Get Mystery Box with random crypto!

በባሕር ዳር ከተማ ውስጥ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም የተንቀሳቀሱ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአ | (ABC) Amhara Broadcasting Corporation

በባሕር ዳር ከተማ ውስጥ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም የተንቀሳቀሱ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያና ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር መሰረት ደባልቄ በሰጡት መግለጫ÷ "በሀገሪቱና በክልሉ ሕግ ለማስከበር እየተንቀሳቀስን እንገኛለን" ብለዋል፡፡
ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ምሽት ኅብረተሰቡን ለማሸበር ያለመ ወንጀል ለመፈፀም የፈለጉ ቀሪ ኀይሎች በባሕርዳር ከተማ በአራት ቦታዎች ላይ ቦንብ እንዳፈነዱ ገልጸዋል።
ፖሊስ ከሕዝብ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ክትትልም ወዲያውኑ 6 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር አውሏል ነው ያሉት።
የተጠርጣሪዎች ቤት በሚፈተሽበት ወቅትም 2 ቦንብ፣ 3 ብሬን መሳሪያ እና 3 ሺህ 700 ጥይት፣ አንድ ስናይፐርና 500 ጥይት እንዲሁም በቀጣይ ተመሳሳይ የሽብር ወንጀል ለመፈፀም የያዙትን እቅድና መመሪያ ፖሊስ መያዙን ኮማንደር መሰረት ተናግረዋል።
በዚሁ ምሽት ከዚሁ ሽብር ጋር ግንኙነት ያላቸው 14 ተባባሪ አካላት በቁጥጥር ስር ውለው የክልልና የፌዴራል የፀጥታ አካላት ምርመራ እያደረጉ ይገኛሉ ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።በባሕር ዳር ከተማ ውስጥ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም የተንቀሳቀሱ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

በዚሁ ምሽት ከዚሁ ሽብር ጋር ግንኙነት ያላቸው 14 ተባባሪ አካላት በቁጥጥር ስር ውለው የክልልና የፌዴራል የፀጥታ አካላት ምርመራ እያደረጉ ይገኛሉ ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል። https://t.me/JournalistNetsanetGetachew