Get Mystery Box with random crypto!

#የሰይዱና_ኸድር_ቅዳሜ በአንድ ወቅት አንድ የአላህ አገልጋይ ነበር አንድ ጊዜ ያያቸ | Abdu ft hasu 🎤🎤

#የሰይዱና_ኸድር_ቅዳሜ

በአንድ ወቅት አንድ የአላህ አገልጋይ ነበር አንድ ጊዜ ያያቸውን ሰይዱና ኸድር አ.ሰ እንደገና ለማየት ፍላጎት ነበረው "ያ ረቢ ሰይዲ ኸድርን በድጋሚ አሳየኝ" እያለ ቀን ከለሊት ዱኣ ያደርግ ነበር ከዚያም ለሰይዱና ኸድር በነበረው ፍቅር የተነሳ አእምሮውን አጣ ለበርካታ አመታት በተራራና በሜዳ ተንከራተተ ከብዙ ጊዚያት ቡሀላም አእምሮ ተመለሷለት ወደ ትውልድ ሀገሩ አቀና ነገር ግን ሰይዱና ኸድር አሁንም አልመጡም አንድ ቀን ለሊት አንደገና መፀለይ ጀመረ "ያረቢ ለብዙ አመታት የሆንኩትን ነገር ተመልከት ለኸድር ባለኝ ፍቅር አእምሮዬን አጣሁ በበርካታ ቦታዎች ተንከራተትኩ ያረብ ሰይዱና ኸድር ለአንድ ጊዜ ብቻ አሳየኝ" እያለ አለቀሰ ብዙም ሳይቆይ ሰይዱና ኸድር ፊቱ ላይ ተገለጡለት ምስኪኑ ያአላህ ባሪያም ደነገጠ "እኔን ለማየት ወደ አላህ ፀለይክ ምን ትፈልጋህ" ሲሉ ጠየቁት "ሰይዲ ኸድር ሆይ አንደዚህ በቅፅበት መምጣት እየቻሉ ለምን አመታት እንድጠብቅ አደረጉኝ ባንቱ ፍቅር አእምሮዬን አጣሁ በተራራው በሜዳው ዞርኩ" አለ ሰይዱና ኸድርም መጎናፀፊያቸውን በሰውዬው ትከሻ ላይ አደረጉ ኮፍያቸውንም ራሱ ላይ አደረጉለት "አሁን አንተ ኸድር ነህ ወደ ገበያው ቦታ ሂድ ሁሉም ሰው ይይህ" አሉት ሰውዬው ኸድር ሲሆን የአይን መጋረጃው ተገለጠ ወደ ገበያው ስፍራም ሄደ ገበያው ስፍራ ሲሄድ ያየው ግን የተለየ ነበር ውሻ:ጅብ:ሸረሪት:እስስት... ብዙ እንስሳዎችን አየ (ውሻ መስለው የሚታዩት ውሸታሞች ጅቦቹ ደግሞ አጭበርባሪዎች እስስት መስለው የሚታዩት አስመሳዬች ሸረሪት የመሰሉት ደግሞ ሌቦች ሰዎች ነበሩ) ከዛም አንድ ሽምግሌ አየ ፂሙ ከነጭ ላይ የነጣ ነበር ወደ ሽማግሌው ሄዶ "ሽማግሌው እኔ ኸድር ነኝ ምኞት አሎት" ሲል ጠየቀ አዛውንቱ እያዩት "ልጄ አንተ የራስህን ስራ አከናውን ኸድር ሲያስፈልግኝ ወዳንተ እመጣለሁ"።

*አለም ላይ ያሉ ነገሮች ሁሉ ቢኖርህ ሁሉንም የሰጠህ አላህ ነው!
*የሚያስፈለግህን ነገር ባስፈለገህ ጊዜ ብቻ ጠይቅ!
*ሰይዲ ፈልገነዎታል ፈልጉን!

@abduftsemier
@abduftsemier