Get Mystery Box with random crypto!

ሐጂ ጦሃ ሃሩን 'ውሃብዮችን አታቅርቧቸው!' የሚል አደገኛ ትእዛዝ ለህዝብ አስተላለፉ ======= | Zidan Hayredin Offical😍

ሐጂ ጦሃ ሃሩን "ውሃብዮችን አታቅርቧቸው!" የሚል አደገኛ ትእዛዝ ለህዝብ አስተላለፉ
==========================================================
«በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ፤ ውሃብዮችን አታቅርቧቸው! የሁዳ የሱን ያክል ዲናችንን አላበላሸም።» [ሐጂ ጦሃ ሃሩን]

(ችግር ሳይፈጠር በፊት በአስቸኳይ ለሚመለከተው ሁሉ ሼር ይደረግ!)
||
የታላቁ አንዋር መስጅድ ኢማም የሆኑት "ሐጂ" ጦሃ ሃሩን ህዝብ በተሰባሰበበት መድረክ ላይ ውሃብያ የሚሏቸውን አካላት እንዳያቀርቧቸው ታዳሚውን በአላህ ስም ጠየቁ።
"ሐጂ" ጦሃ ይህን ተማፅኖ ያቀረቡት፤ ከትናንት በፊት ዕለተ እሁድ መስከረም 02, 2014 E.C በጠሮ ዑሥማን ኢብኑ አፋን መስጅድ የመድረሳ ተማሪዎች ምረቃ ፕሮግራም ላይ ነበር። "ሐጂ" ጦሃ ለመድረሳው የጀርባ አጥንት የተባለን አንድ ግለሰብ እንዲሸልሙ ከተጋበዙ በኋላ ባደረጉት ንግግር ላይ ቃል በቃል እንዲህ ነበር ያሉት፦
«አደራ የምላችሁ ግን፤ የዘመኑን በሽታ በልጁ ጭንቅላት እንዳትከቱ። ውሃቢዚም ምናሚኒዝም የሚባለው ሁሉ ለዲናችን ጠንቅ ነው። #የሁዳ_የሱን_ያክል_ዲናችንን_አላበላሸም። አሸሀዱ ቢላሂል ዐዚም! ስለዚህ የዚህ ምስል ያለበትን ሰው፣ በቀልቡ ውስጥ ትንሽ ኒፍቃ ያለችበትን ሰው፣ አታቅርቧቸው፤ በኮሚቴም በአስተማሪም! በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ!»

ለማመን ስለሚከብድ ይህን ንግግራቸውን ይሄው በዚህ ሊንክ ግቡና በቪድዮ ተመልከቱ።
@Islamic_p_p
@Islamic_p_p


ልብ በሉ!
①) ውሃብያ የሚሉትን ሙስሊም ማህበረሰብ ከየሁዳ በላይ ጠላታቸው መሆኑን ተናግረዋል። እንደት ወደ ቂብላ ዙሮ የሚሰግድን ሰው በአላህ ከካደ ሰው በላይ ይጠላሉ?
*
②) ውሃብያ የሚሉትን ሙስሊም ማህበረሰብ ከየሁዳ የባሱ ናቸውና አታቅርቧቸው ብሎ በአደባባይ ለህዝብ መናገር ግልፅ የሆነ ወንጀል ነው።
ህዝቡ የኚህን ሰው ቀጭን ትእዛዝ ወደ ተግባር ቢቀይረው ኖሮ ሊፈጠር የሚችለውን መገመት አይከብድም።
ለሃገር ሰላም በሚሻትበት በዚህ አጣብቂኝ ወቅት የጠሉትን አካል በጥላቻ ወንጅሎ የበለጠ ሁከት ማስነሳት ዝም ሊባል የሚገባው ድርጊት አይደለም።
የሚመለከተው የመንግስት አካል እንዲህ አይነት ሁከት ቀስቃሽ ትእዛዝ ያስተላለፉ አካላትን በአስቸኳይ ተጠያቂ ሊያደርጋቸው ይገባል። ተከታይ ያላቸውና የአንድ መስጅድ ኢማም የሆኑ ግለሰብ ስለ ሰላም መስበክ ሲገባቸው የጦርነት ነጋሪት የሚጎስሙ ከሆነ መዘዙ ከባድ ነው። አንዳንዶች እንዲህ አይነት ሃሳቦችን ከነ "ሐጅ" ጦሃና መሰሎቻቸው የሚገምቱ ቢሆንም፤ በዚህ ወቅት በእንዲህ አይነት ተማፅኖ በአደባባይ መተላለፉ ግን እንደ ቀላል የሚታይ አይሆንም። ምክንያቱም የዋህ የሆነ ተከታያቸው ውሃብያን መግደል ጀነት የሚያስገባ ጽድቅ ሥራ መስሎት ወደ ተግባር እንዳይገባ ያሰጋልና!

ይህ ንግግር በተነገረበት መስጅድ ላይ ከቀናት በፊት ውሃብያ ያሏቸውን አካላት የቂርኣት ፕሮግራም ለማስቋረጥ ጥረት ተደርጎ ሁከት መቀስቀሱን በገፄ ተናግሬ ነበር። ከነዚህ አካላት ጀርባ የነማን እጅ እንዳለበት ከ"ሐጅ" ጦሃ ንግግር በግልፅ መረዳት ይቻላል።

"ሐጅ" ጦሃ ይህን አሳፋሪና አስደንጋጭ ንግግር ሲናገሩ፤ በመድረኩ ላይ የአሁኑ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ፕሬዝዳንት የሆኑት "ሐጂ" ዑመር ኢድሪስ አሉ። ማስተካከያና እርምት አልሰጡም። ምናልባትም እርሳቸውም የ"ሐጅ" ጦሃ ሃሳብ ተጋሪ ላለመሆናቸው ዋስትና የለም።

ለማንኛውም በአካባቢውና በሌሎች ቦታዎችም ሁከት እንዳይነሳ «ውሃብዮች ከየሁዳ የባሱ ናቸውና አታቅርቧቸው!» የሚል ብይን (ፈታዋ) እና ትእዛዝ ያስተላለፉት ግለሰብ በአስቸኳይ ተጠያቂ እንዲደረጉልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን።
የሚመለከተው አካል ይህን ባለማድረጉ የተነሳ አንዳች ችግር ቢከሰት፤ ኃላፊነቱን በአግባቡ ባለመወጣት ተጠያቂ መሆኑ አይቀርም።

(ችግር ሳይፈጠር በፊት በአስቸኳይ ለሚመለከተው ሁሉ ሼር ይደረግ!)

ሰላምና እድገት ለሃገራችን ኢትዮጵያ !

መስከረም 04, 2014 E.C
September 14, 2021 G.C