Get Mystery Box with random crypto!

በፍጹም አታቁም! ፨፨፨፨//////፨፨፨፨ “አንድ ጊዜ ነገሮችን በቀላሉ የማቆም ልምምድ ከጀመርክ | ሰዋስው/@zsewasw

በፍጹም አታቁም!
፨፨፨፨//////፨፨፨፨

“አንድ ጊዜ ነገሮችን በቀላሉ የማቆም ልምምድ ከጀመርክ ሁኔታው ልማድ ይሆንብሃል” - Vince Lombardi

በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ!
ጠቃሚና ዋጋ ያለው ግብን የምትከታተል ከሆነ፣ የሆነ ጊዜ ላይ ከዚህ በታች ያሉትን ሃሳቦች ማስተናገድህ አይቀርም፡

“ይህ ነገር ካሰብኩት በላይ ከባድ ነው፡፡”
“ለምንድን ነው ይህ ነገር ይህን ያህል ረጅም ጊዜ የወሰደብኝ?”
“ይህ ነገር ወደፊት አልራመድ አለኝ፡፡”
“ይህ ግብ ደጋግሞ እየተበላሸብኝ ነው፡፡”
“ይህንን ነገር መቀጠል የምችል አይመስለኝም፡፡ ምን አስቤ ነው የጀመርኩት?”

“በፍጹም አላቆምም” የሚልን አመለካከት አዳብር፡፡ ተስፋ አለመቋረጥ የአመለካከት ጉዳይ ነው፡፡ ይህም አመለካከት ልታዳብረው የምትችለው አመለካከት ነው፡፡ ይህንን አመለካከት ለማዳበር ከሚረዱህ ልምምዶች መካከል የሚከተሉትን ሃሳቦች ደግመህና ደጋግመህ ለራስህ መናገር ነው፡-

"ነገሮች ሲከብዱብኝ እኔም ከበድ ብዬ በዓላማዬ ጸንቼ እየቀጠልኩ ነው፡፡"
"መንገድን እፈልጋለሁ ወይም እፈጥራለሁ፡፡"
ማንኛውም ችግር መፍትሄ አለው፣ እኔ ደግሞ መፍትሄውን ለማግኘት ብቃቱ አለኝ።
በየቀኑ የሚሰራውንና የማይሰራውን የመለየትን እውቀትና ግንዛቤ እያገኘሁ ነው፣ ይህም ማለት በጥንካሬና በጥበብ እየጨመርኩኝ ነው ማለት ነው፡፡
መሰናክሎች ጊዜያዊ ናቸው፡፡
ከላይ ያሉትን ሃሳቦች ለራስህ ከተናገርክ በኋላ ቆም ብለህ አስብ! እንደገናም ወደፊት ቀጥል!

@zsewasw