Get Mystery Box with random crypto!

የምሁራን ሚና በአገር ግንባታ ላይ በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውይይት መድረክ እየተካሄ | Abrehot Library

የምሁራን ሚና በአገር ግንባታ ላይ በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

እየተካሄደ ያለው ውይይትም ለአራት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ምህረት ደበበ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በተገኙበት የሁሉም ኮሌጆች የካውንስል አባላት መምህራንና የአስተዳደር ኃላፊዎች የሚሳተፉበት ይሆናል፡፡

ስብሰባው የሚመሩት የኢፌዲሪ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት የተከበሩ አቶ አህመድ ሽዴ ናቸው።

በስብሰባዉ ላይ አገራችን አሁን ያለችበትን ሁኔታና ከሰላም ስምምነቱ አንፃር በጋራ ውይይት ማዳበር የሚገባ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን በዚህም ሂደት ውስጥ የምሁራን ሚና ከፍተኛ አስተዋፆ እንደሚኖረው ተገልፀጿል ።