Get Mystery Box with random crypto!

በኬንያ በደረሰ የከባድ መኪና አደጋ ቢያንስ 48 ሰዎች ሞቱ! በኬንያ እንቅስቃሴ በሚበዛበት መስቀ | አዲስ መረጃ

በኬንያ በደረሰ የከባድ መኪና አደጋ ቢያንስ 48 ሰዎች ሞቱ!

በኬንያ እንቅስቃሴ በሚበዛበት መስቀለኛ መንገድ ላይ በደረሰ በአንድ የትራፊክ አደጋ ቢያንስ 48 ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ እና የዐይን እማኞች ገለጹ።አደጋው የተከሰተው ኮንቴኔር የጫነ ከባድ ተሽከርካሪ በምዕራባዊቷ ከተማ ኬሪቾ አቅራቢያ በሚገኝ ሎንዲያኒ መስቀለኛ መንገድ ላይ ከቁጥጥር ውጭ በመሆኑ እንደሆነ የአገሪቷ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የፖሊስ አዛዡ ጄፍሪ ማዬክ እንደተናገሩት በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪ ሌሎች 30 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።የተጎጂዎች ቁጥርም ከተጠቀሰው በላይ ሊሆን እንደሚችል የፖሊስ አዛዡ ጨምረው ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪም አንድ ወይም ሁለት ሰዎች አሁንም በተገለበጠው ተሽከርካሪ ሥር ሳይሆኑ እንዳልቀሩም ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የፈረንሳዩ የዜና ወኪል (ኤኤፍፒ)፣ ቶም ምቦያ ኦደሮ የተባሉ ሌላ የአካባቢው የፖሊስ መኮንን ጠቅሶ እንደዘገበው ወደ ኬሪቾ ሲጓዝ የነበረው ከባድ ተሽከርካሪ ፍጥነቱን መቆጣጠር አቅቶት ስምንት መኪኖችን፣ በርካታ ሞተርሳይክሎችን፣ በመንገድ ዳር የነበሩ ሰዎችን፣ በጎዳና ላይ እቃ ሲሸጡ የነበሩ እንዲሁም በሌላ ሥራ ላይ የነበሩ ሰዎችን ገጭቷል።

የዐይን እማኞችም ተሽከርካሪው በመንገዱ ላይ ተበላሽቶ የቆመውን አውቶብስ ለማለፍ ሲሞክር ከቁጥጥር ውጪ ወጥቶ አደጋው መከሰቱን ለኬንያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

Via BBC