Get Mystery Box with random crypto!

ይድረስ ለፋኖ ወንድሞቻችን! 'የአማራ ፋኖ አንድነት ምስረታ!' የሚል መረጃ በተለያዩ መንገዶች | ዘሪሁን ገሠሠ

ይድረስ ለፋኖ ወንድሞቻችን!

"የአማራ ፋኖ አንድነት ምስረታ!" የሚል መረጃ በተለያዩ መንገዶች በስፋት ሲስተጋባ እያየሁ ነው፡፡ እርግጥ ነው! እንቅስቃሴው የማያስደስተው ቢኖር እርሱ በተቃራኒዉ ምድብ ያለ ሀይል ነው፡፡ ነገርግን ከእስካሁኑ ብዙ ልምዶቻችን ተነስቼ እንደታናሽ ወንድማችሁ << ግዴላችሁም! ድምፃችሁን አጥፍታችሁና ከትናንታችሁ ተምራችሁ ፥ መሬት ላይ ከአለት የጠነከረ ተቋምና አደረጃጀት ገንቡ! >> በማለት የተሰማኝን ልገልፅላችሁ እወዳለሁ!

በተጨማሪ አንዳንድ የየቱብም ሆነ የሜንስትሪሚንግ ሚዲያዎች ብሎም የሳይበር አንቂዎች ፥ በሚመለከተው አካል ሳንሱር ተደርገው ከሚወጡ ፋይዳቸው የጎላ መረጃዎች ውጪ የፋኖን መሪዎችና አባላት ኢንተርቪ ከማድረግ ብሎም ያገኛችሁትን ሁሉ ወደአደባባይ ከማውጣት ብትታቀቡ ትርፉ የትየለሌ መሆኑን ሳልጠቁም አላልፍም!

በእኛ ሀገር ብልሹ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ፥ ድምፅን አጥፍቶ በወጀቡ የማይናወጥ ፥ መነሻና መድረሻ ግቡን በቅጡ የተረዳ ህዝባዊ አደረጃጀት መፍጠር ብልሀት እንጂ ፍርሀት አይደለም!