Get Mystery Box with random crypto!

ሚስ ዪምር ዪምርና የገና ፌስቲቫል ቀጣዩ ፕሮግራማችን ነው። ** ማህበራችን የአዳብና በክስታኔ ዓለ | አዳብና መልቲ ሚዲያ

ሚስ ዪምር ዪምርና የገና ፌስቲቫል ቀጣዩ ፕሮግራማችን ነው።
**
ማህበራችን የአዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ድንቅ ፣ጥንታዊ ከሆነውና ከገና በዓል ጋር ተያይዞ በልጃገረዶች የሚከበረው የዪምር-ዪምር ባህል ለማስተዋወቅ ሰፊ ፕሮጀክት ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

ማህበራችን ለገና በዓል ከያዛቸው ፕሮግራሞች መካከል
ሚስ ዪምር-ዪምር ባህላዊ የቁንጅና ውድድር
ልዩ የገና ፌስቲቫል በአማውቴ:-ዪምር ዪምር፣እንዞሪቴ፣የገና ጫወታ(አንቃት)ና የፈረስ ጉግስ ያካተተ ፕሮግራም
የገና የቴሌቪዥን ዶክመንተሪ ፊልም የሚጠቀሱ ናቸው።

ለሚስ ዪምር ዪምር መወዳደር የምትፈልጉ ከነገ ህዳር 16 ጀምሮ ምዝገባ ይጀምራል።

የውድድር ዘርፎች

1ኛ:-በአካል መድረክ ላይና ከመድረክ ውጪ በሚዘጋጁ ውድድሮች በመሳተፍ ዪምርዪምርን ማሳየት
2ኛ :-በቡድን በመሆን በቪዲዮና በፎቶ ዪምር ዪምርን መግለፅ
3ኛ :-ባሉበት ቦታ በፎቶ መወዳደር
4ኛ:-ለተወዳዳሪዎች የባህላዊ ልብስ ዲዛይ ውድድር

የምዝገባ መስፈርቶች
ማንኛው ፍላጎት ያለውና ባህሉን ጠንቅቆ ማሳየት የሚችል
በአካል ለምትወዳደሩ ቁመት 1.5m በላይ
ለሁሉም ተወዳደሪዎች ዕድሜ ከ30 ዓመት በታች

የምዝገባ ጊዜ ከህዳር 15-ህዳር 30

የየዘርፉ አሸናፊዎች ዳጎስ ያለ ሽልማት ይጠብቃቸዋል።

ስልክ ቁጥር
0910186703
0910337765