Get Mystery Box with random crypto!

ለአርባ ሺህ ሰዎች መስለም ሰበብ የሆነው አስደናቂ ውሻ ገድል! ☞የክርስትና እምነት ተከታዮች | 📚ፈዋኢድ እና ፈራኢድ📚

ለአርባ ሺህ ሰዎች መስለም ሰበብ የሆነው አስደናቂ ውሻ ገድል!


☞የክርስትና እምነት ተከታዮች ሞንጎላዊያን ክርስትናን እንዲቀበሉ በመቋመጥ በሞንጎላዊያን ጎሳዎች መካከል ሰባኪዎቻቸውን ይልካሉ። ይህን መስመር ያመቻቸላቸው አረመኔው ሆላኮው አንዲት ዘፈር ኻቱን ከምትባል ክርስቲያን ሴት ጋር በትዳር በመቆራኘቱ ሰበብ ነበር።

ከእለታት አንድ ቀን ታላላቅ የሚባሉ የክርስቲያን ቀሳውስት ከሞንጎላዊያን መሪዎች መካከል አንዱ ክርስትናን በመቀበሉ ሰበብ የተደገሰውን ታላቅ ድግስ ለመታደም ወደ ቦታው ተመሙ። በዚህም መሀል ከቀሳውስቱ መካከል አንዱ ተነስቶ የአላህ መልእክተኛን ሙሐመድን (صلى الله عليه وسلم) መሳደብ ጀመረ። እዛው ቦታ ላይ የአደን ስልጠናን በሚገባ የተማረ አደገኛ ውሻ ታስሮ ነበር። ይህ ክፉ መስቀለኛ ቄስ ረሱልን መሳደብ ሲጀምር ውሻው ማጉረምረም ጀመረ። ከዛም በእልህ እየጮኸ ቄሱ ላይ ዘሎ በሀይል ቧጨረው። ቦታው ላይ የታደሙ ሰዎች ቄሱን ከዚህ አደገኛ ውሻ በመከራ ገላገሉት።

ይህን ክስተት እዛው ተጥደው የነበሩ ሰዎች "የሙሐመድን ክብር ስለነካህ ይሆናል ውሻው እንዲህ የቧጨረህ" አሉት።
ቄሱም "በፍፁም! ውሻው አደገኛ ስለሆነ በእጄ ወደ እሱ ሳመላክት ልመታው ያሰብኩ መስሎት ነው የዘለለብኝ" አለ።

ከዚያም የአላህ መልእክተኛን በድጋሚ መወረፍና መሳደቡን ተያያዘው። የዚህ ግዜ ነበር ጉዱ ........
ውሻው የታሰረበትን ገመድ በጥሶ የቄሱ አንገት ላይ ዘሎ ደም ስሩን በጣጥሶ ወዲያውኑ ገደለው። እስትንፋሱን አሳጣው።

ይህን አስደናቂ ትእይንት ሲመለከቱ የነበሩ ወደ አርባ ሺህ ሞንጎላዊያን ኢስላምን ተቀበሉ።

አላሁ አክበር!


☞ይህን አስደናቃ ክስተት ታላቁ የኢስላም ሊቅ ኢብኑ ረጀብ (አላህ ይዘንለት) በዚህ ድርሳናቸው አፅድቀው ከትበውታል ▼▼▼▼▼▼

[الدرر الكامنة (202)]

እስኪ እኔን አንዴ አንብቡኝ!

☞የዚህን ውሻ አንድ አስረኛ እንኳን ለኢስላምና ለሱና መቆርቆር በቻልን አትሉም!

☞በህይወት ዘመንህ ቢያንስ አንድ ሰው በሰበብህ ወደ ኢስላም እንዲገባ ጥረት አርግ። ይህ ካቃተህ ከኢስላም እንዳይወጣ ታገል። ይህ ካቃተህ በአንተ ሰበብ ሰዎች ከኢስላም እንዳይወጡ ሞክር። ይህ ካቃተህ ውሻው ከአንተ ይሻላል ማለት ነው!

☞ውሻው ሰንሰለቱን ፈቶ ጠላት ላይ እንደዘለለው እኛም በስሜት ማነቆ የታሰርንበትን ዘለበት ፈተን ለኢስላም ዘብ እንቁም!

☞እንደ ውሻው መናከስ ባንችልም ሱናን ነክሰን እንያዝ!

☞እንደ ውሻው መጮህ ባንችልም ሱናን ለማስተማር በየቦታው ለሚጮኹ እውነተኛ ዳዒዎች ጆሮአችንና ልባችንን ለባጢልና ቢድዓ ደሞ ጀርባችንን እንስጥ!

☞አመት ጠብቀህ መልእክተኛውን እወዳለሁ እያልክ ከሴት ጋር ተቀላቅለህ እየጨፈር ከምትረብሽ ሱናቸው ሲረሳ ቢድዓ ሲነግስ ጀግና ሁን።

"إنا كفيناك المستهزئين"


(ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሀል)

[ሱረቱ'ል ሒጅር :(95)]


ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ

https://t.me/abdurezaq27