Get Mystery Box with random crypto!

የደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት - በተማሪዎች ውጤትም ሆነ በትምህርት ቤት ደረጃ በተመዘገበው ውጤት | ዘሪሁን ገሠሠ

የደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት - በተማሪዎች ውጤትም ሆነ በትምህርት ቤት ደረጃ በተመዘገበው ውጤት ከሀገር አቀፍ አንደኛ ነው!

ወንድማችን ውብሸት ሙላት ባጋራን መረጃ መሠረት ፦

በትምህርት ቤቱ አጠቃላይ የተፈተኑ ተማሪዎች ብዛት- 69 ሲሆን እስካሁን የ68ቱ ተማሪዎች ውጤታቸው ታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት የተማሪዎቹ ዝርዝር ውጤት፦

~ 25 ተማሪዎች - ከ600 በላይ
~ 40 ተማሪዎች - ከ 500 - 599
~ 3 ተማሪዎች 450-499 ማስመዝገባቸው ታውቋል፡፡ ውጤቱ ያልታወቀው የአንድ ተማሪ ብቻ ነው።

በቅርብ ጊዜ ትልቅ ራዕይን ሰንቆ እውን በተደረገና ብዙ ርቀት ሳይጓዝ ከኮቪድ በኃላ ፥ ለረዥም ጊዜ በጦርነት ውስጥ በቆየውና ብዙ ውድመት ባስተናገደ አዳሪ ት/ቤት ፥ ይህን በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ ይህን ትምህርት ቤት ማሳደግና ማጎልበት ብሎም ማስፋፋት ለወደፊቱ የሀገር ተረካቢ የሚሆኑ ብቁ ዜጎችን ለመፍጠር እንደሚያስችል የተገኘው ውጤት በቂ ማሳያ ነው!