Get Mystery Box with random crypto!

ከእንግዲህ ፦ መንግስት መር ለሆነው የወገኖቻችን ጭፍጨፋ ፤ ፈጣሪን እንጂ መንግስትን 'ድረስላቸው | ዘሪሁን ገሠሠ

ከእንግዲህ ፦ መንግስት መር ለሆነው የወገኖቻችን ጭፍጨፋ ፤ ፈጣሪን እንጂ መንግስትን "ድረስላቸው!" አልልም!

የክፋትና ሀገር የማፍረስ አጀንዳቸውን ለማጣፋት የሚሞክሩትም ፥ በሌላ የክፋትና የጭካኔ አጀንዳ ነው!

በትናንትናው እለት በምስራቅ ወለጋ ዞን፥ ጎቡ ሰዮ ወረዳ በአኖ ከተማ የተለመደው አሰቃቂ ማንነትን መሠረት ያደረገ የዘር ፍጅት መፈፀሙ ታውቋል፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ በጨፍጫፊው ቡድን ታግተው ከተወሰዱት 50 ሰዎችና አስከሬናቸው ካልተነሱት ውጪ ፥ አንድ ጭፍጨፋውን የተቃወመ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅን ጨምሮ 23 ሰዎች በስም የታወቁ የጭፍጨፋው ሰለባ መሆናቸው ተገልፇል፡፡

የሟቾቹ ስም ዝርዝር ፦

1. አብዱ ሱፍያን
2. አማን ሰይድ
3. አብዱ ሰይድ
4. ጋሻው ክብረት
5. ከማል መሀመድ
6. ደምሴ ምስጋናው
7. ሰይድ ሙላት
8. ኢብራሂም ሰይድ
9. ሽህ/ ሰይድ ውሴን
10. መሀመድ ቃሲም
11. ካሳዬ ገዛኸኝ
12. መሀመድ አደም
13. ማርዬ እንድሪስ
14. እማዋይ ይመር ከእነ ቧሏ
15. መሀመድ እስማኤል
16. አሊ ሲራጅ
17. አለባቸው -----?
18. መሀመድ ሸኪ
19. ካሳዬ ታደሰ?
20. የኑስ ሰይድ
21. ሱፍያን ሰይድ
22. መሀመድ ይብሬ
23. ጉተታ ዘንባባ (የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ የሆነ ሲሆን የተገደለው ለምን ንፁሀን ወንድሞቻችን ትገድላላቹህ?" ብሎ ቁጣውን በመግለፁና ተፈናቃይ ወገኖችን ሲደግፍ ሲያበረታታ ተስፋ ሲሰጥ የነበረ በመሆኑ የተገደለ ነው፡፡

ጥቃቱ ጥር 25/2015 ንጋት ላይ ከመፈጸሙ ቀደም ብሎ በጥር 24/2015 በአካባቢዉ ሰፍሮ የነበረዉ መከላከያ ሰራዊት በአቅራቢያው ወደምትገኘው ስቡበስሬ ከተማ የተወሰደ ሲሆን ፥ ጨፍጫፊው ቡድን ጥር 25/2015 ዓ.ም ንጋት ላይ ፥ ያለምንም ከልካይ በተሽከርካሪ ተጓጉዞ በመምጣት ፥ ጭፍጨፋ ፈፅሞ ፥ በርካቶችን አግቶ ፥ የመንግስትና የግል ንብረቶችን አውድሞና ጭኖ መሄዱን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል፡፡

ከሟቾቹና ከታጋቾቹ መካከል አብዛኞቹ ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ ከኖሩበት በጎቡ ሰዮ ወረዳና በ አከባቢዉ ባለፉት አመታት በደረሰባቸው ጥቃት ተፈናቅለው ወደወረዳው ከተማ አኖ የመጡ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

ጠዋታ ማታ በንፁሐን የደም ጎርፍ በምትታጠበዋ ወለጋ በፍ የተጨፈጨፉትን ወገኖቻችንን ነፍስ ይማር !

አዎ! መንግስት መር ለሆነ ጭፍጨፋ ፈጣሪን እንጂ መንግስትን "ድረስላቸው!" አልልም!