Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ ዜና! የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፣ ባለቆንዳላ የኦነግ ሸኔ አባላት ፣ የሚሊሻ አባላት እና ወጣ | ዘሪሁን ገሠሠ

አሳዛኝ ዜና!

የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፣ ባለቆንዳላ የኦነግ ሸኔ አባላት ፣ የሚሊሻ አባላት እና ወጣቶች በጋራ በመሆን በሀሮ አዲስ ዓለም አማራዎች ላይ ተኩስ ከፍተዋል!

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ሀሮ አዲስ ዓለም ቀበሌ ላይ ህዳር 21/2015 ከቀኑ 7:30 ጀምሮ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፣ ባለቆንዳላ የኦነግ ሸኔ አባላት፣ የሚሊሻ አባላት እና ወጣቶች በጋራ በመሆን በይፋ ጦርነት ከፍተዋል የሚሉት የአካባቢው ነዋሪዎች በየጫካው በመሳደድ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ዲሽቃን ጨምሮ ሌሎች የቡድን መሳሪያዎችን በመጠቀም በሀሮ አዲስ ዓለም ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ የተጠናከረ ወረራ እየተፈጸመ መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል።

ህዳር 9 ፣ 10 ፣11 እና 20/2015 ዓ.ም በኪረሞ ፣ በጃርዴጋ ፣ በሰቀላ እና በአካባቢው በርካታ አማራዎችን ከኦነግ ሸኔ ጋር በመሆን የጨፈጨፈው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፥ ዛሬ ህዳር 21/2015 በሀሮ አዲስ ዓለም ተፈናቃይ ህዝብ ላይ ይፋዊ የወረራ ጦርነት ከፍቶ ከተማዋን እያወደመ እና ህዝቡን እያሳደደ መሆኑ ተገልጧል።

ሀሮ አዲስ ዓለም ከነሃሴ 2013 ጀምሮ ባለፉት ዓመታት ከመረጋ ጅሬኛ ፣ ከስኒ ዶሮ ፣ ከቦቃ እና አካባቢው እንዲሁም ከሌሎች የኪረሞ ቀበሌዎች በግፍ የተፈናቀሉ ብቻ ከ50 ሽህ በላይ አማራዎችን ያስጠጋ አካባቢ ነው።

በተጨማሪም ከህዳር 9 እስከ 20/2015 ከኪረሞ ፣ ከወዴሳ ዲማ እና አካባቢው በኦሮሚያ ልዩ ኃይል የተፈናቀሉ ከ52 ሽህ በላይ አማራዎችን ተቀብሎ እያስተናገደ ይገኛል።

በጥቅሎ ነዋሪዎችን ጨምሮ በመቶ ሽህ የሚቆጠር የአማራ ህዝብ የሚኖርበት ሀሮ አዲስ ዓለም ከነቀምት እና ከኪረሞ በእነ አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተላከው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሾችና ቄሮዎችን ጨምሮ ከባለቆንዳላው አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጋር በመተባበር ይፋዊ ጦርነት የተከፈተባቸው መሆኑ ታውቋል።

መንግስት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ያደረጉት በጫካ እየተሳደዱ ያሉ ነዋሪዎች በአስቸኳይ ድረሱልን ሲሉ ጥሪ አድርገዋል።

ዘገባውን ያደረሰን "አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ " ነው፡፡