ናፍቆቱ አሰከረን የጦይባው ኢማሙ: ጀሊሉ ሲልከው ብሎ ለአለሙ: በናፍቆት ተከዘ እኔን ቢናፍቀኝ : ከሱም በለጠና ወንድም ብሎ ጠራኝ: ይሄን እየሰማ ልቤ ተሸበረ : በናፍቆት ሰረገላ ከረውዳው በረረ: የነብዬን ሀገር ሙላውን አሰሰው: ሁቡም አይበርድልኝ በእግር ካልረገጠው: ሙሀባና ፍቅርን አንብበን ተረዳነው: በነብዬ ፍቅር በተግባር አየነው: ቀይስም ተቃጠለ በለይላ ፍቅር: ያንቱ ናፍቆትማ ወዳጅን ሚያሰክር: አንድ ጊዜ ታላዬት መቼም የማይበርድ: አንለምንሀለን የአለሙ ጌታ ገፉሩል ወዱድ: ነብዬን በመናም ሁሌም እንድታሳየን: ከረውዳቸው ጓዳ መዲና እንድትወስደን: ሰላት እና ሰላም በአንቢያኦች ኢማሙ: እሱን ለተከተሉ ላሉት በአለሙ: ሰላም ይውረድ በወንድሙም ሙሳ: ከግፈኞች የታገለ የአላህ አንበሳ: ኡመት አርገኝ ብሎ ቀን ከሌት ለመነ: በኛው ነቢ ፍቅር ልቡ መነመነ። #ቀሚስ_ያለው_ኸሚስ!!!! @abduftsemier @abduftsemier 284 viewsAbdu Emre (አብዱ ኤምሬ), edited 19:56