Get Mystery Box with random crypto!

*ታላቅ የመሻይኾች የዱዓ እና ዚክር ፕሮግራም በዳና ሐሪማ ተካሄደ* ከቅርብ አመታት ወዲህ በሃገራ | Ademina Academy - أكاديمية آدمينا

*ታላቅ የመሻይኾች የዱዓ እና ዚክር ፕሮግራም በዳና ሐሪማ ተካሄደ*

ከቅርብ አመታት ወዲህ በሃገራችን የሰላም እጦት እየተስፋፋ መጥቷል። ዜጎች "አማን አውለን" ብለው ወጥተው በሰላም ቤታቸው መግባት እያቃቃታቸው መጥቷል። ግድያ፣ ዝርፊያና መሰል ኢ ሰብአዊ ክስተቶች እዛም እዚህም ዜና ከመሆን አልፎ ኖርማላይዝ ተደርገዋል።

በተለይ ሙስሊም በዝ የሆነውን የወሎ ማህበረሰብ በቀየው ከአመት በላይ በጦርነት ሲጨፈጨፍ ቆይቶ ከሰሞኑ ደግሞ በወለጋ ክፍለ ግዛት እንደ ሳር እየታጨደ ይገኛል።ይህ እንግዲህ የጎንደሩን ጭፍጨፋ ሳንዘነጋ ማለት ነው። በዚህም ሳቢያ በርካታ ሃሪማዎች ወድመዋል። ደረሶች ተሰደዋል። መሻይኾቹም የሚወዱትን ቂርዓት አቋርጠው በመሰደድ በየቦታው በመንከራተት ላይ ይገኛሉ።

ታዳ ይህን በላዕ ጌታችን አሏህ ያነሳው ዘንድ፣ የንፁሃንም ጭፍጨፋ ይቆም ዘንድ አንጋፋ የገጠር መሻይኾች በተገኙበት በታላቁ የዳና ሐሪማ የዱዓ እና የዚክር ስነ ስርአት ተከናውኗል። አሏህ የመሻይኾቻችንን ዱዓ ይቀበል።አሚን!

ይህ የዱዓ እና የዚክር ፕሮግራም እንዲሳካ ሙሉ ወጭ የሸፈነችውን እህት ዱዓ ታደርጉላት ዘንድ ተጠይቃችኃል!