Get Mystery Box with random crypto!

የመስቀል በዓል በሰሜን አሜሪካ በየዓመቱ የክስታኔ ጉራጌ ተወላጆች በመሰባሰብ  በድምቀት ያሳልፉታል | አዳብና መልቲ ሚዲያ

የመስቀል በዓል በሰሜን አሜሪካ በየዓመቱ የክስታኔ ጉራጌ ተወላጆች በመሰባሰብ  በድምቀት ያሳልፉታል። ዘንድሮም ልክ እንደዚህ ቀደም "መስቀል በጉራጌ" በሚል መሪ ቃል ሁሉም የጉራጌ ተወላጆችና ወዳጆች ባሳተፈ መልኩ በድምቀት ተከብሮሯል።

የፕሮግራሙ አዘጋጆች እንደ ገለፁልን። በየዓመቱ መስቀልን ተሰባስቦ ከማክበር ባሻገር የጉራጌ ባህል በሰሜን አሜሪካ በሚኖሩ በሌሎች ማህበረሰቦች ዘንድ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቅ በቀጣይ ጊዜያት ለህዝብ አመቺና በብዛት ሊሰበሰብባቸው በሚችሉ (ስታዲየም) "መስቀል በጉራጌ" በፌስቲቫል ደረጃ ለማዘጋጀት ሂደቶች ላይ እንዳሉ አሳውቀውናል።

ይህ እንዲሁ እንዳለ በተጨማሪም የጉራጌ ተወላጆች ለወጡበት ማህበረሰብ (ለትውልድ ቄዬአቸው) የረጅምና ያጭር ግዜ ዕቅዶችን በመንደፍ በልማቱ ዘርፍ፦
በንፁህ መጠጥ ውሃ፣በትህምርትና በጤና ያሉትን ችግሮችን ለመቅረፍ በአሜሪካ ህግ መሰረት ፍቃድ አውጥተው የባንክ አካውንትም ከፍተው በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ ገልፀውልናል።



ባህላችን ለዓለም እናሰተዋውቅ!
ቅርሶቻችን በአንድነት እንጠብቅ!

አዳብና  መልቲ ሚዲያ Telegram ሊንኩን በመንካት ይቀላቀሉ። https://t.me/Adabnamidea

አዳብና You tube like share subscribers
በማድረግ ባህላችንን  ቅርሶቻችንን እናሳድግ ።

አዳብና ሚዲያ ዩቱብ https://youtube.com/channel/UCbihhwTdI6hy-e7Kj6T_J8g