Get Mystery Box with random crypto!

አደራ! ቁርኣን እንቅራ ~ በርግጠኝነት እዚህ ሶሻል ሚዲያ ላይ ከሚርመሰመሱ ወገኖቻችን ውስጥ ቁርኣ | قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

አደራ! ቁርኣን እንቅራ
~
በርግጠኝነት እዚህ ሶሻል ሚዲያ ላይ ከሚርመሰመሱ ወገኖቻችን ውስጥ ቁርኣን ያልቀሩ ብዙ ወገኖች ይኖራሉ። ወላሂ ሊቆጨን ይገባል። በዚህ አማራጮች በበዙበት ዘመን እንዴት ድንቁርናን አሚን ብለን ተቀብለን በጨለማ ውስጥ እንኖራለን? የትም ብንሆን ካለንበት ቦታ ሆነን መማር እንደሚቻል የሚታወቅ ነው። አላህ ባገራልን መንገድ እንማር። ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን የተማረና ያስተማረው ነው" ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 5027]
ስለዚህ ያልተማርን ጊዜ ሰጥተን እንማር። የተማርን መልክቱን እንማር፣ ባወቅነው እንስራ። በየቀኑ ከጊዜያችን ውስጥ ለቁርኣን ድርሻ ይኑረን። በምንችላት መጠን ለመሐፈዝ እንሞክር። የእድሜ መግፋት ቁርኣን ከመማር አያግድም። በርካታ ሶሐቦች በጎልማሳነት ዘመናቸው ነው ቁርኣን የቀሩት። ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አል0ባድ "አንድ ሰው ከሃምሳ አመቱ በኋላ ቁርኣን ሊሐፍዝ ይችላል ወይ?" ተብለው ተጠይቀው ነበር። ምላሻቸው እንዲህ የሚል ነበር፦
"አዎ! እኔ ራሱ ከሃምሳ በኋላ ቁርኣን ከሐፈዙት ውስጥ ነኝ። ሶሐቦች - ረዲየላሁ ዐንሁ - ትልልቅ ሰዎች ሆነው ነው ኢስላም ያገኛቸው። ከመሆኑም ጋር ቁርኣንን ሐፍዘዋል።"
ስለዚህ በየትኛውም ምክንያት በልጅነቱ ቁርኣን ያልቀራ ሁሉ እራሱን አያዳክም። "በአላህ ፈቃድ እችላለሁ" ብሎ ይነሳ። ኢንሻአላህ ይችላል። አለማወቅን ታቅፈን ፈፅሞ ምቾት ሊሰማን አይገባም። ሰው እንዴት ቁርኣን ሳይቀራ እድሜውን ይፈጃል?!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor