Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ካህን አባት አንድ ትዕግስት የጎደለው ወጣት የንስሀ ልጅ ነበራቸው ።ይህ ወጣት በትንሹም በት | 💖 ዝማሬ መላዕክት 💖



አንድ ካህን አባት አንድ ትዕግስት የጎደለው ወጣት የንስሀ ልጅ ነበራቸው ።ይህ ወጣት በትንሹም በትልቁም ቱግ እያለ፤ሰዎችን ያስቀይም ነበር።ከአንደበቱ ክፉ ቃላቶችን ስለሚያወጣ ከሰው ጋር መስማማት አልቻለም።ትዕግስት ፈፅሞ የለውም።ይህ ነገር እጅግ ያሳሰባቸው አባትም፤ልጁን የሚለውጡበት ዘዴ ሲያወጡ ሲያወርዱ ቆይተው አንድ መፍትሄ ላይ ደረሱ።አንድ ቀንም በቀረጢት ሙሉ ሚስማር ያዙና ልጁን አስጠርተው እንዲህ አሉት“ልጄ ሆይ …ይህን በቀረጢት ያለውን ሚስማር ተቀበለኝ፤ሁሌም ትዕግስት በጎደለህ ጊዜ እና ሰው ባስቀየምክ ቁጥር አንድ ሚስማር የእንጨቱ አጥር ላይ ሰካ” አሉት።ልጁ ምንም ግራ ቢገባውም አባቱ እንዳዘዙት ማድረግ ጀመረ።በመጀመሪያ ሰሞን በጣም ብዙ ሚስማሮችን ሰካ….ቀስ እያለ ግን በቀን እንጨቱ ላይ የሚሰካቸው ሚስማሮች ቁጥር እየቀነሰ መጣ…. እያለ…እያለ….በመጨረሻ ምንም ክፉ ያልተናገረ ቀን አንድም ሚስማር ሳይሰካ ዋለ።ልጁ በጣም ታጋሽ ሆኖ ባህሪው ተስተካከለ ማለት ነው።ይህንንም ለአባቱ አበሰረ።
አባም “ እሰይ ልጄ……አሁን ደግሞ ምንም ያልተናደድክ ቀን እና ክፉ ያልወጣህ ቀን በፊት ከሰካሃቸው ሚስማሮች ውስጥ አንዱን ንቀል” አሉት።ልጁ እንደተባለው አደረገ፤ከቀናት በኋላ ሁሉንም ሚስማሮች ነቅሎ ጨረሰ።ወደ አባም ሄዶ ሚስማሮችን አስረከበ።አባም አንዲህ አሉት
“አየህ ልጄ……አሁን የሰካሃቸውን ሚስማሮች ነቅለህ ጨርሰሃል…..በጣም ታጋሽ ሆነሃል ማለት ነው፤ነገር ግን እስቲ አጥሩን ተመለክት….ፈጽሞ እንደ ድሮው ሊሆን አይችልም፤ሚስማሩ ቢወጣም ተበሳስቷል።ክፉ ንግግርም ልክ እንደ ሚስማር ነው፤ሺህ ጊዜ ይቅር ብትልም፤እንደሚስማሩ ጠባሳ ጥሎ ያልፋል ፤እናም ልጄ……..በህይወት ትዕግስት ይኑርህ…..አንደበትህን ቆጥብ” ብለው አስተማሩት።

-ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤ ከክፉ ፈቀቅ ይበል፥ መልካምንም ያድርግ፥ ሰላምን ይሻ ይከተለውም፤
1ኛ የጴጥሮስ 3:10

-ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ። መጽሐፈ ምሳሌ 18:21

-የጠቢባን ከንፈር እውቀትን ትዘራለች፤ የሰነፎች ልብ ግን እንዲህ አይደለም።
መጽሐፈ ምሳሌ