰገደች ፣ ረመዳንን ከፆመች ብለቷን ከጠበቀችና ባሏን ከታዘዘች በፈለገችበት የጀነት በር ግቢ ትባላለች] . 25 " ከልቡ ላ ኢላሃ ኢለላህ (ከአላህ ውጭ በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ) ያለ ጀነት ገባ] . 26 " [በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳውን ያክብር ፤ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ጎረቤቱን ያክብር ፤ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር አልያም ዝም ይበል ] . 27 "[ ከሰዎች ሁሉ በላጩ ይበልጥ ለሰዎች ጠቃሚው ነው] . 28 " [ በማንኛውም ሁኔታ ላይ ሆነህ አላህን ፍራ፥ ከመጥፎ ስራ በኃላም መልካምን አስከትል ታብሳታለች ፤ ሰዎችንም በመልካም ስነምግባር ተኗኗር] ፣ 29" [ጀግና ማለት ታግሎ የጣለ ሳይሆን በቁጣ ጊዜ ነፍሱን የሚቆጣጠር ነው ] . 30 " [ በኔ ላይ አንድን ሰላት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ አስርን ያወርዳል ] https://t.me/Adnan567mh 1.2K views06:03