Get Mystery Box with random crypto!

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ የመንግሥት አመራሮችን ማፈኑ ተገለፀ! በሁሉም | ዘሪሁን ገሠሠ

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ የመንግሥት አመራሮችን ማፈኑ ተገለፀ!

በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እንዳሻው እየተንቀሳቀሰ ጭፍጨፋ የሚፈፅመው ኦነግ ፥ መጠነ ሰፊ እንቅክቃሴ ከሚያደርግባቸው አካባቢዎች መካከል የጉጂ ዞኖች ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ናቸው፡፡

በጉጂ ዞን ቡድኑ ከሠሞኑ እንኳ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ታጣቂዎቹን ያስመረቀ ሲሆን አካባቢዎችን በመቆጣጠር ወደሞያሌና አዲስአበባ የሚደረጉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎችን በመግታት ብሎም ዘረፋና ግድያ በመፈፀም ላይ ይገኛል፡፡

ይህ ነፍሰበላ ቡድን በትናንትናው እለት ማለዳ በምእራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ ሁሩፋ ከተባለ አካባቢ በነዋሪዎች ላይ ጥቃት የፈፀመ ሲሆን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ነዋሪዎች ተገድለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ቡድኑ በፎቶግራፍ አስደግፎ ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ፥ በዚሁ ወረዳ የወረዳው የካቢኔ አመራሮችን ፥ የፖሊስና የሚሊሻ አባላትን ማእከል አድርጎ በከፈተው ጥቃት ወደ13 የሚሆኑትን በመግደል 3ቱን አፍኖ መውሰዱ አስታውቋል፡፡

በአሸባሪ ቡድኑ ከታፈኑት መካከልም ፦

1ኛ. አቶ ደስታ ገለቶ - የወረዳው አመራርና ካቢኔ
2ኛ. አቶ አብረሀም ዋዱ - የፖሊስ አባልና ሌላ በስም ያልታወቀ የሚኒሻ አደራጅ እንደሚገኙበት ተገልፇል፡፡

ጉጂ ዞኖች ቡድኑ በከፍተኛ ሁኔታ አሸባሪዎቹን እየመለመለ የሚያሰለጥንባቸውና መጠነ ሰፊ የሽብር እንቅስቃሴ የሚያደርግባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡