Get Mystery Box with random crypto!

ዓባይ ኤጀንሲ Abay Agency

የቴሌግራም ቻናል አርማ abayagency — ዓባይ ኤጀንሲ Abay Agency
የቴሌግራም ቻናል አርማ abayagency — ዓባይ ኤጀንሲ Abay Agency
የሰርጥ አድራሻ: @abayagency
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.84K
የሰርጥ መግለጫ

ዓባይ ኤጀንሲ Abay Agency
ዘመናዊና ፕሮፌሽናል ግብይቶች እንዲካሄዱ አስፈላጊ መረጃዎችን ለገዥና ለሻጭ በማድረስ የተሳለጠ የገበያ ሥርዓት እንዲፈጠር ይሠራል፡፡ የምንሠጣቸው አገልግሎቶች፡
 የቤትና የሕንፃ ሽያጭና ኪራይ
 የባንክና ሌሎች የንግድ አክሲዮኖች ሽያጭ
 የመኪና ሽያጭና ኪራይ
 ለመረጃ ☎️ 0911248597 ይደውሉ፡፡
አድራሻ፡ መገናኛ ደራርቱ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 226

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-16 07:06:44
የሚሸጥ ቤት አዲስ አበባ ፣አየር ጤና
**************** ********
የሚገኝበት ቦታ፡ አዲስ አበባ፣አየር ጤና
ሥፋት በይዞታ 460 ካሬ ሜትር
40 ሜትር አሥፓልት የያዘ
ዋጋ: 15,000,000
************************
ለማንኛውም የቤት/ሕንፃ ግዥና ሽያጭ መረጃዎች ይፃፉልን/ይደውሉልን፡፡
ሥልክ፡ 0985055053
0918040000
ቴሌግራም፡ https://t.me/abaysalesagent
ኢሜል፡ abayengineeringpm@gmail.com
*************************
ያሉንን የቤት፣ሕንፃና መጋዘን ሽያጭ/ግዥ/ኪራይ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራምና የፌስቡክ ገፆቻችንን ይከታተሉ!
https://t.me/ethiohomesolutions
https://www.facebook.com/ethiohomesolutions
አድራሻችን፡ መገናኛ ደራርቱ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 226
590 views04:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:23:55
አዲስ አበባ ሰሞኑን የወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውደቅ ተደረገ!

ሐምሌ 6፣ 2014 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 1 ቀን 2014 ያወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ውድቅ አደረገ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ባሳለፍነው ሐምሌ 1 ቀን 2014 የወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውድቅ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ዕጣው የተሰረዘውም የከተማ አስተዳደሩ ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓቱ በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ሲጀመር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነት መኖሩ በመረጋገጡ ነው ተብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 01 ቀን 2014 በወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የዳታ ማጭበርበር ድርጊት በመከሰቱ ሁኔታውን እያጣራ እንደሚገኝ እና በድርጊቱ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሆነ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
መረጃው የኤፍ ቢ ሲ ነው፡፡
715 views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 22:48:41 ሀምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ይመለከታል::

በከተማችን አዲስ አበባ ከሚስተዋሉ ችግሮች መካከል አንዱ የቤት አቅርቦት እጥረት ሲሆን ይህንኑ ደረጃ በደረጃ ለማቃለል አስተዳደሩ የተለያዩ አማራጮችን ነድፎ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የዚህ ሂደት አካል የሆነው የነባሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉበትን ወስብስብ ችግር ለይቶ በመፍታት ተመዝጋቢዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ እና የቤት እጥረት ጫና ለመቀነስ የተደረገው ሰፊ ጥረት ተጠቃሽ ነው፡፡
በዚህ ሂደት በግንባታ ላይ የነበሩ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል 25,491 ያህሉ በቅርቡ ለባለ እድለኞች የዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት መካሄዱ ይታወቃል፡፡

ይህ የቤት ማሰስተላለፍ ስራ እንደ ከዚህ በፊቱ በቆጣቢወች መካከል አድሎና ብልሹ አሰራር እንዳይኖር ለማድረግ ግልፅነት በሚያሰፍን አግባብ ለማስተላለፍ ሲባል በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራ በመስራት ሂደቱን ግልጽና አሳታፊ ለማድረግ የተደረገው ተነሳሽነትና ጥረት እንዲሁም የባልሙያዎችን ሙያዊ ነፃነት አክብረን አስፈላጊውን ሂደት ተከትለን ተዓማኒነቱን እንዲያረጋግጡልን አድርገን ነበር:: በዚህ ሂደት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ አዲስ ሶፍትዌር እንዲበለፅግ እና ስለሶፍትዌሩ ታአማኒነት የኢኖቬንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር እንዲያረጋግጥልንም ተደርጓል::
በቀጣይም ከሁለት ጊዜ በላይ ታዛቢወች እና ባለሙያወች ፊት ቀርቦ እንዲያረጋግጡልን ተደርጎ ማረጋገጫ ሰጥተዋል::
ይህ ሁሉ ሂደት ከእለት ጉርሱ የቆጠበዉን እና በከፍተኛ ጉጉት የሚጠባበቀውን ሕዝብ በፍትሃዊነት ተደራሽ ለማድረግ ቀና ሃሳብ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል::
ይሁን እንጂ ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ስንጀምር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች ተግኝተዋል::
በመሆኑም በእስካሁኑ የማጠራት ስራ ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል፡፡

ከዚህ በመነሳትም የቤት ማስተላለፉን ሂደት ግልፅነት ለማስፈን ሲባል እና ውጤቱን የሚያዛባ ተግባር ሲያጋጥም መልሰን ኦዲት እንዲደረግ በገባነው ቃል መሰረት የተፈጠረውን ችግር ከጉዳዩ ገለልተኛ በሆኑ በሚመለከታቸው ተቋማት የማጣራት ስራ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በጉዳዩ የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገ ይገኛል::

ስለሆነም ሂደቱን በአጭር ጊዜ አጠናቀን ለቤት ተመዝጋቢዎችና ለመላው የከተማችን ነዋሪ የምናሳውቅ መሆኑን ስንገለጽ ተመዝጋቢዎች እንደተለመደው በከፍተኛ ትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን፡፡

ለተፈጠረው ስህተት የከተማ አስተዳደሩ በዚህ አጋጣሚ ይቅርታ ይጠይቃል
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ሐምሌ 4/2014 ዓ/ም
746 views19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 10:31:41
3ኛ ዙር የ40/60 እና 14ኛ ዙር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ስነስርኣት እየተካሄደ ነው።

አጠቃላይ 25 ሺህ 491 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለነዋሪዎች በዕጣ ይተላለፋሉ።

በ20/80 ፕሮግራም 18 ሺ 648 ፤ በ40/60 መርኃ ግብር 6 ሺህ 843 ቤቶች በድምሩ 25 ሺህ 491 ቤቶች ለነዋሪዎች በእጣ ይተላለፋሉ።

በዕጣው የሚካተቱት በ1997 እና በ2005 ዓ.ም ተመዝግበው እስከ የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በአማካይ ለ60 ወራት የቆጠቡ የ20/80 እና 40 በመቶ እና ከዚያ በላይ የቆጠቡ የ40/60 ቤት ፈላጊዎች ናቸው።

79 ሺ 794 ከሚሆኑ ቤት ፈላጊዎች መካከል 25 ሺህ 491 የሚሆኑት ዕድለኞች በነገው የዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት ይለያሉ።

በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ለባለዕድለኞች የሚተላለፉ ቤቶች የሚገኙት አያት 2፣ ቦሌ በሻሌ፣ ቡልቡላ ሎት ነው።

በ20/80 ለባለዕድለኞች የሚተላለፉ ቤቶች የሚገኙት በረከት፣ ቦሌ አራብሳ ሳይት 3 ሳይት 5 እና 6 ወታደር፣ የካ ጣፎ፣ ጀሞ ጋራ፣ ጎሮ ስላሴ ፣ ፉሪ ሀና እና ፋኑኤል ነው።

የመንግስት ሰራተኛ 20 በመቶ ፣ ሴቶች 30 በመቶ ፣ የአካል ጉዳተኞች 5 በመቶ በእጣው ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።
908 views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 10:22:41
677 views07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ