Get Mystery Box with random crypto!

መሀከለኝነት(ወሰጢያህ) 【الوسطية السلفية】 قال الشيخ سليمان | قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

መሀከለኝነት(ወሰጢያህ)
【الوسطية السلفية

قال الشيخ سليمان الرحيلي وفقه الله:
فالوسطية هي موافقة الكتاب والسنة
ሸይክ ሱለይማ አሩሀይሊይ አላህ ይጠበቃቸውና《መሀከለኛ(አማራጭ የለሽ ተመራጭ) በመባል የሚታወቀው ትክክለኛው የኢስላም አስተምህሮት ማለት በቁርአንና በጠንካራ(ሰሂህ) ሀዲስ የተጦቀመው አስተምህሮት ብቻ ነው።》
وما يخالف الكتاب والسنة فإنه لا وسطية فيه،
بل هو إما غلو وتعمّق وتنطّع،
وإما يعني تفريط وتساهل،
ከቁርንና ከሀዲስ አስተምህሮት የሚቃረን አስተምህሮት በፍፁም መሀከለኝነት(ወሰጢያህ) ሊሆን አይችልም።
ከቁርአንና ከሀዲስ አስተምህሮት የሚቃረን አስተምህሮት ከሁለት አንድ ነው
ወይ ከመሀከለኛው አስተምህሮት በማክረር ያፈነገጠ ድንበር አላፊ
አለያም በቁርአንና በሀዲስ የመጣውን ትክክለኛ የኢስላም አሰተምህሮት የሆነውን የመሀከለኛ(የወሰጢያህ) መንገድ ህግጋትን ቸል በማለት አባ እንዳሻውነት ነው ሚሆነው።》

فوالله الذي لا إله إلا هو ما خالف القرآن ولا خالف السنة أمر فيه خير، بل كل ما يخالف القرآن والسنة شر للأمة، ولا وسطية فيه، ولا خير فيه.
ከእሱ ሌላ በሀቅ የሚመለክ አምላክ የሌለ በሆነው በአላህ እምላለው ከቁርአንና ከሀዲስ የሚቃረን አስተምህሮ በሙሉ የኢስላምና የህዝበ ሙስሊም አደገኛ አደጋ እንጂ መሀከለኝነትም(ወሰጢያም) ሆነ ጠቃሚ ሊሆን አይችልም።》
والذي يأتينا بشيء يزعم أنه وسطية وهو يخالف القرآن والسنة، فإنا نسأله: هل الوسط هو ما في القرآن والسنة، أو هذا الذي تعمله،
አንድ ሰው ከቁርአንና ከሀዲስ አስተምህሮት የሚጋጭ አስተምህሮትን ይዞ በመምጣት ይህ መሀከለኝነት(ወሰጢያህ) ነው ቢል
የሁላችንም ጥያቄ ሊሆን ሚገባው ቁርአንና ሀዲስ ያመላከተው አስተምህሮት ነው መሀከለኝነት(ወሰጢያህ) ወይስ አንተ የምትሰራው(ያለህበት)? የሚል ነው።》

فإن قال: إن الوسط هو الذي أعمله، وما في القرآن تطرف، فإن هذا -والعياذ بالله- كفر، وخروج من الملة، ولا يرضى أصلا مسلم أن يتلفظ به فضلا عن أن يعتقده.
ግለሰቡ መሀከለኝነት(ወሰጢያህ) ማለት ቁርአንና ሀዲስ ያመላከተው ሳይሆን እኔ ያለውበት ነው ካለ ከኢስላም የሚያወጣ ክህደትን (ኩፍርን) ይክዳል(ይከፍራል)።
እንዲህ አይነቱን የክህደት(የኩፍር) አቋም አንድ ሙስሊም ሊያምንበት አይደለም ከአንደበቱ እንኳን ሊወጣ አይገባም።》

وإن قال: إن الوسط هو الذي في القرآن والسنة. قلنا: إن الذي أنت عليه إنما هو أحد الطرفين المذمومين: إما أنه تشدد، وإما أنه تفريط؛ لأنه لا يمكن أن يكون الحق في الأمرين المختلفين، بل أحدهما حق والآخر ضلال.
دورة الوسطية في حياة الصحابة - الدرس الرابع
ነገር ግን ግለሰቡ መሀከለኝነት(ወሰጢያህ) ማለት እኔ ያለሁበት(የምሰራው) ሳይሆን ቁርአንና ሀዲስ ያስተማረውና ያመላከተው ነው ካለ ግን የኛ ጥያቄ ሊሆን የሚገባው ትክክለኛው መንገድኮ አንድና አንድ ብቻ ነው
እሱም ትክክለኝነቱ በቁርአንና በሀዲስ የተመሰከረለት ብቻ ነው።
አንተ ያለህበት የእምነት መንገድ ደግሞ ከቁርአንና ከሀዲሰ የእምነት አስተምህሮት ጋር በግልፅ የሚጋጭ ነው።
ስለዚህ ያንተ የእምነት መንገድ የድንበር(የወሰን) ማለፍ አካሄድ አለያም አለአግባብ የሆነ ማገራራትና መዘጋት ያለበት ነውና ወደ ትክክለኛው ወደ ቁርአንና ሀዲስ አስተምህሮት ወደ መሀከለኝነት(ወሰጢያ) ራስህን ማምጣት ይጠበቅብሀል ማለት ይሆናል።


ደውረቱል ወሰጢያህ ፊ ሀያቲሰሀባህ አራተኛው ትምህርት የተወሰደ

https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy