Get Mystery Box with random crypto!

የማያምን አማኝ ***************** የችግሩን ባህር እንደቀልድ ከፍለኸው ፊልም በሚመስል ተ | addicted to holy spirit

የማያምን አማኝ
*****************
የችግሩን ባህር እንደቀልድ ከፍለኸው
ፊልም በሚመስል ተራምዶ እያለፈው
ተርቢያለሁ ቢልህ መና ብትመግበው
ተጠማሁኝ ቢልህ ከአለት ብታጠጣው
እግሩ እየረዘመ ጫማዎች ባያጥሩት
ሰውነቱ ሲገዝፍ ልብሶቹ ባይጠቡት
ጠላቶቹን ሁሉ ብታሸንፍለት
ፅልመቱን አንስተህ ጎህ ብትቀድለት
"የማያምን አማኝ"
እንቅፋት እያየ በልቡ ያምፃል
ለተድላ ቢታጭም ባርነት ይመኛል።

Share &join
@eyobapoem

#ኢዮብ ጥላሁን።