Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ዪንቨርስቲን ጨምሮ የአፍሪካ የምርምር ዩንቨርስቲዎች ጥምረት (ARUA) እና የአውሮፓ | Abrehot Library

የአዲስ አበባ ዪንቨርስቲን ጨምሮ የአፍሪካ የምርምር ዩንቨርስቲዎች ጥምረት (ARUA) እና የአውሮፓ የምርምር ዩንቨርስቲዎች ጥምረት (Guild) የምክክር ጉባኤ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን እተካሄደ ነው፡፡

የአፍሪካ የምርምር ዩንቨርስቲዎች ጥምረት (ARUA) እና የአውሮፓ የምርምር ዩንቨርስቲዎች ጥምረት (Guild) የምክክር ጉባኤ ዛሬም በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን እተካሄደ ይገኛል፡፡

በተለይ በፈጠራና ቴክኖሎጂ ላይ አጀንዳ አድርገው ተወያይተዋል፡፡

ይህ ወሳኝ ጉባኤ የምርምር የልቀት ማእከላትን በቡድን ማቋቋምና ማጠናከር ላይ ትኩረት አድርጎ ተወያይቷል፡፡

ይህም የደቡብ-ደቡብ (South-South) እንዲሁም የሰሜን-ደቡብ (North-South) ግንኙነትን ታሳቢ አድርጎ የሳይንስ ልቀት ትብብር ስለመመስረት፣ የምርምር ልቀትን ስለማጠናከር ውይይት ተካሂዷል፡፡

በዚህም ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣት ተመራማሪዎች ሳይንሳዊ እድገትና የምርምር ክህሎት የሚያሳድግ፣ ለከፍተኛና መሪ ተመራማሪዎችም ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት ከፍተኛ የምርምር ተቋማትን ስለመገንባትም ውይይቱ ዳስሷል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ፣ ተደራሽና አካታች የሳይንስና ቴክኖሎጂ የምርምር ተቋማትን በአውሮፓ ኅብረትና በአፍሪካ ኅብረት ድጋፍ ማጠናከርና በድኅረ-ምረቃ (ማስተርስና ዶክትሬት ዲግሪ) ፕሮግራሞች የአውሮፓ- አፍሪካ ተማሪዎች ግንኙነትን ማጠናከርም የጉባኤው ተሳታፊዎች ያነሷቸው ነጥቦች ናቸው፡፡