Get Mystery Box with random crypto!

እነእስታሊን ግን ''ሼም'' የሚባለውን ነገር የሚያውቁት መቼ ይሆን ? ህወሓት ሰሜን እዝን በጨፈ | ዘሪሁን ገሠሠ

እነእስታሊን ግን ''ሼም'' የሚባለውን ነገር የሚያውቁት መቼ ይሆን ?

ህወሓት ሰሜን እዝን በጨፈጨፈና በሀገሩ ላይ ክህደት በፈፀመ ማግስት ፣ ' ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ'  ውስጥ ሆኖ ኤርትራን ''ኧረ ተበላሁ ድረሽልኝ!'' ያለው እናንተ ''መሽረፈት' የምትሉት ፣ አብይ አህመድ ነበር።

ያኔ እነስታሊን ገ/ስላሴ ፣ በአልጀርሱ ስምምነት መሠረት ተወስኖ ነገርግን በኢትዮጵያ ስር የቆዩ የተወሰኑ የባድመ ወረዳ ቀበሌዎችን '' አብይ የትግራይን ህዝብ ለማስጨፍጨፍ በእጅ መንሻነት  ሀገሩን ቆርሶ ለኤርትራ የሰጠ ባንዳ ነው! >> ብለው እሪሪሪ... ሲሉ ፣ የብልፅግና ሰዎች ደግሞ '' እኛ ለሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ስንል ፣ ወያኔ በአለምአቀፍ ፍርድ ቤት ተወስኖበት ያልፈፀመውን ነው ተፈፃሚ ያደረግነው እንጂ አዲስ መሬት አልሰጠንም! >> የሚል ሙግት ያቀርቡ ነበር።

እንግዲህ ዛሬ '' ደፈረን ፣ አስደፈረን ፣ ጨፈጨፈን አስጨፈጨፈን ፣ ...'' ስትሉት የነበረው አብይ አህመድ ፣ ''አሰብ ወደብን ላስመልስ...!'' በሚል የድጋፍ መሠብሰቢያ ካርድ ፣ የምእራባውያኑ የውክልና ጦርነት አስፈፃሚ ሆኖ እልቂት ደግሶ ሲመጣ ፤ እናንተ የጥላቻ ለሀጫችሁን የምታዝረበርቡበት የአማራ ልሂቅ  ፣   << ገንጣይ አስገንጣዩ ወያኔ  የአሰብን ጉዳይ ጨምሮ የኤርትራን ሉአላዊነት ያወጀው በአለም አደባባይ ነው ! ስለዚህ የአንድን ሉአላዊ ሀገር ክብር ከመዳፈር ይልቅ ፣ ከኤርትራ ጋር ወደቡንም በፍቅር እንጠቀማለን ፣ ወጀቡንም አብረን እናልፋለን! >> ቢል ስህተቱ ምንድን ነው?

ይሄን ማለቱስ ከቀደመ አቋሙ ጋር በምን ይቃረናል? ገንጣይ አስገንጣዩን ትህነግስ በምን መልኩ ከተወቃሽነት ይታደገዋል ? በሁለት አመት ውስጥ የእናንተ የማይታረቅ ተቃርኖስ የሚታያችሁ መቼ ነው!

ግዴላችሁም ሼም የሚባለውን ነገር አልፎ አልፎ እንኳ እወቁት!