Get Mystery Box with random crypto!

በቡድን በቪዲዮ ዪምር ዪምር የማሳየት ዘርፍ ተወዳዳሪዎች አጭር ማብራሪያ * ለውድድሩ መዝገባ የም | አዳብና መልቲ ሚዲያ

በቡድን በቪዲዮ ዪምር ዪምር የማሳየት ዘርፍ ተወዳዳሪዎች አጭር ማብራሪያ
*
ለውድድሩ መዝገባ የምናከናውነው እስከ ህዳር 30 ብቻ ነው።
ቪዲዮ የምንረከበው እስከ ታህሳስ 15 ብቻ ነው
ገለልተኛ ግልፅ በሆኑ መስፈርቶች ፕሮፌሽናልና ታዋቂ በሆኑ ሰዎች ይዳኛል። 30% በማህበራዊ ማዲያ በህዝብ ይዳኛል።
በማንኛውም ቦታ(ከሀገር ውጪም ሀገር ውስጥም) ሆናቹ ቪዲዮ በመላክ ብቻ መወዳደር ትችላላቹ።አሜሪካ፣አውሮፓ ሀረብ ሀገራት ያላቹ በዚህ ውድድር እንድታተፉ ትበረታታላቹ።
ውድድሩ ከ30%እድሜ በታች የሆኑና ከ8ዓመት ጀምሮ ያሉ ታዳጊዎችን ጭምር ያካትታል።ከ13 ዓመት በታች ያሉ ወንድ ታዲዎችም ማካተት ይቻላል።
የዪምር ትክክለኛና ሙሉ ስነስርዓት ማሳየት ይጠበቅባችዋል
ለዪምር የሚያስፈልጉ ግብሃቶች ማሟላት(ወንፊት፣አንጮት፣ገንቦ፣ጣሳቆሎ፣ጠላ፣) ማሟላት ተመራጭ ያደርጋል።
በተቻለ መጠን የአካባቢው አልባሳትና ጌጣጌጥ መጠቀም ተመራጭ ያደርጋል
ባህሉን ጥበባዊና ድራማዊ በሆነ መልኩ እንዲሁም ከባህሉ ጋር የተያያዘ ተጨማሪ እሴት መጨመር ተመራጭ ያደርጋል።
በጥሩ ቪዲዮ ካሜራ ወይም ጥራት ባለው የስልክ ካሜራ ስለቀረፃ እውቀት ባለው ሰው ሊቀረፅ ይችላል።አቀራረፁና ጥራቱ ከውድድሩ መስፈርቶች አንዱ ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
አዲስ አበባና ሀገርቤት ላላቹ የቡድን ተወዳዳሪዎች ቀረፃው በእኛ በኩል ልናከናውንላቹ እንችላለን።

ቡድን መመስረት የሚያስችል የሰው ብዛት ወይም ብቸኛ የሆናቸው ሌሎች ቡድኖች እንድትቀላቀሉ እድሉን እናመቻቻለን።
ስለዪምር ስለዪምር እውቀቱና መረጃ የሌላቹ በቪዲዮና በፅሁፍ መረጃው ከእኛ ማግኘት ትችላላቹ።እንዲሁም እንዴት መስራት እንዳለባቹ እናማክራለን።

የአዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበርና ተባባሪ አዘጋጆች
ለበለጠ መረጃ
ስልክ ቁጥር
0910186703
0910337765