Get Mystery Box with random crypto!

ሁለቱ ገጣሚ ሚስቶች # الزوجتان الشاعرتان # يُحكى أنه كان لأعرابي | 📚ፈዋኢድ እና ፈራኢድ📚

ሁለቱ ገጣሚ ሚስቶች

# الزوجتان الشاعرتان #

يُحكى أنه كان لأعرابي زوجتان فولدت إحداهما ولداً والأخرى بنتاً،

☞ሰዎች ዘንድ የሚተረክ ታሪክ ነበረ እሱም ፦

አንድ አዕራቢይ ሁለት ሚስቶች ነበሩት። አንደኛዋ ወንድ ልጅ ስትወልድ ሌላኛው ሴት ልጅ ወለደችለት።

فكانت أم الولد تحمله وترقص به أمام ضرتها لتغيضها وتقول:

ወንድ የወለደችው ሚስቱ ወንድ ልጇን ተሸክማ ጣውንቷ ፊት ለፊት ሆኖ ልጇን እያጫወተችና እየተወዛወዘች ትቦርቃለች። ሴት ወላዷን ለማናደድም እንዲህ እያለች ትገጥም ነበር

الحمد لله الحميد العالي
أكرمني ربي وأعلى حالي
ولم ألد بنتاً كجلدٍبالي
لا تدفغ الضيم عن العيال.

ከፍ ላለው አላህ ምስጋና ይገባው
ክብሬን ደረጃዬን እጅግ ከፍ አረገው
ሴትን አልወለድኩ እንደ ብስብስ ቆዳ
ከቤተሰቦቿ በደል መከራን ማታፀዳ

فاغتاضت أم البنت وراحت تشكوا ضرتها إلى زوجها ،فقال لها كلمة بكلمة، قولي لها: مثل ماتقول،

ሴት የወለደችው ሚስቱ ይህን የሰማች ግዜ በጣም ተናደደች። ለባሏም ስሞታ ልታቀርብ ሄደች። ይህን ግዜ ባሏ "እሷ እንዳለችሽ አንቺም በያት!" አላት።

فنظمت أم البنت أبياتاً وأصبحت ترقص بإبنتها وتقول:

የሴቷ እናትም እንዲህ የሚል ግጥም እየገጣጠመች ልጇን ይዛ መወዛወዝ ጀመረች።

وما علي أن تكون جارية
تغسل رأسي وتراعي حالية
وترفع ماسقط من خمارية
حتى إذا ما أصبحت كالغانية
زوجتها مروان أو معاوية
أصهار صدقٍ ومهورغالية.

ሴት ብትሆን እኔ ምን ገዶኝ
ፀጉሬን ምታጥብ ምታሰናዳኝ
የወደቀ ሻርፔን አንስታ ምትሰጠኝ
ውበቷ ደምቆ እጅግ ስታማልል
መርዋን ወይም ሙዓውያ ያገቧታል
የእውነት አማቾች መህሯ ይወደዳል

فشاعت أبياتها في الناس،
ولما كبرت البنت قال الأمير مروان بن الحكم : أكرم بالبنت ولاتُخيب ظن الأم ،
فخطب البنت وقدم لها مئة ألف درهم مهرا.

ይህ የሴቷ እናት ግጥም በሰዎች መሀል በጣም ተሰራጨ። ልጅቷ ያደገች ግዜ አሚር የነበረው መርዋን ኢብኑል ሐከም "የእናቷን ምኞት ከንቱ አላረግም!" ብሎ ልጅቷን አጭቶ አገባት። አንድ መቶ ሺህ ዲርሀም መህርም ሰጣት።

فلما علم _ معاوية ابن أبي سفيان- بالأمر قال: لولا أن مروان سبقنا إل
يها لضاعفنا لها المهر،ثم بعث للأم بمئتي ألف درهم هبة من عنده.

ሙዓውያም ይህን ታሪክ ሲሰማ "መርዋን ባይቀድመኝ ኖሮ ከሰጣት መህር በላይ እጥፍ አርጌ አገባት ነበር!" አለ። ከዛም ለእናትየው ሁለት መቶ ሺህ ዲርሀም ስጦታ ብሎ ላከላት።

≅ምንጭ


# فوائد ..... من كتاب،
"# لطائفـ المعارف#"
لإبن رجب الحنبلي رحمه الله


ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ

https://t.me/abdurezaq27