Get Mystery Box with random crypto!

እንዲህ አይነት መልካም ምክሮች ነገዉን ትልቅ ቦታ ለመድረስ ለሚያስብ ወጣት ስንቅ ናቸዉ። የወጣትነ | ዝንቅ መዝናኛ

እንዲህ አይነት መልካም ምክሮች ነገዉን ትልቅ ቦታ ለመድረስ ለሚያስብ ወጣት ስንቅ ናቸዉ። የወጣትነት እድሜያቸዉን ጨርሰዉ የወጡ ሰዎች ስለወጣትነታቸዉ ሲጠየቁ በአብዛኛዉ ምላሻቸዉ "ምነዉ በተረጋጋሁና ሰዉ የመከረኝን በሰማሁ ነዉ" የሚሉት። እኛ እንኳን በአቅማችን ከአምስት ዓመት በፊት ለነበረዉ ማንነነታችን አንድ ነገር ምከር ብንባል "አትልፋ ይሄ ነገርኮ ጥቅም የለዉም" የምንለዉ አይጠፋም። ወጣትነትን ሁሉም ነገር የሚፈልገዉ የእድሜ ክልል ነዉ። መንግስት ይፈልገዋል። ሱስ ይፈልገዋል። ወላጅ ይፈልገዋል። ፈጣሪ ይፈልገዋል። ኑሯችን ይፈልገዋል። ጨዋታ ይፈልገዋል። ጓደኛ ይፈልገዋል። መዝናናት ይፈልገዋል። ስራ ይፈልገዋል። ቦዘኔነት ይፈልገዋል። ሶሻል ሚድያዎች ይፈልጉታል ወዘተ። ስለዚህ በብዙ ነገር መፈለጋችን የተለየን አድርገን እንድናስብ illusion ይፈጥርብናል። በዚህም በተቻለን አቅም ሁሉንም ለማሳደድ እንሞክራለን። እነዚህ ሁሉ ግን ሁሉም አስፈላጊዎቻችን አይደሉም። አንዳንዱ ሊጠቀምብን አንዳንዱ ሊጠቅመን ነዉ የሚፈልጉት። አሳዛኙ ነገር ይህንን ብዙዎቹ የሚገነዘቡት እድሉ ካለፈባቸዉ በኋላ መሆኑ ነዉ። ዛሬ ላይ ሲታይ ግን የሚያልፍ አይመስልም። ዛሬ ወጣት ስለሆንን መቆም ብንፈልግ እንቆማለን። መሄድ ብንፈልግ እንሄዳለን። መሮጥ፣ መተኛት፣ መስከር፣ አለመስከር፣ መስራት፣ መቦዘን፣ መጣላት፣ ማስታረቅ፣ ማንቋሸሽ፣ ማክበር፣ መፎከር፣ መረጋጋት ወዘተ ብንፈልግ ሁሉም በእጃችን ስለሆነ እንችላለን። ነገር ግን የዛሬ እድሎች ነገ ለመኖራቸዉ ዋስትና አልተሰጠንም። ስለዚህ እድሎቻችንን እንጠቀም። አስተዉለን እንኑር!! የሚማር ካለ የሚያስተምር በየቦታዉ አለ!! ይመቻቹ!

ይቺን የመንሱሬን ምክር ጋበዝኳችሁ።
(ይህኛዉ ቪድዮ Size ለሚበዛባችሁ በኮሜንቱ ቦክሱ ዉስጥ በአነስተኛ size አስቀምጠዋለሁ)