2022-09-10 08:35:51
የ2015 ዓ.ም ባሕረ ሐሳብ የአጽዋማትና የበዓላት ማውጫ ስሌት
ክፍል ፩ ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
ዓመተ ዓለም = ዓመተ ምሕረት + ዓመተ ኩነኔ (ፍዳ) = 2015 + 5500 =7515
ወንጌላዊ ፦ በዓመቱ የሚሾም ወንጌላዊ ማለት ነው፡፡
ዓመተ ዓለም፥4
7515 ÷ 4 = 1878
1878 ፦ መጠነ ራብዒት ይባላል፡፡
1878×4=7512
7515-7512=1341 ደርሶ ቀሪ 3
ቀሪው ' 1 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ
ቀሪው ' 2 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ
ቀሪው ' 3 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ
ቀሪው ' 0 ' ከሆነ (ያለ ቀሪ ከተካፈለ)ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ይሆናል።
ስለዚህ ቀሪው '3' ስለሆነ የዘንድሮው ወንጌላዊ ሉቃስ ሲሆን ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ ይባላል።
•••
ዕለተ ቀመር፦ መስከረም አንድ የሚውልበት ቀን ነው፡፡
ዕለተ ቀመር= ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት÷7
= 7515 + 1878 =9393
= 9393 ÷ 7 = 1341 ደርሶ ቀሪ 6 ይሆናል
ቀሪው '0 'ከሆነ ሰኞ
ቀሪው '1' ከሆነ ማክሰኞ
ቀሪው '2 'ከሆነ ረቡዕ
ቀሪው '3 'ከሆነ ሐሙስ
ቀሪው '4 'ከሆነ ዓርብ
ቀሪው '5 'ከሆነ ቅዳሜ
ቀሪው '6 'ከሆነ እሁድ መባቻ ይሆናል። በመሆኑም ዘንድሮ ቀሪው '6' ስለሆነ ዕለተ ቀመር እሑድ ይሆናል።
•••
መደብ = ዓመተ ዓለምን በዐቢይ ቀመር(532) በማዕከላዊ ቀመር(76) እና በንዑስ ቀመር(19) በማካፈል ማግኘት እንችላለን
1.7515፥532=14 ደርሶ ቀሪ 67
2.67 ለ ማዕከላዊ ቀመር ወይም ለ 76 መካፈል ስለማይችል ቀጥታ ለንዑስ ቀመር (19) ይካፈላል።
67 ፥19=3 ደርሶ 10 ይቀራል።
ስለዚህ መደብ 10 ይሆናል፡፡
•••
ወንበር =መደብ ሲቀነስ አንድ ነው(አሐደ አእትት ለዘመን የሚል አዋጅ አለና ላለፈው መሸኛ ለሚመጣው መቀበያ)
መደብ - 1=ወንበር (10 - 1= 9) ይሆናል።
በዚህም መሠረት ወንበር 9 ነው እንላለን
አበቅቴ ፦ጥንተ አበቅቴን በዘመኑ ወንበር አባዝተን ከ 30 በላይ ከሆነ በ30 ገድፈን ቀሪውን ከ30 በታች ከሆነ ደግሞ የመጣውን ቁጥር በመጠቀም እናገኛለን።
አበቅቴ =11×9=99
99፥30= 3 ደርሶ ቀሪው 9 ይሆናል ስለዚህ የዘንድሮው አበቅቴ 9 ነው እንላለን።
አበቅቴን ለማግኘት ሌላው አማራጭ ያለፈው ዘመን አበቅቴ ላይ ጥንተ አበቅቴን (11) በመጨመር የሚገኘው ቁጥር ከ30 በላይ ከሆነ ለ 30 በማካፈል ቀሪውን ከ30 በታች ከሆነ ደግሞ የመጣውን ቁጥር በመጠቀም ማግኘት እንችላለን ። ይህም ማለት
የ2014 ዓ.ም አበቅቴ 28 ነበር፤ ስለዚህ የ2015 ዓ.ም አበቅቴን ለማግኘት 28+11=39
ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 9 ስለሆነ አበቅቴ '9' ይሆናል ማለት ነው።
መጥቅዕ፦ ጥንተ መጥቅዕን በዘመኑ ወንበር አባዝተን በ 30 በመግደፍ(በማካፈል) እናገኛለን።
መጥቅዕ = 19×9 = 171
171 ÷ 30= 5 ደርሶ ቀሪው '21 'ስለሆነ መጥቅዕ ዘንድሮ '21 'ይሆናል።
መጥቅዕን ለማግኘት ሌላው አማራጭ ያለፈውን ዘመን መጥቅዕ ከጥንተ መጥቅዕ ላይ( 19 ) በመጨመር የሚገኘው ቁጥር ከ30 በታች ከሆነ ራሱ ከ30 በላይ ከሆነ ለ 30 ተካፍሎ ቀሪው የዘመኑ መጥቅዕ ይሆናል። ይህም ማለት የ2014 ዓ.ም መጥቅዕ 2 ነበር፤ ስለዚህ የ2015 ዓ.ም መጥቅዕን ለማግኘት
2+19=21 ስለዚህ የ2015 መጥቅዕ '21' ይሆናል ማለት ነው።
“አበቅቴ ወመጥቅዕ ክልዔሆሙ ኢይበዝኁ እም ሠላሳ ወኢይውኅዱ እም ሠላሳ ወትረ ይከዉኑ ሠላሳ ፤
አበቅቴ ቢበዛ መጥቅዕ ቢያንስ መጥቅዕ ቢበዛ አበቅቴ ቢያንስ ከሠላሳ አይበዙም ከሠላሳ አያንሱም”
ይህም ማለት በሌላ አገላለጽ መጥቅዕና አበቅቴ ተደምረዉ ውጤቱ ከሠላሳ መብለጥና ማነስ
የለበትም፤ ሁልጊዜ ሠላሳ ይሆናል፡፡ የዘንድሮዉ የ2015 ዓ.ም = 9+21= 30
መጥቅዕ ከ14 በላይ ከሆነ በመስከረም ይዉላል፤
መጥቅዕ ከ14 በታች ከሆነ በጥቅምት ይዉላል፤
መጥቅዕ በመስከረም ቢዉል ጾመ ነነዌ በጥር፣ መጥቅዕ በጥቅምት ቢዉል ጾመ ነነዌ
በየካቲት ይውላል።
ስለዚህ በዚህ ዓመት መጥቅዕ 21 ስለሆነ ከ14 ይበልጣል፤ ስለዚህም መጥቅዕ በመስከረም ይዉላል፤
•••
ስለዚህ የ2015 መጥቅዕ መስከረም 21 ሲሆን መጥቅዕ የሚወድቅበት ዕለት (ዕለተ መጥቅዕ) ቅዳሜ ይሆናል፡፡
•••
መባጃ ሐመር= የዘመኑ መጥቅዕ + መጥቅዕ የወደቀበት የዕለት ተውሳክ በመጠቀም የሚገኘው ቁጥር ከ 30 በላይ ከሆነ ለ 30 በማካፈል ቀሪውን መባጃ ሐመር እንላለን፡፡
ልብ ይበሉ የዕለታት ተውሳክ ከቅዳሜ ይጀምራል፡፡
የቅዳሜ---8
የእሑድ---7
ክፍል ፪ እና ፫
ስለ ግእዝ እንማርን ይቀላቀላሉ እና አንብበው ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ
https://t.me/Learning_Geez
https://t.me/Learning_Geez
https://t.me/Learning_Geez
https://t.me/Learning_Geez
መልካም
አዲስ
ዓመት
3.6K viewsYonas, 05:35