Get Mystery Box with random crypto!

ወዳጄ ሆይ በምን ሰከርክ? ************************ አብዝተህ የጠጣኸው ነገር ያሰ | addicted to holy spirit

ወዳጄ ሆይ በምን ሰከርክ?
************************
አብዝተህ የጠጣኸው ነገር ያሰክርሀል.....ትንገዳገዳለህ.......ከቁጥጥርህ ውጭ ሆነህ ያሰከረህ ይቆጣጠርሀል!!

የምትሰክርለት አብዝተህ ለጠጣኸው ጉዳይ ነው!!

ቀንህን የምታሳልፈው ምን እየጠጣህ ነው?

ያልጠጣኸውን መስከር የጠጣኸውን አለመስከር አትችልም!!

አብዝቶ ፖለቲካ የጠጣ ሰው ሰክሮ የሚንገዳገደው ለፖለቲካ ነው!!

አብዝቶ ኳስ የጠጣ ሰው ሰክሮ የሚንገዳገደው ለኳስ ነው!!

አብዝቶ ጥላቻ የተጋተ ሰው ሰክሮ የሚንገዳገደው ለጥላቻ ነው!!

አብዝቶ ክርስቶስን የጠጣ ሰው ሰክሮ የሚንገዳገደው ለክርስቶስ ነው!!

ወዳጄ አብዝተህ የምትጠጣው ምንድን ነው?

ስትሰክር የምትተፋው የጠጣኸውን ነው........በፖለቲካ ሰክረህ ያገኘኸው ሰው ሁሉ ላይ ፖለቲካ እንጂ ኢየሱስ ካፍህ አይወጣም.........በክርስቶስ ስትሰክር ያገኘኸው ሰው ሁሉ ላይ ክርስቶስ እንጂ ጥላቻ ካፍህ አይወጣም!!

የሰከርከው በምንድን ነው?

በክርስቶስ ስትሰክር ስካር ራሱ ያምርብሀል? መንፈስ ሞልቶብህ የምትሰክረው ስካር ለሕይወት የሆነ ትርፋማ ስካር ነው!!

የሰከርከው በክርስቶስ ካልሆነ ሰክረሀል ሳይሆን ከስረሀል ነው የሚባለው!!

እናልህ ወዳጄ ሰክረሀል ወይስ ከስረሀል?


@addictedtoholyspirit