Get Mystery Box with random crypto!

ስሟን ቀይሩላት @ሀይማኖት(የዲማው) ያኔ ልጅ እያለን፥ የቃላትን ትርጉም ሲያስረዱን የኔታ ሆሄ | ግጥም በማሙሽ እና ሀይማኖት

ስሟን ቀይሩላት

@ሀይማኖት(የዲማው)

ያኔ ልጅ እያለን፥
የቃላትን ትርጉም ሲያስረዱን የኔታ ሆሄ ሲያስተምሩ፣
ማፍረስ ማደፍረስ ነው የ "ኢ" ፊደል ግብሩ፣

ቀድሞ እየተገኘ፥
መልካም የሆኑትን ከአቻ ትርጉማቸው እንዳደፈረሰ፣

"ኢ" የሚሉት ፊደል ከሆሄነት አልፎ ሀገር አፈረሰ፣
ሰላም በምድሯ ላይ፥
ፍትህ፡ፍቅር፡ስኬት ሁሉ እንዲሰምርላት፣
ቶሎ ምከሩና (ኢ)ትዮጵያ ሚለውን ስሟን ቀይሩላት፣

ማዕበል ያየለ
ችግር የበረታ በሆነው ባልሆነው ሰርክ መደናገር፣
በ "ኢ"ጀምራ ነው ያልፀናች ይቺ አገር።

Join as telegram
@a1hay

@a1hay

@a1hay