Get Mystery Box with random crypto!

ስሉስ ቅዱስ ወደ አብርሃም ቤት የገቡበት እና የአብርሃምን ጥያቄ የመለሱበት ለችግሩ መፍትሔ የሰጡበ | 💖 ዝማሬ መላዕክት 💖

ስሉስ ቅዱስ ወደ አብርሃም ቤት የገቡበት እና የአብርሃምን ጥያቄ የመለሱበት ለችግሩ መፍትሔ የሰጡበት ታላቅ በዓል ነው
እንኳን ለቅድስት ስላሴ ዓመታዊ ክብረበዓል አደረሳችሁ

ስላሴና አብርሃም የሚተዋወቁበት ምስጢር

የአባቱን እና የእናቱን አገር ጥሎ እግዚአብሔርን ተከትሎ
ከወጣ በኋላ በብዙ መከራና ፈተና ላይ እያለ ነበር ያን ሁሉ መከራና ውጣውረድ በእግዚአብሔር ስም ይቀበል ነበር

ዮሐ 15 (14፤ እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ።ብሎ እንደተናገረ ሐዋርያው

እግዚአብሔር አብርሃምን የሚያውቀው እኛን እንደሚያውቀን አይደለም ምን አልባት እኛን የሚያውቀን ስንበላ ስንጠጣ ስንጫወት ስንዝናና ወዘተ ሊሆን ይችላል

እግዚአብሔር አብርሃምን የሚያውቀው ጣዖትን ሰብሮ ከቤተሰቡ ተለይቶ ከካራን ሲወጣ ነው የእንግዳ ቤት ሰርቶ እንግዳ ሲቀበል የእንግዳ እግር ሲያጥብ ነው

በእየቀኑ ኃጢአቱን እያሰበ መስዋዕት ሲያቀርብ ነው

በመጨረሻም ይህን አገልግሎቱን ያየ ሰይጣን እንግዶች ወደቤቱ እንዳይመጡ ሲከለክልበት አብርሃምም ያለ እንግዳ ስለማይመገብ እንግዳ በማጣት አዝኖ ተክዞ ሳለ
እግዚአብሔር በአንድነት በሶስትነት እንግዳ ሁኖ ከቤቱ ተገኝቷል

እግዚአብሔር ወዳጆቹ እንዲያዝኑ አይፈልግም ማንኛችንም እንድንፈተን መከራ እንድንቀበል እንድንጎዳ እንድራብ አይፈልግም

እግዚአብሔር በአብርሃም ህይወት ውስጥ ያደረገውን ታሪክ ያየነው ገደብ የሌለው ፍቅሩን ነው

ሰይጣን ትንሹንጉሥ ጠባቡን በር ሲዘጋው እግዚአብሔር ለአብርሃም ሰፊውን በር ከፈተለት ሰይጣን ትንሹን ነገር ሲያበላሽበት እግዚአብሔር በእጥፍ ባረከው

ይህን ታሪክ ስመለከት አብርሃም ሰይጣን እንኳን እንግዶችን ከለከላቸው የሚል ይመስላል ምክንያቱም ሰይጣን እንግዶችን ባይከለክላቸው ስላሴ ከቤቱ በእንግድነት ላይገኙ ይችላሉ አብርሃም ከስላሴ ጋር በአንድ ማዕድ ተቀምጦ አይመገብም ነበር የይሳቅን ልደት በስላሴ አንደበት አይነገረውም የእግዚአብሔር ሰው መሆን በእራሱ በእግዚአብሔር አንደበት አይነገረውም ይህን ሁሉ ምስጢር አያገኘውም ነበር

በፈተና የጸና የተባረከ ነው የሚለው መጽሐፍ ለዚህ ነው እኛ ሳናውቀው ፈተና ለሌላ ማዕረግ ለትልቅ ክብር እያዘጋጀን ነው አብርሃም በመፈተኑ ለዚህ ታላቅ ክብር በቅቷል እግዚአብሔር ያጽናን

የአብርሃምን ቤት የባረከ እግዚአብሔር የእያንዳንዳችን ቤት ይባርክልን እንኳን አደረሳችሁ