Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ሊፈርስ ነው በሚል የሚሰ | Abrehot Library

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ሊፈርስ ነው በሚል የሚሰራጨው መረጃ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ካሉት ኮለጆች አንዱና ግንባር ቀደም የያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ነው፡፡ ሆኖም አንዳንድ አካላት በተለያዩ የሚዲያ ገፆች ላይ የተሳሳተ መረጃዎችን በተደጋጋሚ በማሳራጨት በሕብረተሰቡና በተማሪዎች ላይ ውዥብር ለመለፍጠር ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

በዚህ ሰሞን አንጋፋው የሙዚቃ ትምህርት ተቋም የሆነው ያሬድ ት/ቤት ሊፈርስ ነው የሚል መረጃ በማሰራጨት በሕዝቡ ውስጥ ውዥንብር በመፍጠር ላይ ይገናሉ ፡፡

ነገር ግን በምህርት ቤቱ በኩል ምንም የተፈጠረም ሆነ የተለየ ነገር አለመኖሩን እያሳወቅን ሕብረተሰበ በተደጋጋሚ የበሬ ወለደ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን በማጋለጥ የበኩሉን እንዲወጣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት