Get Mystery Box with random crypto!

ጉዳዩ መኖሪያህን ማወቁ ነው። “ሽኮኮዎች ያልበረቱ ሕዝቦች ናቸው፥ ቤታቸውን ግን በቋጥኝ ድንጋይ | addicted to holy spirit

ጉዳዩ መኖሪያህን ማወቁ ነው።

“ሽኮኮዎች ያልበረቱ ሕዝቦች ናቸው፥ ቤታቸውን ግን በቋጥኝ ድንጋይ ውስጥ ያደርጋሉ።”
— ምሳሌ 30፥26
“እንሽላሊት በእጅ ይያዛል፥ በነገሥታት ግቢ ግን ይኖራል።”
— ምሳሌ 30፥28

እዚህ ክፍል ላይ በጣም የሚገርሙኝ እነዚህ ጥቃቅን እስሶች ናቸው።

ሽኮኮ የሚኖሩት በህብረት ነው/ህዝብ/ ሆነው ማለት ነው፤ ነገር ግን ያልበረቱ ህዝቦች ናቸው። እነዚህ እንስሶች ጠቢብ ያደረጋቸው ነገር መኖሪያቸውን መምረጣቸው ነው። የሚኖሩት #በቋጥኝ ድንጋይ# ውስጥ ነው።

ወዳጄ አስተውል ብርቱ አለመሆንህ አያሳስብህ፤ ብርቱ አለመሆንህን አውቀህ መኖሪያህን #በቋጥኝ ድንጋይ# ውስጥ አድርግ። የኔ እና ያንተ የቋጥኝ ድንጋይ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሽኮኮዋ ከቋጥኝ ድንጋዩ የተነሳ አትፈራም፣ አትሰጋም፤ መተማመኛዋም ድንጋዩ ነው። እኔና አንተ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ስለሆንን ከምንሰማው ከምናየው ነገር ተነስተን አንናወጥም፣ አንፈራም፣ አንሰጋም። አሜን!!!

እንሽላሊት ራሷን የምትከላከልበት አቅም የላትም፤ በቀላሉ በእጅ የምትያዝ ናት። ነገር ግን ጠቢብ ናት ምክንያቱም አቅሟን አውቃ መኖሪያዋን #በነገስታት ግቢ# ውስጥ አረገች። ወዳጄ እንሽላሊቷ ምንም ያለመሆኗ ምስጥር ከራሷ ብቃት አይደለም ከመኖሪያዋ አንጂ።

ወዳጄ በአለም ላይ ምንም አይነት ነገር ሊፈጠር ይችላል የማንፈራው፣ የማንሰጋው ሰው ስላልሆንን አይደለም መኖሪያችንን መምረጣችን ነው። መኖሪያችን #የዘላለም አምላክ እግዚአብሔር# ነው።

ወንድሞቼ አንድ ነገር ላሳስባችሁ ከሁለቱ ጠቢብ ጥቃቅን እንስሶች አንድ ነገር ተማሩ በመረጣችሁት መሮሪያ መታመን ይሁንላቹ። መኖሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። አሜን።
@addictedtoholyspirit