Get Mystery Box with random crypto!

ለጓደኞቹ፣ ለስራ ባልደረቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን። == # አዳብና | አዳብና መልቲ ሚዲያ

ለጓደኞቹ፣ ለስራ ባልደረቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን።
==
# አዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር

ዜና እርፍት

ወጣት ኢንጂነር ይስሃቅ ታደሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ወጣት ይስሃቅ ከአባቱ አቶ ታደሰ ገለቱ ከእናቱ ወ/ሮ ፈለቀች መገርሳ በ1980 ዓ.ም ቡኢ ከተማ ውስጥ ተወለደ። ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ የ1ኛ ደረጃ ትምህርቱን በቡኢ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃና መስናዶ ትምህርቱን በሶዶ ቡኢ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ከተከታተለ በኃላ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሜካኒካል ኢንጂነሪንግ የትምህርት መስክ የከፍተኛ ትምህርቱን ተከታትሏል።

ወጣት ይስሃቅ የከፍተኛ ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት በማዕረግ ካጠናቀቀ በኋላ በኢትዮጵያ መርከብ ትራንስፖርት ድርጅት በመቀጠር አገሩን አገልግሎዋል። ባጋጠመው የጤና ዕክል ድርጅቱን በመልቀቅ ወደተውለደበት አካባቢ በመመለስ በቡኢ ከተማ አስተዳደር መንገድ ትራንስፖርት ፅ/ቤት በአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድ ማረጋገጫ ዋና ስራ ሂደት የአሽከርካሪ ፍቃድ ማረጋገጥ ባለሙያ በመሆን ህይወቱ እስካለፈበት ድረስ በቅንነት ሲያገለግል ነበር።

ወጣት ይስሃቅ ከአለማዊ ህይወቱ በተጨማሪ በመንፈሳዊ ህይውቱም በቡኢ ደብረ ሰላም ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲያን ከልጅነቱ ጀምሮ ቤተክርስቲያኒቱን በድቁና አገልግሎዋል።

ወጣት ይስሃቅ በትምህርቱ እጅግ የተዋጣለት በባህሪው ሰው አክባሪ በስራው ትጉህና ታታሪ ወጣት ነበር።

ወጣት ኢንጂነር ይስሃቅ ታደሰ በቀን 22/03/2015 ዓ.ም ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ህይወቱ አልፎዋል። የቀብር ስነ ስርዓቱም በቡኢ ደብረ ሰላም ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲያ በቀን 24/03/2015 ዓ.ም በዕርገት ይፈፀማል።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር በወጣት ኢንጂነር ይስሃቅ ታደሰ ህይወት እልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለፀ ለጓደኞቹ፣ ለስራ ባልደረቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለቤተሰቦቹ መፅናናትን ይመኛል።