Get Mystery Box with random crypto!

Abdu Book Center

የቴሌግራም ቻናል አርማ abdubook — Abdu Book Center A
የቴሌግራም ቻናል አርማ abdubook — Abdu Book Center
የሰርጥ አድራሻ: @abdubook
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 446
የሰርጥ መግለጫ

በመጻሕፍት መደብራችን ፡
የታሪክ መጻሕፍት
የትምህርት አጋዥ እና መማሪያ መጻሕፍት
የተለያዩ ልበ-ወለድ እና ኢ-ልበወለድ መጻሕፍት
ቆየት ያሉና አዳዲስ መጻሕፍት ሌሎችም..
አድራሻችን=አዲስ አበባ ፒያሳ የምኒልክ ሀዉልት ፊቱ ባዞረበት በኩል ፊት ለፊቱ ባስ እስቴሽኑ 50ሜትር ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ በ0929574133 ደዉልሉን
@Abduseller

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-02-02 18:09:32
«ካፖርቱ»፣«የመጨረሻዉቅጠል»እና« ሽማግሌዉና ባህሩ» ከረጅም ጊዜያት በኋላ በአንድ ላይ ተጠቃለዉ ለገበያ ቀርበዋል
https://t.me/Abdubook
68 viewsAbdu Book Delivery, edited  15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 22:21:07
በኢትዮጵያ የግማሽ ክፍለ ዘመን የታሪክ ባልተቤት የሆኑት ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ታሪክ በሰፊዉ ከሚያትቱ መጻሕፍት ከብዙ በጥቂቱ

ሁሉንም በመጻሕፍት መደብራችን ያገኝዋቸዋል

https://t.me/Abdubook
115 viewsAbdu Book Delivery, 19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 08:03:20 ሰላም ዉድ የቻናላችን ቤተሰቦች በግሩፓችን የምንለቃቸዉ መጽሐፍቶችም ሆነ ከዛ ዉጭ ያሉ ማንኛዉንም ዘዉግ ያላቸዉ መጻሕፍት መሸመት ካሻዎት
በዚህ @Abdu_Book_seller
ያናግሩኝ
112 viewsAbdu Book Delivery, edited  05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 19:46:55
➾ሰዎች የበለጠ ስልጣን ባላቸዉ ቁጥር ያ.. ቦታ እንደሚገባቸዉ ለማረጋገጥ የበለጠ ችግር ዉስጥ ይገባሉ፡፡ በራሳቸው ላይ ምንም ጥርጣሬ እንዳይኖራቸዉ ሲሉ ``ሲልኩት አቤት ሲጠሩት ወዴት`` የሚባሉ አይነት ጭፍሮችን በዙሪያቸዉ በማሰለፍ የማያባራ ሙገሳና አዎንታዊ ማረጋገጫን ማየት ይሻሉ!

#Dale Carnegie

https://t.me/Abdubook
119 viewsAWSA❶2❹ሺ , edited  16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 17:15:15
"ህመሜን በትግስት ሜዳ ላይ ስተክል የደስታ ፍሬ ወለደች ።"

⁽ካህሊል ጂብራን⁾

https://t.me/Abdubook
108 viewsመናኙ ባተሌ, edited  14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 07:04:52
ብዙዎቻችን ገንዘብ ለማግኘት ቀን ከሌት እንባዝናለን...እንለፋለን...እንባትላለን....እንከራተታለንም ግና ስለምንባዝንለት ገንዘብ ምንነት በቂ ግንዛቤ የለንም።ኧረ እንደዉም እስከነ ጭራሹ አናዉቀዉም።

ስለገንዘብ ምንነት ሳናዉቅ ስለገንዘብ አያያዝ እንማራለን።ይህንን ክፍተታችን ለመድፈን በሚል እሳቤ በወንድም #አብዱልቃድር_ኑረዲን የተዘጋጀዉ «ፊያት፣ገንዘብና ወለድ» የተሰኘዉ መጽሐፍ ጥቂት ቅጂዎች መጋዘን ስናገለባብጥ ለማግኘት ችለናል።ስለሆነም መጽሐፉን በእጃችሁ ያላስገባችሁ ተደራሲያን ፒያሳ ጊዮርጊስ ፊትለፊት ወደ አገር ፍቅር በሚያስወርደው ቀጭኑ መንገድ በሚገኘዉ መደብራችን ጎራ በማለት መሸመት ትችላላችሁ።

‍አሊያም ያላችሀበት ቦታ እናደርስላችኋለን።


https://t.me/Abdubook
107 viewsአፍን ዘግቶ ፉጨት, edited  04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 21:44:41 #ሁላችንም ሃሳብ አለን፣ ግን ሃሳባችን ዋጋ ያለው አይመስለንም። ሁልጊዜም ከእኛ የተለየዩ፣ ከእኛ የተሻሉ "አሳቢዎች" አሉ ብለን ማሰብን ለማናውቃቸው "ሌሎች" እንተወዋለን። ወይም "ማሰብ" ምሁራን የሚባሉ ሰዎች ብቻ ስራ ነው ብለን፣ ላሉብን ችግሮች አንድ መፍትሄ አምጥተው እስኪሰጡን አፍ አፋቸውን እያየን እንጠብቃለን።

#እያንዳንዱ ሰዉ ዋጋ አለዉ። የራሱ ብርሃን አለዉ፤ ለሌላው የሚያበራ። አንዳችን ለአንዳችን የምናበራበትን አለም መፍጠር ይቻላል። ሁል ጊዜ አንዳችን ለአንዳችን የጨለማ ምንጭ መሆን አይጠበቅብንም።"

#የራሳችን ዋነኛ ጠላት ራሳችን ነን።  ስለራሳችን የማናውቀውን ማወቅ ያስፈራናል። በመሆኑም በተቻለን መጠን ስለራሳችን ማወቅ በፈለግን ቁጥር በየትኛውም መንገድ ያንን ለማዘግየት እንጥራለን። ... በህይወታችን ሙሉ የምንዋጋው ትልቁ ጦርነት ይኸው ነው - ራስን የማወቅ ጥቃት!....

#ህልምም ይሁን እውን የገጠመንን ሁሉ፣ ከልጅነት እስከ እውቀት የሆነው ሁሉ፥ በአእምሮአችን ጓዳ አለ፤ የምናስታውሰው ግን በጣም ጥቂቱን ነው። ብዙውን ማስታወስ አያስፈልገንም። የግድ የምናስታውሰው ግን ለጊዜው በሠላምና በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ለመቆየት የሚበቃንን ያህል ነው።

#ሰዉ መሆን በጣም ይደንቃል።
ሰዉ መሆኑን የረሳ ሰው፥ ወንድ መሆኑን ሲያስታውስ ግን አይደንቅም?

ሰዉ መሆኑን የረሳ ሰዉ፥ ነጭ ወይም ጥቁር መሆኑን ሲያስታውስ አይደንቅም?

መሬት ላይ የተፈጠረ ሰዉ፥ መሬትን ረስቶ ሀገሩን ሲያስታውስ አይደንቅም?

መግባቢያ ቋንቋ እንዳለዉና ይህም ደግሞ ከየትኛውም ፍጡር እንደሚለየዉ ረስቶ ፥ መናገሪያዉን ማስታወሱ አይደንቅም?
https://t.me/Abdubook
97 viewsመናኙ ባተሌ, 18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 18:04:06
በጉጉት ስትጠብቁት የነበረዉ መ‒ገንዘብ የተሰኘዉ #የአብዱልቃድር_ኑረዲን መጽሐፍ በመደብራችን አስገብተናል።

መጽሐፉ የምዕራቡ አለም ዓለምን እንዴት በካፒታሊዝም የኢኮኖሚ ስርዓት ተብትቦና ጠርንፎ እንደያዘ ብትንትን አድርጎ ያፍታታልናል።የፋይናንስ ስርዓት ደም ስር ስለሆነዉ#ገንዘብ ከጥንስሱ ማለትም ከአባታችን አዳ(ደ)ም እስከ ዘመናችን ያለፈበትን የእድገት ደረጃዎች በሰፊዉና በጥልቀት ይዳስሳል

መጽሐፉን ወደመደብራችን ጎራ ብለዉ ይሸምቱ! አለያም ይዘዙን ያሉበት ቦታ እናደርስሎታለን። ክፋላተ ሀገራትና ዉጭ ሀገራት ያላችሁ ደግሞ እንደየምርጫችሁ እንልክላችኋለን።

አድራሻችን=አዲስ አበባ «ፒያሳ ምኒልክ አደባባይ »
ወደ ሀገር ፍቅር የሚያስወርደዉ ቀጭኑ መንገድ ጤና ጣቢያዊ ፊትለፊት

https://t.me/Abdubook
114 viewsAWSA❶2❹ሺ , edited  15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 16:11:03 ከራስህ ስህተት ስትማር ልምድ ይባላል፤ ከሰዎች ስህተት ስትማር ደግሞ ጥበብ ይባላል።

ማንበብ የሚጠቅምህ የሌሎችን ስህተት እንዳትደግም ስለሚረዳህ ነው። ወዳጄ በቀን ውስጥ አንድ መስመር አሊያም አንድ ገፅ ቢሆንምኳ ሳታነብ እንዳትቀር!

https://t.me/Abdubook
135 viewsመናኙ ባተሌ, 13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 10:11:16
የ 19ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ መጽሃፍ
French classic
የፈረንሳያዊዉ ጸሀፍት ቪክቶር ህዩጎ«ሌይ ሚዘራብል» የተሰኘዉ መጽሐፍ በሀገራችን ሁለት ጉምቱ ተርጓሚ ወ_ፀሀፍቶች ተተርጉሞ ቀርበዉላችኋል

የኋንስ ገ/ፃዲቅ «ምንዱባን» የሚል ርዕስ ሰጥተዉ ሲተረጉሙት

ሳህለስላሴ ብርሀነ ማርያም ደግሞ «መከረኞቹ»የሚል ርዕስ ሰጥተዉ ተርጉመዉታል
152 viewsመናኙ ባተሌ, 07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ