Get Mystery Box with random crypto!

አአዩ በደቡብ አፍሪካ፣ ኬፕ ታውን እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ የምርምር ዩንቨርሲቲ ኅብረት የጋራ | Abrehot Library

አአዩ በደቡብ አፍሪካ፣ ኬፕ ታውን እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ የምርምር ዩንቨርሲቲ ኅብረት የጋራ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

በጋራ ጉባኤው ላይ የአባል ዩንቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶች፣ ቻንስለሮችና የልቀት የምርምር ተቋማት ዳይሬክተሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ጉባኤው የቅድሚያ ትኩረት በሰጠባቸው የምርምር አጀንዳዎችና በስልታዊ እቅዱ አፈጻጸም ላይ እየተወያየ ይገኛል።

የአሩዋ (የአፍሪካ የምርምር ዩንቨርስቲዎች ጥምረት) ተልዕኮ የአፍሪካ ተመራማሪዎችና የምርምር ተቋማት በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻል፣ በሚፈጥሩትና በሚያሰራጩት አዳዲስ የምርምር እውቀትም የአፍሪካን ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ማገዝ ነው።

የአፍሪካ የምርምር ዩንቨርስቲዎች ጥምረት አባላት የሚከተሉት ናቸው።

Member Universities

• Addis Ababa University, Ethiopia
• University of Lagos, Nigeria
• University of Ibadan, Nigeria
• Obafemi Awolowo University lle-Ife, Nigeria
• University of Ghana, Ghana
• University of Dar es Salaam, Tanzania
• University of Nairobi, Kenya
• University of Cape Town, South Africa
• University of the Witwatersrand, South Africa
• University of Rwanda
• University Cheikh Anta Diop, Senegal
• Makerere University, Uganda
• University of Stellenbosch, South Africa
• University of Pretoria, South Africa
• Rhodes University, South Africa
• University of Kwa-Zulu Natal, South Africa